Saturday, September 22, 2012

የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ


የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ
(ከእየሩሳሌም አርአያ)
በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎን
ተሰልፈዋል።አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ»ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት
አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል። አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም
ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል።
ሕወሀትን ከጀርባ በማሽከርከር የሚታወቁት ስብሀት ነጋ ለቀጣዩ ፍልሚያ ሀይል እያደራጁ ነው። ለበረከት ያላቸው ጥላቻ-ንቀት ጭምር
የተላበሰ ነው። አዜብን ለመበቀል ግዜው አሁን እንደሆነ አረጋግጠዋል።የስብሀትና አዜብ ቁርሾ የተጠነሰሰው ከአምስት አመት በፊት ነበር።
በወቅቱ የተወሰኑ የህውሀት ማ/ኮሚቴ አመራሮችን የሰበሰቡት አዜብ«ስብሀት ከኤፈርት ሃላፊነቱ መነሳት አለበት » ይላሉ። ትእዛዙን
የተቀበሉት እነቴዎድሮስ ሀጎስ መልእክቱን ለሽማግሌው ያደርስሉ። ስብሀትም በቁጣ«ጉአል ጎላ ክትቅመጠሉ ድያ?ሞይተ ድየ ብደወይ?»
ማለትም «የጎላ ልጅ ልትቀመጥበት ነው? ሞቼ ነው በቁሜ?» ነበር ያሉት። «የሚስቱን ትእዛዝ ሳያወላዳ ተግባራዊ ያደርጋል» ሲሉ
በገረሜታ የሚገልጹአቸው መለስ በወቅቱ በአዜብ የቀረበውን ስብሀት ነጋን የማስነሳት ሀሳብ ከመተግበር ወደሁዋላ አላሉም።
«ፉከራ»ብቻ ሆነው የቀሩት ሽማግሌው ከኤፈርት፣በሁዋላም ከፓርቲው አመራር እንዲወጡ በማድረግ አዜብ የበላይነታቸውን አሳዩ።
ስብሀት ነጋ ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ የባልና ሚስቱን ስም እየጠቀሱ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልቦዘኑም። አዜብ ከሽማግሌው
አልፈው «ታማኝ» የተባሉ ጄኔራሎችን ሳይቀር ከሀላፊነት እንዲወገዱ አድርገዋል። ከነዚህም ጄ/ል ወዲ አሸብር እና ጄ/ል ዮሀንስ(ጆኒ)
ሲጠቀሱ፣ የዛሬ አምስት አመት ለጄ/ል ሳሞራ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ወዲ አሽብር ለአንድ አመት የቁም እስረኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል።
በወቅቱ አስገራሚ ሀይለ ቃል እስከመለዋወጥና እስከ መዘላለፍ ደርሰዋል። ከአመት በሁዋላ ወደ ስራቸው ቢመለሱም ብዙ አልቆዩም።
ሁለቱን ጄኔራሎች ጨምሮ ሰባት ከፍተኛ የቀድሞ የህውሀት አባላት ጄኔራሎች እንዲባረሩ ተደረገ።
በሌላም በኩል የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሀላፊ ወ/ስላሴ ለረጅም ወራት ታግዶ ከቆየ በሁዋላ ወደቦታው እንዲመለስ ተደረገ። የታገደው
የስብሀት ነጋ ደጋፊ ነው ተብሎ ነበር። ብዙዎቹ በዚህና በአንጃ ደጋፊነት እየተፈረጁ ሲያበቁ
እግዱ ተነስቶላቸው የሚመለሱበት፣ በሁዋላም ጠቅልለው የሚወጡበት አካሄድ ለፓርቲው ቅርብ ለሆኑ አባላት ጭምር ግራ ያጋባ
እንቆቅልሽ እንደነበር ይጠቁማሉ። አዜብ ብዙ ርቀት ለመጝዋዝ የጣሩት የስብሀትን አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ነገርግን ያሰቡት
እቅድ ሙሉ ለሙሉ ሳይሳካ የአሁኑ ጠንካራ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል።ስብሀት ከፓርቲው ሲለቁ «የእኔ» የሚሉአቸውን ሰዎች ቁልፍ ቁልፍ
ቦታ እንዲጨብጡ አድርገዋል። የህወሀት ማ/ኮሚቴ ውስጥ የስብሀት ሁለት እህቶች አሉ።የፌደራል ደህንነት ቢሮ የሚመራው በጸጋዬ
በርሄ (ሀለቃ)ሲሆን፣ የጸጋዬ ባለቤት ቅዱሳን ነጋ፣ የስብሀት ነጋ ታናሽ እህት ናት። ስብሀት በአዜብና በረከት ላይ ለከፈቱት የውስጥ ዘመቻ
ከጎን ካሰለፉት አንዱ አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።አርከበ ከአዜብ በተደጋጋሚ የደረሰባቸው ጥቃት ለመጠጥ ሱሰኝነትና ብስጭት
ዳርጎአችው ቆይቶአል። የእግዜር ሰላምታ መለዋወጥ ካቆሙ ክርመዋል። ስብሀት አርከበን ከጎን ሲያሰልፉ ሌላም አላማ አንግበው ነው።
ይኽውም የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ይረከባል ተብሎ የሚጠበቀው አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ታናሽ እህት ንግስቲ ገ/ክርስቶስ
የአርከበ ባለቤት ናት። ብርሀነ የነበረው ወዳጅነትና ታማኝነት ከመለስ ጋር አብሮ ምእራፉ ተዘግቶአል።
የፍጥጫው አንዱ አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት ይገኝበታል። በአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘር ተገቢ ጥያቄ አለ።«የጦር
ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠ/ሚ/ር በሌለበት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?» የሚል ሲሆን፣ ለዚህ ደግሞ ከመንግስት አፈ
ቀላጤዎች የሚስጠው ምላሽ ሹመቱ ቀደም ሲል በአቶ መለስ የጸደቀ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ይህ ግን ውሀ የማይቕጥር ነው ሲሉ የመከላከያ ምንጮች ማስተባበያውን ያጣጥላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ከተሾሙት ጄነራሎች
መካከል በአንጃነት ተፈርጀው የቆዩ፣ በመለስ በጥሩ አይን የማይታዩና ለረጅም አመት ለእስር የተዳረጉ እንዳሉም ይገልጻሉ። ሀቁ ይህ ሆኖ
ሳለ መለስ እነዚህን ይሾማሉ ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ ነው ሲሉ ያክላሉ። እርከን ጠብቀው የተሾሙ እንዳሉም ይጠቁማሉ።
ቢሆንም ግን ህገ መንግስቱን ያልተከተለና ተገቢውን መንገድ የልተከናወነ ሹመት እንደሆነ አልሽሽጉም።የብ/ጄኔራል ሹመት ከሰጣቸው አንዱ ኮ/ል አታክልቲ በርሄ ይገኝበታል። ከዚህም ቀደም ባቀረብኩት መጣጥፌ «መለስ ካጠፋቸው
የፓርቲው አባላት»ይኸው ኮ/ል እንደሚገኝበት ጠቅሼ ነበር። በተሰነይ ግንባር ከፍተኛ ጀግንነት የፈጸመው ኮ/ል አታክልቲ ከጦርነቱ
በሁዋላ መለስን ሀይለ-ቃል በመናገሩና በማውገዙ እስር ቤት ወርዶ ለረጅም አመት ድምጹ ጠፍቶ ቆይቶአል።በ 2000 አ.ም ከእስር ተለቆ
እንደቆየና በቅርቡ የብ/ጀነራልነት ሹመት አግኝቶ በተሻለ ሀላፊነት ላይ መቀመጡ ታውቆአል።
ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ
ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል በነመለስ ተገፍተው ሜዳ ተጥለዋል። ጀነራል አስካለ
ይህን ሹመት ማግኘትዋ አስገራሚ የሚያደርገው ነጥብ አለ። የቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ጀ/ል አበበ (ጆቤ)ባለቤት ስትሆን ፣ጆቤን ጨምሮ
የጦር አዛዦችና ከፍተወታደራዊ መኮንኖች እንዲባረሩ የተደረገው በመለስ ህገወጥ ውሳኔና ፊርማ እንደነበር ምንጮቹ ያስታውሳሉ።
የጄ/ል አስካለ ባለቤት- እህት ከተባረሩትና ከተንገላቱት መካከል ይጠቀሳሉ። የህወሀት ፖሊት ቢሮ አመራር የነበሩት አለምሰገድ ገ/አምላክ
ባለቤት ሀመልማል ተ/ሀይማኖት ስትሆን ጋዜጠኛ ሀመልማል የጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት እህት ናት። ከራዲዮ ፋና እና ከፓርቲው
እንድትባረር የተደረገው ባለቤትዋ ከመለስ ጋር በመለያየታቸው እንዲሁም ወንድሟ በመባረሩ ነበር።
በሌላም በኩል በአንጃ ደጋፊነት ተፈርጀው ከቆዩትና በመለስ በጥሩ አይን ከማይታዩት መካከል ፍስሀ በየነ፣አብርሀም አረጋይ፣የማነ ሙሉ፣
ማአሹ ሀጎስ፣ግኡሽ ጽጌና ገብሩ ገ/ሚካኤል የብ/ጀነራልነት ሹመት ካገኙት ይጠቀሳሉ።አብዛኞቹ በሎጀስቲክ መምሪያ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው።
ከዚሁሉ ጀርባ እጃቸውን አርዝመው የሹመቱን ሚና የከወኑት ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ሲታወቅ በሁለቱ ባላንጣዎች ላይ (አዜብና
በረከት)የጥፋት ሴራ ማዘጋጀቱን ገፍተውበታል።
በደብረ ዘይት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሹም ጄ/ል ወዲ ዳኘው በሚመራው መንግስታዊ ተቛም አቶ ቢተው በላይ ስራ መጀመራቸው
ታውቛል። በመለስ ታግደውና ታስረው የነበሩት ቢተው ቁልፍ በሆነ ቢሮ መመደባቸው ሚስጥሩ ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ተጠቁሟል።
የሜ/ጄነራልነት ሹመት ካገኙት አንዱ መሀሪ ዘውዴ ሲጠቀሱ የፓርቲው አባላት «ወዲ ዘውዴ» እያሉ የሚጠሩአቸው እኚህ ጄ/ል
ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የሳሞራ ቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሎአል።
በመጨረሻም በመከላከያ ቢሮ የምስራቅ እዝ ዋና እዛዥ ሆነው የቆዩት ጄ/ል ባጫ ደበሌ ባለፈው አመት በእረፍት ሰበብ ከሀላፊነት እርቀው
እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ በዛው እንደተባረሩ ተገልጾላቸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እንዳሉ ሲታወቅ የት ከተማ እንዳሉና ለምን
እንደመጡ ማወቅ አልተቻልም።

Teddy Afro New Wedding Song - Yemushiraye Enat

Emperor Menelik's Voice ][ የአጤ ምኒሊክ ድምጥ

ትንሽ ድጋፍ ለአቶ ሀይለማርያም – ደረጀ ሀብተወልድ-ሆላንድ


ደረጀ ሀብተወልድ – ሆላንድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከአቶ መለስ የተረከቧት ኢትዮጵያ፤ እርሳቸው  ቃለ-ምሕላ ከፈጸሙ በሁዋላ እንዳሉት ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ሩብ ጉዳይ የቀራት ኢትዮጵያ ሳትሆን፤ በውድቀት አፋፍ እያጣጣረች የምትገኝ ኢትዮጵያ ናት።
በፖለቲካው መስክ በወንድማማቾቹ ኢትዮጵያውያን መካከል የቆመው የልዩነት አጥር እንደ ሰናዖር ግንብ ቋንቋችንን ደበላልቆት መደማመጥ ባልቻልንበት ሁኔታ ነው አቶ መለስ ያለፉት።
በኢኮኖሚው መስክ ጥቂት ሰማይ የነኩ ከበርቴዎች በተፈጠሩበትና ብዙ ድሆች እንደ አሸን በፈሉበት ጊዜ ነው አቶ መለስ የሞቱት።
በማህበራዊው ዘርፍ የፍትሕ ሥርዓቱ የአንድ ፓርቲ መሳሪያ ሆኖ ተቃዋሚዎችን ማጥቂያ በሆነበትና ከኢትዮጵያ ምድር ጨርሶ ፍትሕ በጠፋበት፤ በትምህርቱ መስክ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃን ሥራ አጥተው ድንጋይ በማንጠፍ ሥራ በተሰማሩበት ወቅት ነው አቶ መለስ እስከወዲያኛው ያሸለቡት። በሌሎችም ዘርፎች አቶ ሀይለማርያም የተረከቧት ኢትዮጵያ የተዘፈቀችበት ችግር፤ ከዚህ ቢብስ እንጂ የሚሻል አይደለም።
ይህ ማለት አቶ ሀይለማርያም በብዙ ዘርፎች ብዙ ፈተናዎች ተጋርጠውባቸዋል ማለት ነው።አዎ! በእውነት እንናገር ካልን፤በአቶ ሀይለማርያም ፊት፦ እንደ ጎልያድ የገዘፉ በርካታ ችግሮች ቆመውባቸዋል።ይሁንና የድሉን ምስጢር አውቀው በትክክለኛው መስመር ከሄዱ፤ እነዚህን <ጎልያዶች>(ችግሮች) ሊያሰኝፉዋቸው ይችላሉ።
ጎልያድን የማሸነፊያው ዋነኛ የድል ምሥጢር ደግሞ፤ ራስን ሆኖ ወደ ፍልሚያው መግባት ነው። መጽሐፉን ያስታውሱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!
ዳዊት ጎልያድን እንዲገጥም ሲላክ የንጉሥ ሳዖልን ካባና ሰይፍ ነበር ያለበሱት። ሆኖም ልኩ አልሆነም።ካባውም ሰፋው፣ሰይፉም መሬት ለመሬት ተጎተተ። በዚያ መልኩ ወደ ጎልያድ ቢሄድ ኖሮ የሚጠብቀው ዕድል ሽንፈት ነበር።ዳዊት ግን -የንጉሥ ካባና ሰይፍ ስለሆነ ብቻ ፤ልኩ ያልሆነን ትጥቅ ታጥቆ ወደ ፍልሚያው መግባት አልፈለገም።ለዚህም ነው የሳዖልን ካባና ሰይፍ አውልቆ በመጣል ፦”ወንጭፌን አምጡልኝ!”ያለው።እናም ወንጭፉን አነገተ፤ጠጠር በኮሮጆው ጨመረ። በግ ጠባቂው ዳዊት ራሱን ሆነ። የሚያውቀውንና የተለማመደውን ወንጭፍና ኮሮጆ አንግቶ ጎልያድን ገጠመ።አሸነፈም።
ይህን ነገር ያነሳሁት አቶ ሀይለማርያም  ከሹመታቸው በሁዋላ ባደረጉት ንግግር፤ በአቶ መለስ መስመር ከመሄድ ውጪ ሌላ መንገድ እንደሌለ በተደጋጋሚ በአጽንኦት ሲገልጹ በመስማቴ ነው።የአቶ መለስ መስመር ባለፉት 21 ዓመታት የ ኢትዮጵያን ችግሮች(ጎልያዶች) አላሸነፈም። እንዲያውም ይበልጥ አግዝፏቸዋል። በዚህ ተሸናፊ መስመር ለመቀጠል መወሰን፤ በሳዖል ካባና ሰይፍ ጎልያድን ለመግጠም እንደመዘጋጀት ነው። የዚህ ውጤት ደግሞ ያለ ጥርጥር ሽንፈት እንደሚሆን ለመተንበይ ነቢይነት ቅባት አይጠይቅም።
ስለዚህ አቶ ሀይለማርያም ሆይ! በአቶ መለስ ካፖርት ውስጥ ለመግባት አይሞክሩ። የራስዎን ጫማ ይጫሙ። ምንም <ኢህአዴግ> የሚባል የጋራ ማዕቀፍ ቢኖራችሁም፤እርስዎ ሀይለማርያም እንጂ መለስን አይደሉም።በዚህ ምድር ላይ እርስዎን የመሰለ ሰው ከዚህ በፊት አልተፈጠረም፤ከዚህ በሁዋላም አይኖርም! ይህም የአምላክ ልዩ ሥራ ነው። አምላክ የሰጠዎትን ይህን ውብ የራስን ማንነት፤ሌላን ለመምሰል በመታተር አያጥፉት።

“እንግዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሬ ማነው? ኃይለማሪያም አይደለምን…!?”



ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (ወይ ጊዜ ድሮ ድሮ አረ የምን ድሮ ከሶስት እና ከአራት ወራት በፊት ብዙዎች መለስን ሲግለፁዋቸው ገዳዩ እና አምባገነኑ እያሉ ነበር። በእርግጥ እኔ እንደዛ ብያቸው አላውቅም። እኔ መለስን ገዳይ ካልኳቸው ግፋ ቢል በሳቅ ይገሉኛል ለማለት ይሆናል እንጂ በግልፅ ይፋ በሆኑ ሪፖርቶች ላይ እንደሚታየው በትንሹ የባድመውን የተሳሳተ ጦርነት ሳይጨምር የሶስት ሺህ ሰዎች ደም በእጃቸው ላይ እያለ ጨክኜ ገዳይ ብያቸው አላውቅም። (በሌላ ቅንፍ ቡቡ እኮ ነኝ!)) የሆነው ሆኖ ጊዜ ደጉ “ገዳይ” ሲባሉ የነበሩትን ሰውዬ “ሟች” እያልን እንድንጠራቸው አድርጎናል። ሞት አይቀርም ከቶ ምንም ታክቱ ምን ቢከተክቱ… ብለን በአዲስ መስመር እንቀጥል።
ሟቹ ጠቅላ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ… በህይወት ዘመናቸው 21 ዓመታት እንዲሁም በአስከሬናቸው ለሶስት ወራት አስተዳድረውን ሲያበቁ አሁን ደግሞ መንፈሳቸው በአዲሱ ሰውዬ ላይ ሆኖ ሊመራን የተዘጋጀ ይመስላል። ትላንት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ባደረጉት ንግግር ለትህትና ይሁን የምራቸውን ይሁን እናጃ እንጂ “የኔ ስራ እንደ መለስ ዜናዊ ሆኖ መተወን ነው” አይነት ንግግር ሲናገሩ ሰምተናቸዋል። ይህንን ንግግራቸውን የሰማው የኢሳቱ ደረጄ ሀብተወልድ አንጀት ላይ ጠብ የሚል የአዋቂ ሰው ምክር መክሯቸዋል። ምን አላቸው….?
“ዳዊት ጎልያድን እንዲገጥም ሲላክ የንጉሥ ሳዖልን ካባና ሰይፍ ነበር ያለበሱት።ሆኖም ልኩ አልሆነም።ካባውም ሰፋው፣ሰይፉም መሬት ለመሬት ተጎተተ። በዚያመልኩ ወደ ጎልያድ ቢሄድ ኖሮ የሚጠብቀው ዕድል ሽንፈት ነበር።ዳዊት ግን-የንጉሥ ካባና ሰይፍ ስለሆነ ብቻ ፤ልኩ ያልሆነን ትጥቅ ታጥቆ ወደ ፍልሚያውመግባት አልፈለገም።ለዚህም ነው የሳዖልን ካባና ሰይፍ አውልቆ በመጣልወንጭፌን አምጡልኝ!”ያለው።እናም ወንጭፉን አነገተ፤ጠጠር በኮሮጆውጨመረ። በግ ጠባቂው ዳዊት ራሱን ሆነ። የሚያውቀውንና የተለማመደውንወንጭፍና ኮሮጆ አንግቶ ጎልያድን ገጠመ።አሸነፈም።”
ደሬ እንዳላቸው አቶ ሃይሌ ከመለስ ካባ እና ሰይፍ ይልቅ የራሳቸውን ወንጭፍ ይዘው ከፊታቸው የሚጠብቋቸውን በርካታ ጎልያዶች ቢሞክሯቸው ይሻላል።
አቶ ኃይለማሪያም ከፊት ለፊታቸው ብዙ ጎልያዶች አሉ። እርሳቸው እና ፓርቲያቸው እንደሚለው ድህነት አንዱ ጎልያድ ነው። የፍትህ ማጣት እንዴት ያለ ጎልያድ እንደሆነ ለማወቅ አንድ ጊዜ ቃሊቲ ወይም ቂሊጦ ኧረ ምን ሩቅ አስኬዳቸው እዝችው ማዕከላዊ ሄድ ብለው ማየት ይበቃቸዋል። ዛሬ በሀገራችን የማንበብ እና የመፃፍ ነፃነት በህገ መንግስቱ ላይ ብቻ ነው ያለው። ይሄም ትልቅ ጎልያድ ነው። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው የህገ መንግስት ቃል መከበሩን ለማረጋገጥም ወንጭፋቸውን ማሰናዳት አለባቸው። ሙስናም ቢሆን ዋዛ የሚባል ጎልያድ አይደለም።
ዘርዝረን የማንጨርሳቸው በርካታ ጎልያዶች አሉብን እነዚህን ለመፋለም የአቅማቸውን ወንጭፍ ካላዘጋጁ በስተቀር የአቶ መለስን ካባ ለብሰው በአቶ መለስ ሰይፍ ተፋልመው አይችሉትም። ራስዎን መሆን አለብዎ… “ራስን መሆን” የሚል መፅሀፍ ፒያሳ ወይም አራት ሎ አካባቢ አይጠፋም። ከጠፋ ከጠፋ ብሄራዊ እነ ጃፋር ዘንድ መጠየቅ ነው። እንጂ፤ መለስን ለመሆን መሞከር አያዋጣም። እኛም እንጠይቃለን… “እንግዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሬ ማነው ኃይለማሪያም አይደለምን!?”