Saturday, September 1, 2012


የአቶ መለስን ዜና እረፍት ሲሰሙ አላዘኑም ወይም አላግጠዋል የተባሉ ወደ ሰንዳፋና ሸዋ ሮቢት እስርቤቶች ተላኩ


ነሀሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት በርካታ አስገራሚ ነገሮችን እያሳየ በመጠናቀቅ ላይ ነው። እሁድ እለት አብያተ ቤተክርስቲያናት ለአቶ መለስ ልዩ የጸሎት ስነስርአት እንዲያዘጋጁ መታዘዙ በተሰማ ማግስት፣ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ አላግጣችሁዋል ወይም በደንብ አላዘናችሁም የተባሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ በርካታ ወጣቶች በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ (ማዕከላዊ)፣ ሰንዳፋ እና ሸዋሮቢት ተወስደው መታሰራቸውን የኢሳት የፖሊስ ምንጮቻች ገልጸዋል፡፡ አብዛኞቹ ወጣቶች አቶ መለስ ዜናዊ ለአገር የሰሩት ስራ ለም፣ የእርሳቸው መሞት ለኢትዮጵያ እረፍት ነው፤ የበሉት ሲያለቅሱ፣ ያልበላነው እንስቃለን የሚሉ ንግግሮችን እንደተናገሩ እንዲሁም  ፎቷቸውን ለመስቀል እና ለቲሸርትና ለፎቶ የሚዋጣውን ብር በተቃውሞ አልተቀበሉም የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
በሰንዳፋ የሚገኙ ብዙዎቹ እስረኞች በተበሳጩ ወታደሮች እንደተደበደቡ እና ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሎአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚካሄደውን  የቀብር ሥነ-ስርዓት ለከፍተኛየኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ለክልል የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ለውጭ አገራት መሪዎች፣ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና ለታዋቂ ሰዎች ደህንነት ሲባል  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የደህንነት አባላት ለጥበቃ መመደባቸው ታውቋል። በከፍተኛ የደህንነት ጥበቃ  ስነስርአቱን ለማካሄድ ለምን እንደተፈለገ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች በስነስርአቱ ላይ እንደሚገኙ መገለጡ ውጥረቱን ሳይጨምረው አልቀረም።
በርካታ የአዲስ አቅራቢያ እና አካባቢ ህዝቦች በአዲስ አበባ መግቢያ አራቱም በሮች  ማለትም በኮተቤ፣ አየር ጤና፣ ሰሜን መዘጋጃ እና ፣ ቃሊቲ አካባቢዎች በተዘጋጁት ትላልቅ ሶኒክ ስክሪኖች የቀብር ሥነ- ስርዓቱን እንዲከታተሉ የተመቻቸ ሲሆን በመሐል አዲስ አበባም በፒያሳ በማዘጋጃ ቤት አቅራቢያ፣ በመገናኛ ፣ በአስኮ፣ በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ቦታዎች ዋልታ የኢንፎርሜሽን ማዕከል የሚቆጣጠረው የመረጃ መረብ ተተክሏል።  የኢቲቪን  የቀጥታ ሥርጭት  የዋልታን ዶክመንተሪዎችና ልዩ ፕሮግራሞች ወደ ህዝቡ እንደሚያሰራጭ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የተተከሉትን እና ቀደም ሲል የነበሩትን ትልልቅ ሶኒክ ስክሪን የመረጃ፣ የፕሮፓጋንዳ እና ማስታወቂያ ማስተላለፊያ ስክሪን የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ክንፍ የሆነው ዋልታ የመረጃ ማዕከል በባለቤትነት በመቆጣጠር ይሰራባቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸው፣ ለዚህም ድርጊቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመንግስት ካዝና ወጪ ተደርጎ እንደሚከፈለው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን በሀዘኑ ምክንያት እንዳያስነግር በታዘዘበት በዚህ ወቅት የአቶ መለስን የዶክመንታሪ ስራዎች ሰርቶ ለኢቲቪ በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ገቢ የሚያስገኝ ስራ መስራቱ ታውቋል።
በተያያዘ ዜናም   የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማህበር የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን በሙዚየም እንዲቀመጥና በህይወት ዘመናቸው የሰሩት አኩሪ ስራ እንዲታወስ መጠየቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገበ።
ኢዜአ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ፋሲል ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አገሪቱ ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገብ በአለም አቀፍ ተጠቃሽ እንድትሆን የጣሩ መሪ በመሆናቸውና በህዝቦች ተፈቃቅሮና ተሳስቦ የመኖር ባህል በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ያደረጉ በመሆናቸው ማኅበሩ አስከሬናቸው ሙዚየም ይቀመጥ የሚል አቋም ይዟል ብሎአል።
አገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ዕቅድ ያወጡና ኢንዱስትሪው መሪ እንዲሆን ብቁ አመራር የሰጡ በመሆናቸው ታሪካቸው ለትውልድ እንዲተርፍ አስከሬናቸው በሙዚየም እንዲቀመጥ የሚለውን ሃሳብ ህብረተሰቡ እንዲወያይበት እንጠይቃለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በምዕተ ዓመቱ ያገኘችው ታላቅ መሪ በመሆናቸው ህያው ስራቸው ለትውልድ መትረፍ አለበት ያሉት ፕሬዚዳንቱ አስከሬናቸው በሙዚየም ቢቀመጥ ስራቸው ህያው እንዲሆንና ትውልድ እንዲማርበት እንደሚያደርግ ገልፀዋል እንደ ኢዜአ ዘገባ።
አስከሬኑ በሙዚየም የሚቀመጥ መሪ ለአገሩ ትልቅ እመርታን ያስገኘ ነው ያሉት አቶ ፋሲል እኚህ ታላቅ መሪ አገሪቱን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት ትልቅ ትግል ያደረጉና ትልቅ ዕቅድ ወይም መስመር የዘረጉ ባለ ራዕይ መሪ በመሆናቸው ይህ ይገባቸዋል ብለዋል።
የአስከሬኑ መቀመጥ መጪው ትውልድ የእሳቸውን አርአያ በመከተል መልካም ጅምሮችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር እንደሚያደርግም አክለዋል።
የአቃቂ ጋርመንትና ጂጂ ጋርመንት ስራ አስኪያጅና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ጌታቸው ቢራቱ በበኩላቸው እንደተናገሩት የጥንት አባቶቻችን ”ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል” ይላሉ እኛም ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳይርቁና የእሳቸውን አርያነት እንድንከተል አስከሬናቸው በሙዚየም ይቀመጥ የሚል ሀሳብ አለን ማለታቸውን የመንግሰት የዜና ወኪል ገልጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንትና ለዚች አገር ነፃነት የተዋደቁ፣ ዛሬ ላይ ልማቷን አፋጥነው በዕድገት ጎዳና እንድትጓዝ ያደረጉና ለዚህች አገር የሞቱ በመሆናቸው የእኚህን ድንቅ መሪ አፅም አለም እንዲያየው ሙዚየም ቢቀመጥ ደስተኛ ነኝ ሲሉ አክለዋል።
በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የተፈለገው ደረጃ እንዲደርስና ዘርፉ ያለበት ችግር እንዲወገድ ሌት ቀን ከእኛ ጋር ሲሰሩ የኖሩ በመሆናቸውና በማለፋቸው ከፍተኛ ሃዘን ቢሰማንም ህያው እንዲሆኑ አስከሬናቸው ሙዚየም ይቀመጥ የሚለው የማህበሩ አባላት ሃሳብ ነው ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሶሎኔስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ይድነቃቸው ታዬ ናቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በእምነታቸው ያልጠነከሩና በመንፈሳዊ ዕውቀት ያልታነጹ እንዲሁም በጥቅም እና በዘር የተጋረዱ አንዳንድ ወገኖች ሰሞኑን በአቶ መለሰ አስከሬን ፊት ወድቀው ሢሰግዱ የተስተዋለ ሲሆን፤ የሥርዓቱ አገልጋዮችም ይህንኑ ትዕይንት በካሜራቸው እያስቀሩ  የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ባለፉት 21 ዓመታት የአቶ መለስ አስተዳደር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውን፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ታፍነው መጥፋታቸውን፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ለእስራት፣ለግርፋትና ለስደት መዳረጋቸውን እና ሌሎችም እጅግ ዘግናኝ የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ለ9 ዓመታት በ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ የሰሩት አቶ ያሬድ ሀይለማርያም አጋልጠዋል።
አቶ ያሬድ ፦”የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረጉት “ዶክመንት” በአቶ መለስ አመራር የተፈፀሙትን አስከፊ የጭካኔ ተግባራት  በፎቶና በስም ዝርዝር ጭምር አመላክተዋል።
የዋልታ ማእከል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተተካ በቀለ ለሰራተኞቻቸው ባደረጉት ንግግር ደግሞ  “በምንወዳቸው መሪያችን ሞት ልባችን ቢሰበርም ወደ ኋላ ተመልሰን ድህነት ውስጥ እንደማንገባ እርግጠኞች ነን ብለዋል።” አቶ ተተካ ገልፀዋል።
በአለም ላይ በድህነት የነበሩ ሀገራት ከፍፁም ድህነት ወደ ፍፁም ብልፅግና የተሸጋገሩት ጥቂት ባለ ራዕዮች ያፈለቁትን ሀሳብ ቀጣዩ በትውልድ ውስጥ እየተቀባበለ እንዲሄድ በማድረግ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በኢትዮጵያ ባለው ትውልድ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ፅናትን፣ ህዝብ መውደድንና ለአላማ መኖርን ያስተማሩ ታላቅ መሪ ነበሩ ያሉት ስራ አስኪያጁ ለመጪው ትውልድ ለኑሮ የምትመች ሀገር ፈጥረውልናል ብለዋል።

የሕዝባዊ ከያኒ ያለህ !


የዛሬው ‘ የጽናት’ ሬድዮ ጋዜጠኛ የቀድሞው አቀንቃኝ ሰለሞን ተካልኝ ‘ቅንድባሙ መሪ’ የሚለውን ዘፈኑን ወደ ሸገር ዘልቆ ካስባረካና ከስርዐቱም ጋር እርቅ ካደረገ በሁዋላ የመጀመሪያ ልምጩን ያሳረፈው የሙያ ወዳጁ አቀንቃኝ ነዋይ ደበበ ላይ ነበር። ( አቀንቃኝ ሲያረጅ ኮሚቴ ይሆናል መሰል ነዋይ ደበበ የልቅሶ ኮሜቴ አመራር ውስጥ ይህን ጽሁፍ ሳዘጋጅ ሰማሁ ሹመት ያዳብር ብለናል ነዋይ ) የሰለሞንን እርቅና እርሱን ተከትሎ አውራ ወያኔ ለመሆን መሻቱን ካልወደዱለት መሃል ነዋይ አንዱ ሳይሆን አልቀረምና ሰለሞን እንዲህ ሲል የወረፈው ዛሬ ድረስ ፈገግ ያሰኘኛል፡
ፍየል ቅጠል እንጂ አትበላም እንጉዳይ
በጥርሷ ሰላሳ በአይኗ መቶ ገዳይ
የሚለውን የነዋይ ዘፈን አዜሞ ሲያበቃ ከመቼ ወዲህ ነው ፍየል በጥርሷ መቶ ስትገድል ነዋይ ያየው ሲል አድማጮቹን በተሳልቆ ድምጸት ጠየቀ። ሰለሞን በዚህም አላበቃም ነዋይ በሶስተኛ ወገኖች በኩል ወደ ሀገሩ ለመግባት ‘ድርድር’ ላይ እንደሆነ እንደሚያውቅ ሁሉ ለሬዲዮ አድማጮቹ ጠቅሶ አላርፍ ካልክ ‘ ብዙ እናውቃለን’ ሊለው ቃጥቶት ነበር። (ምናልባትም ሁለቱንም ልማታዊ አቀንቃኝ ይሆኑ ዘንድ ከስርዓቱ ጋር የሚያደራድሯዋቸው ሰዎች መረጃ እየሸላለሙ ያቃርኑዋቸውም ይሆናል) ዛሬ ነዋይ ደበበም ሰለሞንም የስርዓቱ ልማታዊ አቀንቃኞች ናቸው። ምን አልባትም ቀድሞ ለሰለሞን ያልታየው የፍየሊቱ አይነ ገዳይነት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጸበል ሲጠመቅ ይገባው ይሆናል። አልያም ነዋይ ሂስ ውጦ የፍየሊቱ ጉዳይ ትምክህተኛ አመለካከት እንደሆነ ያምንም ይሆናል ። ከዚህ ባለፈ ግን የእነርሱ እንካ ሰላንታ ፤ የእነርሱ ትላንት ሰበታ ነገ ወላይታ መገኘት እኪነት አካባቢ ምን እየሆነ ነው ወደሚለው ጨዋታ ይወስደናል። የአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት ተከትሎ የታዘብነው ደግሞ ምነው በዚህ ዕድሜ ፤ ምነው ምነው ፕርፌሰር እገሌ ፤ ምነው አትሌት እገሌ ፤ ምነው ዶፍተር እንቶኔ ደግሞ ደጋግሞ አሰኝቶናል። ምንም እንኳን ያለፉት ጥቂት ቀናት የአርቲስቶቻችንን ብዛት ከሺዎች ከፍ አድርጎት ፌዲራል ፓሊሱም፤ አትሌቱም፤ ዶክተሩም፤ ካድሬውም ፤ የዪኒቨርሲቲ መምህራን ሳይቀሩ ተሰጥዖዋቸውን ካሜራ ፊት ያሳዩበት ቢሆንም ማህበረሰባችን አልቦ የኪነት ሰው መሆኑን ያሳየበት ሁነት ይበልጥ ገኖ ተስተውሏል።
በቅርቡ የማውቀው አንደ ሰው መቼ ይሆን ሀገራችን ህዝባዊ ከያኒ የሚኖራት ሲል የሞገተኝ ጉዳይ እነዚህን ለቅሶ ተኮር ክስተቶች ካስተዋልኩ በሁዋል ይበልጥ ይከነክነኝ ገባ።ይህ ሀሳብ የብዙዎች እንደሚሆንም እገምታለሁ። ከያኒዎቻችን በተለይም አቀንቃኞቹ ‘ የአዝማሪነት’ ዘመን እንዳበቃና አዲስ የአብርሆተ ከያኒነት ጊዜ እንደባተ በተደጋጋሚ ሲነግሩን ነበር የቆዩት አንዳንድ አጉል ጊዜ እየመጣ ሲሸሹት ከኖሩት ‘ የአዝማሪነት’ ምግባር አሁንም አንዳልወጡ ባያሳብቅባቸውም። ለጨዋታችን መስመር ሲባል የአቀንቃኞቹን ጉዳይ እፊት ረድፍ አስቀመጥኩት እንጂ የሌላውም የኪነት ዘርፍ ( ስነ ስዕሉም ፤ ተውኔቱም ፤ የፊልም ጥበቡም ፤ ድርሰቱም ) ከእነርሱ ቢብስ እንጂ የተሻለ አይሆንም። የደራሲያን ማህበር መሪ አቶ መለስ በህይወት ሳሉ የወርቅ እስኪርቢቶ ሸልሞአቸው ሲያበቃ የማህበሩ አባል እንዲሆኑ ለጠየቃቸው አስብበታለሁ ያሉትን ይዞ ሲቃ እየተናነቀው ደስታውን ለካሜራ ሙያተኛው ሲያጋራውና ሰውየው መጽሀፍ ትራሱ መሆናቸውን ሲናገር ቤተ መንግስት ነው እንዴ የሚኖረው ስንል እርሳችንን ከጠየቅን አመት አይሞላም። እንዲህ አይነቱ ገጠመኝ ጉዳዩ ሐገራዊ ወረርሽኝ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ ያሰያል። አንዳንዴ በአንክሮ ላስተዋለ ባለቅኔ ጸጋዬ ገ/መድህንም ይኽኛውም አደግዳጊ እኩል ደራሲ መሰኘታቸው ግርምትን የግድ መጫሩ አይቀርም። ኢትዮጵያ መቼም የፍቅረ አዲስ ነቅአ ጥበብን ‘ የሀሙሱ ፈረስንም’ የጻፈውም እንደ በዓሉ ግርማም አይነቱ ምጡቅና ደፋር ደራሲ አንድ አግዳሚ የሚቀመጡባት ሐገር ነችና አንዳንድ የቁጩ ደራሲ ነኝ ባይ ሲያጋጥምም ወይ ነዶ ከማለት ውጪ ማለት ምን ይባላል ? በተለይም የኋለኛው ልማታዊ ደራሲ ከሆነ ከግንድ የሚያጋጭ አባት አጋር ሲኖረው !
ጉዳዩ ከተነሳ አይቀር ጥቂት ስለ ‘ህዝባዊ ከያኒ’ ሀሳብ መጨዋወቱ የሚሻል ሳይሆን አይቀርም። በመጀመሪአይ ሕዝባዊ ኪነት ካልሆነው እንጀምር። ሕዝባዊ ከያኒ የዚህኛውን ወይም ያኛውን የፓለቲካ ቡድን የሙጥኝ ብሎ ‘ እምበር ተጋዳላይ’ አልያም ‘ጀግናን ይወዳል ልቤ’ የሚል ማለት አይደለም። ብዙዎች እንደሚስማሙበትም ወይ ደረቱ ፤ ወይ ሽንጧም ሲል ዘወትር ለፍትወት ንሸጣም የሚያሸረግድም አይደለም። ሕዝባዊ ከያኒ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፤ ፓለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ችግሮች ባለበት ሐገር ዘወትር ለምን እያለ የሚጠይቅ፤ ጊዜ ከሞላላቸው ሚሊዮኖች ይልቅ ቀን የጎደላባቸውን ጥቂቶች ለቅሶ የሚያስተጋባ ድምድ ነው። በአጭሩ የሕዝባዊ ከያኒ ወገንተኝነቱ ከግፉአን እና ምንዱባን ዘንድ እንጂ ከባለጊዚዎች ጋር አይደለም። ሕዝባዊ ከያኒ የጥበብ ስራውን ለእውነት ባለው ቅርበት የሚመትር እንጂ በንዋያዊ ፍይዳውንና በአድናቂው ብዛት የማይለካ የጥበብ ሰውም ነው። ሕዝባዊ ከያኒ እውነተኛዋ ኪነ ጥበብ አንገት የምታስቀስፍ እንጂ ቤተ መንግስት የምታደገድግ አለመሆኗንንም ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝባዊ ከያኒ ‘ሕዝባዊ’ ነው ብንልም የብዙኋኑን ጉድፍ ለመንቀስና ለመሄስ ወዳ ኋላም አይልም እንዲያውም በተቃራኒው ሕዝብ በመንገኝነት አስተሳሰብና ልማድ የሚሄድበትን የዘወትር መንገድ ‘አይሆንም’ የጥፋት መንገድ ነው እያለ የተሻለ የመሰለውን ሀሳብ የሚጠቁም ነው።
ጥያቄው ታዲያ ምነው የእኛ ምድር ለምን ሚሊዮን አዝማሪዎች ግፋ ካለም ጥቂት ‘ልማታዊ’ ከያንያን ብቻ በዙባት ነው። የኢንቨስትመንት መሬታቸውን ጉልበተኛ ሲነጥቃቸው ግጥምና ዜማ ለመሬታቸው የሚያወጡ ዘፋኞች፤ አምባገነኖችን በቁማቸው ‘ ንጉሱ እርቃኑን ነው’ ሊሉ ሲገባቸው ለአስከሬናቸው ‘ የሙሴ በትርን’ የሚቀኙ (ቅኔ ከተባለ)፤ የቲያትር ድርሰታቸው ለተቃዋሚ ሀሳብ ያዘማል ተብሎ ከመድረክ በታገደባቸው ሳምንት ‘ ልማቲው ቲያትር’ ሊያሰተምሩ ባህር ዳርና ጎንደር የሚረግጡ ባጠቃላይ ዝለል ሲባሉ የት ድረስ እንጂ ለምን የማይሉ ‘አርቲስቶች’ ብቻ ያች ምድር ስታፈራ የኪነ ጥበብ ግዝትና እርግማን ይኖርብን ይሆን አሰኝቶ ጥያቄ ውስጥ መክተቱ አይቀርም።
ለማንኛውም ብቁ የፓለቲካ ሰዎችን የመፍጠሩ ነገር የእኛው ጉዳይ እንደመሆኑ እውነተኛ ከያኒያንን የመውለዱም ነገር የጋራ ፈተናችን መሆኑን ልብ ማለት ይገባል። አቀንቃኞቻችን ‘ ፍየል ቅጠል እንጂ …’ ባሉ ቁጥር ቁጭ ብድግ ማለታችን የትም እንዳላደረሰን ጊዜ አስተምሮናል። ለፍትሕ የሚሟገቱ ሕዝቦች ቀድሞም አሁንም እንደሚያደርጉት ቅድሚያው የሕዝብ ጉዳይ መሆኑን አስተውለን ከያኒዎቻችንን አንቱ ከማለታችን በፊት ሚዛን ላይ ማስቀመጡና የሀሳባቸውንና አቋማቸውን ጥንካሬ መመርመሩ ግድ የሚል ይመስላል። በየስደቱ ሐገሩም በሀገር ቤትም ‘አቧራ’ የሸፈናቸውን ሕዝባዊ ከያንያን ማበረታታቱ አዲስ መጪዎቹንም ከአገልጋይነት መነፈስ ወጥተው እውነትን፤ ፍቅርንና ፍትህን የሚሹ ይሆኑ ዘንድ መንገድ ማሳየቱ ተገቢ ተግባር ነው። እንደተለመደው ደግሞ ትልቁ ሀብታችን ‘ ተዓቅቦ’ ነውና አፍቃሪ ወያኔ አቀንቃኞች እነ ‘ ወይ ደረቱን’ ይዘው ኪሳችሁን እንለባችሁ ሲሉ ወግዱም ማለት ትልቅ ነገር ነው። የመሀመድ አላሙዲንን ማባባል ያሸነፈ ትውልድ የፍቅረ አዲስንና የማዲንጎን ‘እሪ በል ጎንደር’ ፈረንጅ ብላ ለማለት ብዙም አይከብደውም።
የቃላት መፍቻ ፡
አዝማሪ ፡ ከቤቱ ጥቂት ግጥም መሰንቆና ድምጹን ይዞ የሚወጣ ሰዎች ሊወዱት ይችላሉ የሚለውን ዘፈን በተከፈለው መጠን ሕዝብ እተሰበሰበበት ስፍራ የሚጫወት ሰው ማለት ነው። የአዝማሪ መነሻው ኑሮን ማሸነፍ በመሆኑ በተቸረው ገንዘብ መጠን መላጣውን ጎፈሬ ፤
ልማታዊ ከያኒ ፡ ይኅኛው ዘመናዊ አዝማሪ ሊባል የሚችል ነገር ግን ደጓሚው መንግስት አልያም ልማታዊ ባለ ሀበት ነው። በፈጠራ ችሎታው የአዝማሪን ያህል እንኳን ክህሎት የሌለው ፤ የመንግስትን የልማት ውሽከታ በግጥምና ዜማ መልክ ከሽኖ ሀገሪቱ ማርና ወተት የሚፈስባት ናት ካላመናችሁ በረከት ስምዖንን ጠይቁ የሚል ነው።
ቸር እንሰንብት
ወልደ ገብራኤል – ስዊትዘርላንድ

atse minilik: The Cause of Zenawi’s Death and Its ImportSelam B...

atse minilik: The Cause of Zenawi’s Death and Its Import
Selam B...
: The Cause of Zenawi’s Death and Its Import Selam Beyene, PhD Beyene50@gmail.com May 18, 2012 Ethiopian Journalist Abebe Gellaw con...

The Cause of Zenawi’s Death and Its Import


Selam Beyene, PhD
Beyene50@gmail.com
Abebe Gelaw Doctrine Follow the tyrant wherever he attempts to buy legitimacy
May 18, 2012 Ethiopian Journalist Abebe Gellaw confronting Dictator Meles Zenawi
In the absence of a legitimate autopsy report, a death certificate or a credible official statement relating to the reason behind the hospitalization and eventual death of the former ruler of one of the most populous countries in Africa, there are compelling medical and circumstantial arguments to suggest that the episode of May 18, 2012, in which the valiant Ethiopian journalist Abebe Gellaw confronted Zenawi, might have played a major role in accelerating the demise of the dictator.
Prior to August 21, 2012, when the TPLF cadres that are currently terrorizing the country announced his death, Zenawi had not been seen in public for several weeks, and there had only been conflicting reports about his conditions or whereabouts issued by the Woyanne propaganda machinery.
Nonetheless, there were several pieces of circumstantial evidence that indicated the deteriorating condition of Zenawi’s health in the aftermath of the May18th encounter with Abebe Gellaw. Most notably, immediately after the confrontation, Zenawi reportedly failed to attend a function at the Ethiopian Embassy in Washington, D.C., that was organized to express gratitude to his followers in the Diaspora. A few weeks later, he was seen as a ghost-like creature during his meeting with Chinese officials at the G20 summit in Los Cabos, Mexico. The final confirmation of his ailment later came when he failed to attend an African Union summit in Addis Ababa in July.
While there is no conclusive medical evidence to indicate that shock can actually kill a person, there is ample literature to surmise that it can impact the cardiovascular system, and thereby exacerbate a deteriorating or compromised condition leading to death.
In the medical literature, fear and stress are known to cause substantial biochemical conflicts between the sympathetic and parasympathetic responses when a person is faced with an imminent danger, the so-called fight-or-flight phenomenon. In particular, shock, as an extreme stress reaction, ensues when the stress level is so high that the endocrine and nervous systems are unable to cope with the circumstance. People who have underlying health problems may, therefore, experience fatalities as a result of the exacerbation of these conditions.
In their book, Gleitman et al. (2004)[1] report that, in the face of extreme stress, catecholamine hormones, such as adrenaline, trigger physical reactions, including acceleration of heart and lung action, constriction of blood vessels, and shaking. For someone with cardiovascular problems, a huge release of catecholamines can lead to instant or eventual death.
Some of the above events were, of course, observed in Zenawi’s reaction to the unexpected challenge by Gellaw. In one of his weekly commentaries, Alemayehu G. Mariam poetically captured the moment as follows:
“…. For seven seconds, the mighty Zenawi zoned out into a catatonic trance like the patrons of opium dens. For a fleeting moment, he seemed almost comatose. His head was bowed, his back hunched, his chin drooped, his lips quivered and his eyes gazed vacantly at the floor just like the criminal defendant who got handed a life sentence or worse. A close-up video showed him breathing heavily, almost semi-hyperventilating. His pectoral muscles heaved spastically under his shirt. An imminent cardiac event?” [2]
For a dictator who, distrusting the people he ruled with an iron fist, had insulated himself with one of the most skilled and highly armed protective security details in the world; for a dictator who, out fear and insecurity, had never interacted or mingled with the people that he had so despised, mocked and disparaged during his two decades of tyranny; the sudden outburst of such dreaded phrases as “Meles Zenawi is a dictator!” in that world forum was a shocking experience that his frail body had not been accustomed to or able to withstand.
Although the secretive TPLF ruling party never revealed the general health condition of the dictator while he was in office, rumors did abound about his poor health resulting from a slapdash life-style, including smoking, drinking and other substance abuse – all risk factors for cardiovascular and oncological complications.
In view of the indirect association of death and shock in a compromised person, and given the poor state of Zenawi’s health prior to the event, it is not beyond the realm of possibilities to surmise that the May 18th confrontation might have contributed to his death.
If Gellaw’s heroic action had a role in the death of the dictator, then it would explain in part why the TPLF cadres kept the condition of the late dictator and the bona fide cause of his death a highly guarded secret. Manifestly, any suggestion that the event of May 18th contributed to the demise of the dictator would hearten others to follow suit and challenge the repressive rule of the TPLF. Most importantly, if there was the perspicacity that one person could contribute in a momentous way to bring down a vicious dictator, despite his ostensibly impenetrable security details, the millions of oppressed citizens would be emboldened and an organized mass uprising would be inevitable to end the monopoly enjoyed by the minority thugs on the nation’s political and military power structure and scarce resources.
The North Korean style funeral ceremony and the idolization of the deceased is also part of an overall orchestrated stratagem to demonstrate spurious invincibility and to thwart any semblance of vulnerability. The attempt to paint a larger-than-life picture of the deceased despot, and the much advertized claim that he was a respected leader in the world forum is, of course, at variance with the low esteem in which the despot was held by world leaders in private conversations. As revealed in the United States diplomatic cables leak, he was in fact a light weight in the eyes of diplomats and heads of states. Contrary to the myth propagated by his henchmen, in the opinion of German Chancellor Angela Merkel, for example, he was an “economic illiterate”, while in the assessment of George W. Bush he was nothing more than “an errand boy”.  What the TPLF cadres are doing in his death validates what Former US ambassador Donald Yamamoto observed when the dictator was alive: a “democratic deficit” example, and someone “begging to get world attention to have his ideologies acceptable.” [3]
The death of the dictator a short while after his encounter with Abebe Gellaw may serve both as a metaphor and as a template for the demise of tyranny in Ethiopia. Authoritarianism inherently is an aberration in human society, and hence a sick political system. So, as in the case of Zenawi, a major shock could unavoidably trigger the collapse of the system, as has been recently observed in the Middle East and other regions ruled by tyrants. This shock could come in the form of popular uprisings, concerted resistance by the people, organized lobbying by the Diaspora to cut the supply line of foreign aid, or internal fractures spearheaded by pro-democratic factions.
The only way out of this predicament for TPLF rulers is to recognize and respect the will of the people to live in freedom and liberty. In the short term, they should open up the political space and invite all opposition leaders for a genuine dialog to chart a framework for a democratic Ethiopia in which individual rights will be unconditionally respected, and all citizens will have equal opportunities in the pursuit of happiness and determination of the government of their choice.
If the TPLF insists in propagating the failed autocratic, ethnic-based and corrupt policies of the late dictator, then all freedom loving Ethiopians back home and in the Diaspora should rise in unity and give the aberrant system a shock from which it will never recover. It is a mathematical impossibility for a minority group to dream it would be able to perpetuate its repression over eighty million people for much longer.
It is time for the West to refrain from continuing to nurture the activities of a criminal regime and derailing the aspirations of the people to live in freedom and prosperity. In this regard, pro-democracy groups and individuals in the Diaspora have a historic role to play and influence donor nations and institutions.

atse minilik: ከኢቲቪ ምስሎች በስተጀርባየሚዲያ ትንተና - በያሬድ ጥበቡዳያሰፖራ ውስጥ በም...

atse minilik: ከኢቲቪ ምስሎች በስተጀርባ
የሚዲያ ትንተና - በያሬድ ጥበቡ
ዳያሰፖራ ውስጥ በም...
: ከኢቲቪ ምስሎች በስተጀርባ የሚዲያ ትንተና - በያሬድ ጥበቡ ዳያሰፖራ ውስጥ በምንኖረው ኢትዮጵያውያን መሃል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕይወትና ሞት እንዳከራከረን ኖሮአል ። ሰሞኑን ደግሞ የሽኝት ስርአታቸው ሌላው ድራ...

ከኢቲቪ ምስሎች በስተጀርባ
የሚዲያ ትንተና - በያሬድ ጥበቡ
ዳያሰፖራ ውስጥ በምንኖረው ኢትዮጵያውያን መሃል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕይወትና ሞት
እንዳከራከረን ኖሮአል ። ሰሞኑን ደግሞ የሽኝት ስርአታቸው ሌላው ድራማ ነው ። ዛሬ 10ኛ ቀኑን
የያዝው ይህ ድራማ ራሱን ለፖለቲካ ትንታኔ በሚያውስ መልኩ እየተተወነ ይገኛል ። የጠቅላይ
ሚኒስትሩ አስከሬን ቦሌ አየር ማርፊያ ሲደርስ፣ የኢቲቪ ካሜራ ትኩረት አቶ በረከት ላይ ስለነበረ፣
“የመለስ መንግስት ወራሸ ሰለሆኑ መሆን አለበት” የሚል ትርጉም ነበር የሰጠኝ ። የወያኔ አመራር
አባላትን ለማየት ብሞክር ከስዩም መስፍን በቀር አንዳቸውም አይታዩም ። “እየዶለቱ ቢሆን ነው
ቦሌ ያልተገኙት” ብዬ ከራሴ ጋር ተሟገትኩ ። የሃዘኑ ትርኢት ቀጠለ፣ ሆኖም የነዚህ የወያኔ ቱባ
ባለስልጣኖች ክስመት እተጋነነ ሄደ ። ወዴት ገብተው ይሆን ብለን ስንጨነቅ፣ ዕድሜ ለአውራምባ
ታይምስ፣ የመለስ ወንድም ቤት ሐዘን መቀመጣቸውንና፣ አቦይ ስብሃት “መለሰ ብቻውን አይደለም
የሞተው፣ ወያኔን ቀብሮ እንጂ ነው!” እያሉ ማንባታቸውንና በጠባብ ብሄርተኝነትና በሙስና
እየተከሰሱ ከድርጅቱ የተባረሩትንና የተሰናበቱትን ሁሉ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ሰማን ። ከዚህ
ዜና ብስረት በሁዋላ ደግሞ የሚከተሉተን የሚዲያ ትዝብቶች ለማድረግ ቻልን ።
በሚቀርቡት የመለስ ገድሎች ሁሉ፣ ተሓህት፣ ህወሓት፣ ወያኔ የሚባሉ ድርጅቶች ውስጥ የታገሉና
የመሩ መሆናቸውን በሚያስረሳ መልኩ፣ መለስ ከኢህአዴግና ኢትዮጵያ ጋር ብቻ ተዳብለው
እንዲታዩ ተደረገ ። ከጎንደርና ወሎ ገበሬዎች ጋር ሲወያዩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ይበልጥ አመዘኑ
። ስለ ስውዬው ማንነትም ሰብዕናቸውን የሚመሰክሩት እነ ስብሃትና አባይ መሆናቸው ቀርቶ እነ
ሬድዋንና ኩማ ሆኑ ። የወያኔ መሪዎች ወይ አኩርፈው አንተባበርም ብለዋል፣ ወይም ኢቲቪ
መንደር ድርሽ እንዳይሉ ታግደዋል ። መለስ የብሄረሰቦችን እስር ዘለው ለኢትዮጵያ ሴቶችና
ወጣቶች ህይወታቸውን የሰጡ ታጋይ ሆነው ቀረቡ ። በዚህ ሁሉ መሃል የወያኔ አንጋፋዎች ምስል
ተዳፍኗል ።
እሮብ በማለዳ በ12 ሰአት ዜና ላይ ቀዳሚዎቹ ሶስት ዜናዎች፣ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ
የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ቢሾፍቱ በሚገኙ የአየር ሐይል አባላት፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ
ሰራተኞች ለጠቅላይ ሚኒሰትሩ ራዕይ ቀጣይነትና ለህገ መንግስቱ ያላቸውን ታማኝነት
መግለጻቸውን የሚያበሰር ነበር ። ጥያቄው ለምን ይህ አስፈለገ የሚል ነው ። ለህገመንግስቱ
ያላቸውን ታማኝነት ይዞ ምን ለማድረግ? አሰላለፉ ግልፅ ይመስላል ። የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ራዕይ
እናስፈጽማለን ብለው በአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ዙሪያ በበረከት አስተባባሪነት ሚዲያውን ይዘው
በቆሙትና፣ ኒቆዲሞስ መኖሪያ ቤት ዙሪያ በተኮለኮሉት የወያኔ ጎምቱዎች ። ይህንኑ ጥርጣሬ
የሚያጠናክሩ ትርኢቶችም በዛሬው ዕለትም ቀጥለዋል ።
ሐሙስ ምሽት የአዲስ አበባ ሴቶች የጧፍ ማብራት ትዕይንት በመስቀል አደባባይ ነበር ።
መድረኩ ላይ ግዙፍ ከሆነው የመለስ ፎቶግራፍ ስር፣ በህይወታችው ሳሉ ያልተደመጡትና
ስንናፍቀው የኖርነው “በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ…” የሚል ጥቅስ ይታያል ። ሴቶች ሲያነቡ፣
ሲገጥሙ ከቆዩ በሗላ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታው ብቅ ብለው፣ የጠቅላይ
ሚኒስትራችንን ራዕይ ከመተግበረና አንድነታቸንን ከመጠበቅ የሚቀናቀኑንን እናወግዛለን ይሁን
እናወድማለን የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አደረጉ ። ለመንግስት የውጪ ተቃዋሚዎች
ያልተሰነዘረ መሆኑን በሚያሳበቅ መልኩ ነው ያን ያሉት ። ለምን? በመስቀል አደባባዩ ሰልፍማሳረጊያ ላይ አስተባባሪው “የፌዴራል ፖሊስ የሙዚቃ ባንድ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርን ማርሸ
አሰምቶ ሰልፉ ይጠናቀቃል” ቢሉም፣ አስቀድሞና መዝሙሩን ተከትሎ የቀረበው ግን ኢህዴን
ውስጥ ሳለን ህላዌ ዮሴፍ ያቀነባበረው፡
ስንቶች ተኮላሽተው ከአረንቛ ዘቀጡ
ሰንቶች ተደናብረው ከጎዳና ወጡ፤
ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረከክነው
ነግ እልፍ እንሆናለን ታሪክ ምስክር ነው የሚለው መዝሙር ነበር። ለምን?
የመዝሙር ነገር ካነሳን አይቀር፣ ህወሓት ስለ መስዋእትነት ብዙ የዘመረ ድርጅት መሆኑን
እናውቃለን ። እኔ ራሴ እንኳ የምዘምረው “ጀጋኑ ብጾት” አንዱ ነው ። ሆኖም በትግራይ ቲቪ
ፕሮግራሞች እንኳ እነዚያ መዝሙሮች አይደመጡም ። የአማርኛ ዋሸንትም በእኩል ደምቆ
ይቀርባል ።
ምናልባት ይህ ሁሉ በወያኔ መሪዎች ትብብር፣ የመለስን የመጨረሻ ስንብት እድሜ ልኩን ሲዋጋ
የኖረውን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ተቀበሎ እንዲሄድ የሚደረግ፣ ይዞት ከቆየው ስልጣን ጋር
የሚመጣጠን የፖለቲካ ሽግግር ሊሆን ይችላል ። ይህ ቢሆን እሰዬው ነው ። ትልቅነት ነው ።
ምናልባትም የህወሓት አመራር አባል የሆኑት አቶ አባይ ፀሃዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በኢቲቪ
መታየታቸው ተፋጠው የቆዩት ቡደኖች መሃል ዕርቀ ሰላም መውረዱን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል ።
ወይም ቀድሞ ወያኔ ውስጥ በነበረው ክፍፍል እንዳደረጉት ሁሉ፣ ተሸናፊውን ወገን የማሽተት
ክህሎት ያላቸው ሰው ሰልፍ ማስተካከላቸውም ሊሆን ይችላል ። ሆኖም ከኒቆዲሞስ ግቢ ድንኳን
የሚሰማው ልቅሶ ግን ያንን አይጠቁመንም ። እንዲያውም ፍርሃትህ ምንድን ነው ብትሉኝ፣ እነ
በረከት “ሁሉን ነገር በቁጥጥር ስር አድርገናል ሽግግሩ ከቀብር በሗላ ቀስ ብሎ ይደርሳል” ብለው
በፈጠሩት የሚዲያ የበላይነት ሲዝናኑ፣ “ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረስናቸው” የሚል አምባገነን
እንዳይቀድማቸው ነው ።