Wednesday, October 24, 2012

ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ

Wednesday, October 24, 2012

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ
ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ  በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ በማትኮር፤ አደጋውን ለመቀነስ፤ ቅድመ ጥንቃቄ ስለማድረግ፤ ህክምናና ምርምር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በተረጋገጠው መሰረት በአብላጫ በዓለም ላይ ሴቶችን በማጥቃት ላይ ያለው የጡት ካንሰር ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች በበሽታው በየዓመቱ ሲለከፉ ከነዚህም መሃል በሢ የሚቆጠሩት ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ኮመን ፎር ዘ ኪዩር የተባለው የአሜሪካ ድርጅት እንደአስቀመጠው በአሜሪካን የሚገኙ አብላጫዎቹ አፍሮ አሜሪካውያን መሃል ሁለተኛው ገዳይ በሽታ የጡት ካንሰር እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡ በአፍሪካ ስለዚህ ገዳይ በሽታ የታማሚ መጠንና ስለሚያደርሰውም አደጋ አያም ስለሚሰጠው ትኩረትና ህክምና በትክክል እንዲህ ነው ለማለት ዘገባም ሆነ መግለጫ ስለሌለ ብዙ ማለት ያስቸግራል፡፡ በአፍሪካ የበሽታው ሁኔታ ሊታወቅ የሚችለው ታማሚው በበሽታው ተይዞ ለህክምና ወይም ለመመርመር ወደ ጤና ጣቢያ አለያም ህክምና ማእከል ሲሄድ ብቻ ነው፡፡ አብላጫው የሴቶች ቁጥር በሚኖርበት የገጠሩ ክፍል ስለበሽታው ሁኔታ መዝግቦ መያዝና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡ በብዙም የተለመደ ወይም ሁኔታ የተፈጠረለትም አይደለም፡፡ ስለበሽታው  ሁኔታ ክትትልና ዘገባም ሆነ ስለበሽተኞቹ ሁኔታ ጥናት ማካሄድን ከምር ይዘው በማስኬድ ላይ የሚገኙት ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት ናቸው፡፡
የጡት ካንሰርና የሕክምና አገልግሎት በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የጤና ባለስላጣናት በሚያወጡት ሪፖርት ላይ የጡት ካንሰር ቅድሚያ የሚሰጠው በሽታ ሆኖ አይታይም፡፡ በሃገሪቱ ካለው የጤና ላዕላይ መዋቅር ደካማና ያልተመጣጠነ መሆን፤ የጤና ማእከል እጥረት፤ለጤና ካለው ደካማ ትኩረት አኳያ፤ ይህ አዲስ ነገር ሆኖ ባይታይም ይቅር የሚባል ጉዳይ ግን ጨርሶ ሊሆን አይችልም፡ ፡ በኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ላይ የሚታየው ስታትስቲክስ የጨለመና ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው፡፡
እንደ 2006ቱ የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ዘገባ መሰረት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 77 ሚሊዮን ተብሎ ተገምቷል፡፡ ይህን ታላቅ የሕዝብ መጠን የህክምና አገልግሎት ለመስጠትም 1,936 ሃኪሞች አሉ (1 ዶክተር ለ 39,772 ሰዎች)፥ 93 የጥርስ ሀኪሞች (1 ለ 828,000 ሰዎች)፥  15,544 ነርሶችና የልምድ አዋላጆች (1 ለ 4,985 ሰዎች)፥ 1,343 ፋርማሲስቶች (1 ለ 57,334 ሰዎች)፥ እና 18,652 የጤና ባለሙያዎች (1 ለ 4,128 ሰዎች) አሉ::  የሃገር ውስጥ ጠቀሜታ በመቶ ሲሰላ ለጤና ይሚወጣው 5.9 በመቶ ነው፡፡ አጠቃላይ የመንግስት የገንዘብ ፍሰት ድርሻን በጤና ላይ በተመለከተም 58.4 በመቶ ሲሆን ተራፊውን 41.6ቱን የሚሸፍኑት የግል ባለሃብቶችና  ድርጂቶች ናቸው፡፡ የህክምና መኝታ አልጋዎች መጠን ለ10,000 ሰዎች ከ25 አላጋ ያነሰ ነው፡፡ የሕክምና የመንግስት ወጭ በግለ ሰብ ሲተመን ከ3 የአሜሪካ ብርን አያልፍም፡፡የዓለም የጤና ድርጅት አነስተኛው መጠን ለ 100,000 ሰዎች 25 ዶክተሮች ያስፈለጋሉ ይላል፡፡ በማርች 2007 ዓም፤ ሙት ወቃሽ አያድርገንና፤ ያለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስለ ሃኪሞች ሲናገሩ እንዳሉት፤ ‹‹በኢትዮጵያ ዶክተሮች አያስፈልጉንም……. ሃኪሞቹ ወደያሻቸው ቦታ ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ በፍጹም የተለያ አመለካከት ሊደርግላቸው አይችልም›› በማለታቸው በኮንፍራንሱ ላይ የነበሩትን ሁሉ ያስደነገጠና ያሳዘነ አባባል ነበር፡፡ እንደ ፎሪን ፖሊሲ መጽሔት አባባል፤ ‹‹በአፍሪካ ሁለተኛዋ ታላቅ የሕዝብ ቁጥር ባላት ኢትዮጵያ (80 ሚሊዮን) ካሉት ሃኪሞች የበለጠ ቁጥር በቺካጎ የሚሰሩት የኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ቁጥር የበለጠ ነው፡፡”
በ ኦክቶበር 2010 በአምስት ተከታታይ ጽሁፍ ‹‹የኢትዮጵያ እናቶች›› በሚለው ዘጋቢ የጋዜጣ ጽሁፏ ሃና ኢንግበር ዊን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ስላለው የአፍሪካን የውልደትና የጤና አሳሳቢና አስደንጋጭ ጉዳይ ስዕላዊ ድርሰቷን አቅርባ ነበር፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ የወላጆችን የጤና ሁኔታና የወሊድ ስርአትን በተመለከተ ተሃድሶ የሚያስፈለግው ጉዳይ ነው›› ብላ ዊን ጽፋ ነበር፡፡ ከስድስት በመቶ የሚያንሱት ኢትዮጵያዊያት እናቶች በወሊዳቸው ወቅት የህክምና እርዳታ እንደሚያገኙ የ2005ቱ የጤና ጥናት ያሳያል፡፡ በወሊድ የሚሞቱት ቁጥር በዓለም እጅጉን አስከፊ የሆነ ነው፡፡ በጥናቱ መሰረት ከ 100,000 ወላዶች መሃል 673 እናቶች በወሊድ ሰበብ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡››
በዚህ አስደንጋጭ ዘገባና የጡት ካንሰርን ሁኔታ ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ  የግልም ሆነ መንግስታዊ ተቋም በሌለበት፤ ይህ የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ፤ መወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ፤ ሰለአጠቃላይ ሁኔታው እንዲህ ነው ብሎ ማስቀመጡ አስቸጋሪ ነው፡፡ ዘመን አመጣሹን ቅድመ ምርመራ ለማድረግ የሚያስችለው “ማሞግራም” የተባለው መሳርያ በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጨርሶ አይታወቅም በእርግጠኛነትም ልመርመር ለምትል እናትም ዋጋው የሚደፈር አይደለም፡፡ በሽታው ስር ሰዶ የከፋ ደረጃ በሚደርስበትም ጊዜ ቢሆን ኢትዮጵያዊያን እናቶች አማራጭና አቅማቸው የሚፈቅድላቸው የባሕል መድሃኒትና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ኪሞና ራዲዩቴራፒ ከጥቂት የተረፋቸውና ያላቸው ወደ ውጪ ሄደው ለመታከም ከታደሉት ባሻገር ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያት እናቶች በሃሳብ ደረጃ እንኳ የማይታወቅ ነው፡፡
ስለካንሰር ኤች አይ ቪ /ኤይድስ የሚስጥራዊነትና የዝምታ ባሕል
ስለአንዳንድ በሽታዎች ሚስጥር ማድረግና ዝምታን መምረጥ በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራው የሚገኙ እትዮጵያዊያን መሃል እጅጉን የሚያስገርምና የሚያሳዝን ባሕል አለን፡፡ ሁለቱ የማይደፈሩትና በድብቅ የሚያዙት በሽታዎች ደግሞ ኤድስና ካነሰር ናቸው:: የዚህም ዝምታና ሚስጥራዊነቱ ህጉ እስከ እለተ ሞት ድረስና ከዚያም በኋላ ሚስጥረነቱን ማክበር ነው፡፡ ይህንንም አሳዛኝና አሳፋሪ የሚስጥራዊነት ባህል በቅርቡ ለህልፈት በተዳረጉት በመለስ ዜናዊ ሁኔታ አይተነዋል፡፡ የመለስ ሕመምና የሞቱ መንስኤ ምንነትና ሰበቡ ከፍተኛ ጥብቅ ሃገራዊ ሚስጥር ሆኖ ይኖራል፡፡ በስፋት እንደሚነገረውና እንደሚታመነውም የመለስ ሞት ሰበቡ የአንጎል ካንሰር ነው፡፡ የኒው ዮርክ ታይምስ የውጪ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ እንደዘገበው ‹‹መለስ በጉበት ካንሰር ይሰቃይ ነበር፡፡›› ጋዜጠኞችን ለመጠበቅ የተሰለፈው ድርጅት  (ዘ ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስት) እንደዘገበው መለስ በብራስልስ ሆስፒታል በጉበት ነቀርሳ ሳቢያ ሞቷል ብልዎል፡፡ በአጠቃላይ ካንሰር በተለይም የጡት ካንሰር በብዙ ኢትዮጵያዊያን በተማሩትም መሃልና ውጪውን ዓለምም ባዩት መሃልም ቢሆን የማይነገር የማይነሳ የሚደበቅ ሚስጥር ነው፡፡
ይህ የሚስጥራዊነትና የዝምታ ባህል ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ ለምሳሌ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በዲያስፖራው ለሞት የተዳረጉበት መነሾ አስቀድመው ስለበሽታው ምርመራን ባለማደረጋቸውና የፍርሃታቸውም ምክንያት የምርመራው ውጤት የበሽታው ተጠቂነታችንን ያሳውቀናል በሚል መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበሽታው የተያዙት እነዚህ ሴቶች ጉዳዩን ከዘመድም ከወዳጅም ደብቀው በማቆየት እስከመጨረሻው ድረስ ሳያወጡት ኖረው በሽታው ስር ከሰደደና ሕክምናም ምንም ሊያደረግ ወደማይችልበት ደረጃ እስኪደርስ በሚስጥር ይይዙትና መደምደሚያው የሞት መቅሰፍትን መጠበቅ ይሆናል፡፡
የግልጽነትን ባሕል በማዳበር የጡት ካንሰርንም ሆነ ሌሎችን በሽታዎች በነጻ መወያየት
ለብዙ ዓመታት ስለ ጡት ካንሰር ምንም ግንዛቤ አልነበረኝም፡፡ ስለቅድመ ምርመራው በቂ እውቀት ሳይኖረኝ በሬን እስኪያንኳኳ ቆይቼ ነበር፡፡ቆይቼ ግን ብዙ ተማርኩ፡፡ አወቅሁ፡፡ ያም የሚከተለው ነው፡-
…….አስቀድሞ ከተደረሰበትና አስፈላጊው ቅድመ ምርመራ ከተደረገ፤ ዘመን በፈጠራቸው የሕክምና መሳርያዎች እርዳታ የጡት ካንሰር ሊታከም የሚችል በሽታ ነው፡፡ የጡት ካንሰር እንዳለባት ለአንዲት ሴት መንገር ማለት የሌት ተቀን ቅዠቷን ማስታጠቅ ማለት ነው፡፡ ሴቶች ሁኔታውን ሲሰሙ ወዲያው ወደ መደናገጥና ፍርሃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ወቅታዊውን የሚሞግራፍ ምርመራቸውን ቸል ብለው ይተዉታል፡፡ ለአንዳንዶቹ እንደ ሰበብ የመመርመሪያውን ሂሳብ የመክፈል አቅም ማጣት አድርገው ይሸሹታል፡፡ ኢንሹራንስ ከሌለ በስተቀር በአሜሪካ ሕክምናን ማድረግ እጅጉን አስቸጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ለምርመራውም ሆነ ለህክምናው አቅሙና መንገዱ ያላቸውም ቢሆኑ አያደርጉትም፡፡ ለዚህ አደገኛ በሽታም አቅም እያለ ክትትልና ህክምና  አለማድረግ ሰበብ አለው፡፡ ከሰበቦቹ ዋነኛ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለውም፤ ስለ ጡት ካንሰር ጉዳት በቂ ግንዛቤ አለመኖር ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ጨርሶ ስለዚህ ጉዳይ ማንሳትም ሆነ መወያየት አይፈቅዱም፡፡ በጠና ካልታመሙ በስተቀር ወደሃኪም አይሄዱም፡፡በዚህም እራሳቸውን ለማዳን መንገድ አይኖራቸውም፡፡
የጡት ካንሰር  ማንኛዋም ሴት ልትደብቀው አለያም ችላ ልትለው የማትችለው በሽታ ነው፡፡ የጡት ካንሰርን ችላ ማለት በደን ውስጥ  መቀጣጠል የጀመረን እሳት ችላ እንደማለት ነው፡፡ በደን መሃል ችላ የተባለ እሳት ደኑን እንደሚያጠፋው አያጠያይቅም፡፡ የጡት ካንሰርም መኖሩ ተጠርጥሮ ከታወቀ በኋላ ችላ ከተባለና አስፈላጊው ክትትል ካልተደረገ በቀር ስር እየሰደደና በሰውነት ውስጥ በመሰራጨት ተጠቂውን ለሞት መዳረጉ አይቀሬ ነው፡፡ ለብዙዎቹ ሴቶች በጡት ላይ የሚሰማን መጎርበጥ አለያም የሚታይን እብጠትም ሆነ አዲስ ስሜት፤ ሕመም እስካላስከተለ ብሎ ችላ በማለት ተዘናግቶ መቆየት የተለመደ ቢሆንም ግን አግባብ አይደለም፡፡ምንም አይነት በጡት አካባቢ የሚታይ እብጠት አስጊነቱ ቅድሚያ ተሰጥቶ ወደ ዶክር ሄዶ መታየቱ እጅጉን አስፈላጊ ው፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቃላቶች ከሁለት ዓመታት በፊት በባለቤቴ ‹‹ለኢትዮጵያዊያት እህቶቼ የተጻፈ ደብዳቤ›› በሚል ርዕስ የተጻፉ  ናቸው፡፡ የጡት ካንሰርን በማሸነፍ ታሪኳንም ከኢትዮጵያዊያት እህቶቿ ጋር ተካፍላለች፡፡ ‹‹በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስለ ጡት ካንሰር ምርመራና ህክምና ያላቸው እምነት ከአፈ ታሪክነት የማያልፍ ነው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያት ወቅታዊ የማሞግራፍ ክትትላቸውን የሚያቋርጡት ከመመርመርያው መሳርያ የጡት ካንሰር ይይዘናል ብለው ያምናሉ፡፡ ማሞግራፍ ግን የጡት ካንሰር አያሲዝም፡፡ ልክ ራጂ እንደመነሳት ቀላልና ህመምም የሌለው ነው፡፡›› በፅሁፏ ላይ ትኩረት ሰጥታ ያስገነዘበችው ‹‹አንዳንድ ኢትዮጵያዊያት በካንሰር መያዝን እንደ አሳፋሪ ተግባር አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ጓደኞቻቸውም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁባቸው አይፈልጉምና በሚስጢር ይዘውት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ ህክምናም ምንም ሊያደርግ በማይችልበት ወቅት  ወደ ሆስፒታል መሄዳቸው ግድ ይሆናል፡፡ የጡት ካንሳር በምንም መለኪያ አሳፋሪ አይደለም፡፡በሽታው ድሃና ሃብታም ሳይልና ልዩነት ሳያደርግ፤ጥቁር ነጭ ብሎ ቀለም ሳይለይ፤ የትም ዓለም ላይ በምትኖር ሴት ላይ የሚደርስ ነው፡፡››
አንዳንድ ኢትዮጵያዊያት ሴቶች ትኩረት ሊሠጧቸውና ሊገነዘቡት ስለሚገቡ ሁኔታዎች አበክራ ትናገራለች፡፡ ‹‹ከምንም በላይ ላተኮርበት የምፈልገው ጉዳይ ኢትዮጵያዊያት ሴቶች ወቅታዊ የሆነ የሃኪም ክትትል ማድረግና፤ በማሞግራፍም መመርመርንና የሚከሰተውን አላስፈላጊ ስሜት ምንነት መረዳት አስፈላጊነትን ነው፡፡ የጡት ካንሰር እንደ ኢንፍሉዌንዛ አይደለምና በጥቂት ቀናት የአልጋ ላይ እረፍት አይጠፋም፡፡ ችላ ከተባለ ህይዎትን ከባድ አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ከዚህ አስጊ ሁኔታ ለመዳን መፍትሔው ወቅታዊ ክትትል ማድረግ ብቻ ነው፡፡›› ባለቤቴም ስታስረዳ ‹‹ኢትዮጵያዊያት ሴቶች መሰረታዊ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቸል በማለት፤ በጅምሩ ሊቆምና ሊገታ የሚችለውን በሽታ በመዘንጋትና በሌላም ሰበብ በርካታ ጓደኞቿን፤ ወዳጆቿን የስራ ባልደረቦቿን፤እና የቤተሰቦቿን አባላት በዚህ በሽታ አጥታለች፡፡›› በዚህም እጅጉን ታዝናለች ትጸጸታለች፡፡
ለኢትዮጵያዊያት ሴቶች የጡት ካንሰር ማስገንዘቢያ ወር ፡ – ለኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ የተጻፈ ‹‹ደብዳቤ››
በ‹‹ደብዳቤዋ›› ላይ ባለቤቴ ስለ ውይይት ማካሄድና የአካባቢም የተግባር እንቅስቃሴ ፤ ትኩረት አስፈላጊነትን  አበክራ ትናገራለች፡፡
‹‹በአሜሪካ ለሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያት የቋንቋ የባሕል፤የገንዘብ ጥያቄ ወቅታዊ ክትትልና የማሞግራፍ ምርመራ  ለማደረግ ችግር ፈጣሪ እንደሆኑ እረዳለሁ፡፡ ይህን ችግር ለማሰወገድ ደግሞ ኢትዮጵያዊያት እህቶች እርስ በርስ በመረዳዳት፤ በአብያተ ክርስቲያናት በመነጋገር፤ በማህበረስብ ግንኙነቶች በመመካከር፤ ስለ ጡ ካንሰር በግልጽ በመወያየት፤ የአስቀድሞ ጥናቃቄን በማጎልበት ይህን ሀኔታ ሊወጡት እንደሚችሉም እምነት አለኝ፡፡ በዚህም ስለ ደም ግፊታችን እንደምንመካከረው ሁሉ ስለጡት ካንሰርም በመነጋገር በጊዜው እርዳታ ማግኘት እንችላለን፡፡››
ጥሪዋንና ተማጽኖዋን በተለይም ለኢትዮጵያዊያት ሴተ ዶክተሮች ስታስተላልፍ፤ ‹‹ሴቶች እህቶቻችንን የማስተማር ቀደምት ሚና እንዲጫወቱና፤ስለበሽታው በማስተማር፤ቅድመ ምርመራውንም በማድረግ በበሽታው የተያዙትንም አስፈላጊውን የክትትል ህክምና እንዲያደርጉ በመምከርና በመርዳት እንዲተባበሩ ትጠይቃለች፡፡›› በአሜሪካ ነጻ የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ አቅም ለሌላቸው ነጻ ምርመራ የሚያደርጉ በርካታ የአካባቢ ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች አሉ፡፡›› ተስፋዋም ‹‹ሴቶች እህቶቿ በየአካባቢያቸው ተሰባስበው በመደራጀት በመላው አሜሪካ የመተጋገዝ ቡድን ለማቋቋምና ለመረዳዳት ይችላሉ፡፡›› የሃይማኖት ተቋማትንም ‹‹የሙያው እውቀት ያላቸውን በመጋበዝና ሴቶችንም በማስተባበር አስፈላጊውን ትምህርት እንዲያገኙ በማድረጉ ረገድ ቅድመ ምርመራን፤ የማሞግራፍ ምርመራ፤ለማድረግም ለማያውቁት መንገዱን በማሳየትና በማበረታታት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ እንዲተባበሩ ታሳስባለች….በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል የተቋቋሙ በርካታ የሬዲዮ ጣቢያዎች አሉ፡፡ እነዚህ ጣቢያዎችም የጡት ካንሰርን አስመልክተው በጣቢያቸው ላይ ጥቂት ደቂቃዎች በመመደብ ስለበሽታውን ቅድመ ምርመራው፤ ስለክትትል ህክምናውና ነጻ ሆስፒታሎችና ከሊኒኮች የሚገኙበትን መንገድ በመጠቆም ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡ ከዚሁ ባልተናነሰ መልኩ በድህረ ገጾችም ላይ ይሄው እንቅስቃሴ ሊደረግ ተገቢ ነው፡፡ ተስፋዬም በሚቀጥለው ዓመት በሚከበረው የሴቶች የጡት ካንሰር ማሳወቂያና መሳሰቢያ ወር ላይ ብሔራዊ ፕሮጋራሞችም እንደሚቀናጁና እንቅስቃሴውም በሃገር አቀፍ ደረጃ ጎልብቶ ማየትን ነው፡፡››
በዚህ የማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ወር፤ይህንን መሰሉን ጉዳይ ማካፈሉ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በቅድሚያ ይህንን ገዳይና ቀሳፊ በሽታ ደጋግሞ ማጥፋት ወሳኝ ነው፡፡ ምናልባትም ሌሎች የበሽታውን ቀሳፊነት የተገነዘቡና በበሽታውም የተጠቁ  ፊት ፊት በመውጣት ልምዳቸውንና ያደረጉትን ምርመራና ቅድመ ጥነቃቄ በተመለከተ በዓለም ላይ ባሉ ኢትዮጵያዊያት መሃል ጠቃሚ የመነጋገርያና የመረዳጃ ቡድኖች ይቋቋማሉ የሚል ተስፋ አለን፡፡ የጡት ካንሰርን የማሸነፊያው መንገድ ስለበሽታው በቂ እውቀት ማግኘትና ቅድመ ምርመራንና ክትትልን ሳያስተጓጉሉ በማድረግ ብቻ ነው፡፡  ሁለተኛም ለእህቶቻችንና ለወንድሞቻችን ልናረጋግጥ የምንፈልገው፤ በጡት ካንሰርና በማንኛውም የካንሰር አይነት መያዝ፤ አንዳችም የሚያሳፍር፤ የሚያሸማቅቅ፤ ጨርሶ በሌላ ስም የሚያስጠራ፤ ፈጽሞ አጸያፊም ያልሆነ፤  እንዳልሆነ ነው፡፡ ይልቅስ የሚያሳፍረውና የሚያሳስበው፤ አጉል ተብሎም ሊጠቀስና ሌላም ስም ሊያሰጥ የሚችለው፤ አስፈላጊው አገልግሎት ሁሉ በተሟላበት ሃገር ተቀምጦ ቅድመ ምርመራውንን ክትትሉን በአግባቡ አለመወሰዱና በአጉል አፈ ታሪክና ባሕል ተሸብቦ፤ መገለል ይደርስብኛል በሚል ወሬና ተረት ለሞት መዳረግን መምረጥ ነው፡፡››
እንደ እውነቱ ከሆነማ ከጡት ካንሰርም ሆነ ከሌላውም የካንሰር ህመምተኝነት ድኖ መገኘት የትም ቢኬዱ የሚያኮራና የሚያስከብር ተግባር ነው::  ከጡት ካንሰር ጋር ገጥሞ በሽታውን ድል ማድረግ ልክ አንድ የጦር ተዋጊ ዘምቶ ጠላቶቹን ድል በማድረጉ ሂደት ከፍተኛውን ሚና በመጫወትና ለድሉም ጀግንነቱ ብቃት ያለው ተግባር በመፈጸሙ ለሜዳልያ ሽልማት እንደሚበቃው ጀግና መቆጠር ማለት ነው፡፡ ማለቴም የጡት ክንሰርን ተቋቁመው ድል ያደረጉና ከበሽታው የተፈወሱትን እህቶች ጥንካሬ፤ ቆራጥነት፤ አልበገር ባይነት፤ ጀግንነት፤ ድል አድራጊነት፤ተመልክቼ መስክሬያለሁና ነው፡፡ እንዲሁም ከበሽታው ጋር ትንቅንቅ ተያይዘው ፤ ሲሰቃዩ፤መከራ ሲበሉ፤ አቅም ሲያጡ፤ በሽታው ስር እየሰደደ ሲጨርሳቸውና ለሕልፈተ ሞት ሲዳርጋቸውም መስክሬያለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች: ወንድሞች ስለጡት ካንሰር በሚደረገው ማንቂያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አምናለሁ፡፡ አንዳንድ ጥቃቅን ተግባራትን በቅድመ ምርመራውና ክትትሉ ዘርፍ በመውሰድ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ፡፡ለዚህም በቅድሚያ ራሳችንን ማስተማርና ማወቅ ይገባናል፡፡ የሁላችንም እህቶች፤ እናቶች፤ ሚስቶቻችን ባህላዊ ተጽኖና አለማወቅ ስላለባቸው ስለበሽታው ቅድመ ምርመራም ሆነ ክትትሉን በበሽታው ክፉኛ እስኪጠቁና መንገዱ እስከጠብ ድረስ በሚስጥር መያዝ ስለሚመርጡ መደረግ ያለበትን ሳያደርጉ ይቀራሉ፡፡ እነዚህ እናቶቻችን: እህቶቻችን፤ ሚስቶቻችንና ወዳጆቻችን ስለ ጡት ካንሰር አስፈላጊው እውቀት እንዲኖራቸውና ቅድመ ምርመራውንም ሆነ ማሞግራፍ ምርመራውን፤ ክትትሉንማ ማደረግ እንዳለባቸው ሳንሰለችና ሳንደክም በይሉኝታም ሳንታሰር በመንገርና በመጎትጎት አቅጣጫውን ማስያዝና  ሂደቱንም ማገዝ ይገባናል፡፡ በዚህ ሁሉም ነገር ባለበት ሃገር ተቀምጠን በበሽታው ተይዘን ግን ምንም ሳናደርግ በሚስጥር ይዘን ለሞት መዳረግ ከማሳፈርም ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ ሁላችንም ተባብረን በዚህ የጡት ካንሰር ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ወር (የወሩን ሶስተኛውን አርብ) ልዩ እንቅስቃሴ በማድረግና ሴቶች እህቶቻችንን በማስተባበር ብሔራዊ ማሞግራም ቀን በማለት ሰይመን ለምርመራ ማስተባበር ይጠበቅብናል፡፡
ለጡት ካንሰር ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ወር በርካታ የእግር ጉዞዎችና ሌሎችም ተግባራት እየተዘጋጁ በመሆኑ፤ይህንንም በመጠቀም ማስተባበራችንን ማከናወን ይጠበቅብናል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያዊያት ተሰባስበው በሚኖሩባቸው መንደሮች በነዚህ እንቅስቃሴዎች መሳተፍን ተግባራዊ ማድረግ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነውና ለዚህም መትጋትና መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ተስፋ በመቁረጥ በዚህ ሕመም መሰቃየትና በግል መጨነቅ ለኢትዮጵያዊያት ሴቶች አዲስ ልምድ አይደለም፡፡ ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች በተለይም የጡት ካንሰርን በመዋጋት ላይ ላሉት እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ስለ ጡት ካነሰር የሚያስረዱ ማንኛቸውም ነገሮች፤ (ነጻ የማሞግራም አገልግሎት፤የግልና የመንግስት ህክምና ቦታዎች) በጥንቃቄ ተሰባስበው ለኢትዮጵያዊያት ሴቶች ሊደርሱ ይገባል፡፡ በተለይም ወንዶች ይህን ጎታችና አስቀያሚ የሆነውን የሚስጥራዊነት፤ድብቅነትን፤ ጎጂ ባህል በተለይም የጡት ካንሰርን በተመለከተ የማጥፋቱ ሃላፊነትና በአደባባይ ስለጡት ካንሰር መነጋገርንና መወያየትን ባህል ማድረጉ እንዲለመድ ሃላፊነቱ የወንዶች ነው፡፡
በዚህ ወር በሽታውን ተቋቁመውና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ለድል የበቁትን እህቶቻችንን የምናከብርበት ወር እናድርገው፡፡ ከጡት ካንሰር ጋር ተዋግተው ድል ካደረጉ በላይ ጀግና የለምና፡፡ በጡት ካንሰርም ሕይወታቸው ያለፈውንም እናስባቸው እናስታውሳቸው፡፡ በትምህርትና በማሳወቅ ረግድ በሰፊው ማህበረሰብ ውስጥ የጡት ካንሰርን ለማሸነፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በማጠናከር እንስራ፡፡ የክትትል ምርመራና ቅድመ ጥንቃቄ ትክ የማይገኝላቸው የጡት ካንሰርን ማሸነፊያ ሃይለኛ መሳርያ ናቸው፡፡ እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድ ባንድ ሴቶቻችንን ከጡት ካንሰር ተጠቂነት ነጻ እናድርጋቸው!
‹‹በሽታውን ያልተናገረ መድሐኒት አይገኝለትም፡፡›› እንዲሉ!
የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
http://open.salon.com/blog/almariam/2012/10/21/breast_cancer_awareness_for_ethiopian_women_and_men
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

”ላለመማር መማር.. ፤ ከራስ ክህደት እስከ ሀገር ማፍረስ…”


ከፊልጶስ / ጥቅምት 2005
በመጀመሪያ ‘ራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም  በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውን ‘ርስ-በ’ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣ ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች።
የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር  ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?
በቅርቡ የወያኔው ”የበኩር አባት” አቶ ስብሐት ነጋ ”….. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር……..” ሲሉ ተሰምተውል። ይህ በ’ርግጥ የለመደነው ክህደትና ሸፍጥ ነው። ታዲያ አኒህ ሰው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸው ጥላቻ ይበልጥ በሽበታቸው ዘመን ስር እየሰደደና እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። ብዙውን ግዜ በሌሎች ላይ ጥላቻ ያለባቸው ሰዎች ለራሳቸው ከሚሰማቸው የበታቸነት ስሜት የሚመጣ ሲሆን መድረኩንና አጋጣሚወን ሲያገኙ ደግሞ እንደወያኔ ሀገረንና ህዝብን ከማዋረድና  ይዘው ከመጥፋት  ወደ ኋላ አይሉም።
የአቶ ስብሐት የክህደትና የጥላቻ የበኩር ልጃቸው  የሆነው አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን አፍርሶና ሕዝቦቿ ‘ርስ-በርስ አባልቶ ሳይጨርስና ሳይሳካለት ወደ ማይመለስበት ስለሄደ፤ እሱ ያላያትን ”የፈራረሰች ኢትዮጵያን” እሳቸው ለማየት ካላቸው ጉጉት አንጻር የሚያደርጉትን አ’ተው ግራ ተጋብተዋል። ምክንያቱም ”ታላቋን ትግራይ” የመመስረት “ቅዥት”፣ “ቅዥት” ሆኖ እንደቀረ ሁሉ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረሱም እኩይ ምግባራቸው ደግሞ ‘’ቅዥት’’ ሆኖ ሊቀር መሆኑ እንቅልፍ ነስቷቸዋል።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ይ’ች ዓለማችን አስከ አለች ድረስ እንኖራለን። ይህ ሚሊዮን ግዜ ተነግሮ’ል። መነገር ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ዜጎቿ መሰዋአትነት ሲከፍሉበት ኑረዋል፤ አሁንም የተፈለገውን ያህል ውጤት ባያመጣም እየከፈሉ ይገኛሉ። ግን የወያኔ ገዥዎች ከልጅነታቸው እስክዚች ሰዓት ድራስ አእምሮ’ቸው  በጥላቻና በተንኮል አድጎ፣ በክህደትና በዘረኝነት ጎልምሶ፣ ከሀገራችን ጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት እኩይ ዓላማ፣ በሽበት ዘመናቸውም ሆነ ”በትምህርት” ሊወገድ አልቻለም። አቶ መለስ ከነ ጥላቻቸውና ከነ ዘረኝነታቸው ሄደውል። ቀሪዎቹ እነ አቶ ስብሐት ደግሞ ”ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል!” እንዲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን እንደ ምክንያት እያደረጉ ያመላቸውን “ዳቦ ይልሳሉ”።
የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጠ/ሚኒስተር ስልጣን መድረስ  ዋናው ምክንያት እንደሚከተለው ነው፤
1/አቶ መለስ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ምክትል ጠ/ሚኒስተር ያደረጓቸው ኦሮሞና አማራ ነኝ ባይ ተለጣፊዎን ለማራቅ ነበር። ምክንያቱም በውቅቱ ሁለቱም ተለጣፊዎች የምክትልነቱwho is hailemariam desalegnቦታ ይገባናል በማለት ”ከሚስቶቻቸው” ጋር አልጋ ላይ ያንሾካሹኩ ስለነበር ነው። ታዲያ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡቡ ተለጣፊ ቡድን በመሆናቸው እንደ መፍትሄ የተውሰደ ነው።
2/ አቶ ሃይለማርያም ወያኔን ”እንድ ግል አዳኛቸው” የተቀበሉ በመሆናቸውና አቶ መለስ የተናገሩትን መልሰው እንደ በቀቅን የሚያስተጋቡ ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ምንም አይነት ችግር የማይፈጥሩ ”ተነጅ” መሆናቸውተ ሌላው ምክንያት ነበር። አሁንም ”የመለስ ራእይ” እያሉ እየደነፉብን ነው። ለነገሩ የ’ራሱ ራዕይ ያለው ሰው ከመጀመሪያውም ወያኔ አይሆንም ነበር።
3/ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ እነ አቶ ስብሐት አቶ ሃይለማርያምን ጠ/ሚኒስተር ለማድራግ ማቀድ ቀርቶ አልመውተም አያውቁም ነበር።  የጠ/ሚኒስተርነቱን ቦታ ለወያኔ ተወላጅ ”ተገዳላይ” ለመስጠት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ነገር ግን የ’ርስ በርስ ሽኩቻው የወያኔን ህልውና እስከመፈታተን ደረሰ። ታዲያ እነ አቶ ስብሐት ”’ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ነው…” ማለታቸውን ስሰማ በልጅነቴ የሰማሁትን ተረት አስታወሱኝ። ተረቱ እንዲህ ነው፤……ሁለት አብረው የሚኖሩ ወንድና ሴት ፍዬሎች ነበሩ። አንድ ቀን ውንድዬው ፍዬል የወይን ዛፍ አየና ወደ ዛፏ አመራ። የወይኑን ፍሬ ለመብላት ቢሞክር ሊደርስበት አልቻለም። እናም ‘ራቅ ብሎ ሄዶ ጋደም አለ። ሴቷ ፍዬል በተረዋ ወደ ወይኗ ዛፍ አዘገመች። የወይን ፍሬውን ለምብላትም ሞከረች። ግን አልቻለችም። ወደላይ ዘለለች። አልቻለችም። የፊት እግሮቿን ተጠቅማ ወደ ወይን ፍሬው ለመድረስ ሞከረች። አልቻለችም። ምንም ማድረግ እንደማትችል ስታውቅ ምራቋን እየዋጠች ወደ ጓደኛዋ ሄደች። እሱም ከርቀት ይከታተላት ነበርና ” እንዴት ነው የወይኑ ፍሬ?” ሲል ጠየቃት። ” እባክህ… ልበላ ፈልጌ ስቀምሰው የወይኑ ፍሬ ይመራል።” አለችው።  እሱም ” አይ ያንች ነገር!….. ዘለሽ ..ዘለሽ ሲያቅትሽ ይመራል ትያለሽ።” በማለት መለሰላት። ታዲያ ዛሬ ወያኔዎች ”ዘለው..ዘለው… ሲያቅታቸው፣ የተሻለ ነገር መናገር አይችሉምና “ስልጣኑን ከአማራና ከኦርቶዶክስ ለማጽዳት ነው…” ማለት ሳይብቃቸው ‘’የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ የበቃ አይደለም።” በማለት መዘላበዱን ተያያዙት።
4/ ወያኔዎች አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳይፈልጉ ጠ/ሚኒስተር መሆናቸውን አማራጭ አጥተው ሲቀበሉ በ’ርግጥ  ቢሳካላቸውም ባይሳካላቸውም ሁለት ነገሮችን እሳቤ ውስጥ አስገብተዋል፤
- የመጀምሪያው ጠ/ ሚኒስሩን ለዚህ ስልጣን የበቁት ባላቸው አፍቅሮ ወያኔ ስለሆነ፤ ከወያኔዎች ፈቃድ ውጭ ምንም የሚያደርጉት ነገር እንደሌለና ላድርግ ቢሉ እንኳ’ በቀላሉ ማስወገድ እንደሚችሉ ስለአመኑ።
- ሁለኛው እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የ’ርስ በርስ ሽኩቻዎችን ስለሚያስወግዱ ጠ/ ሚኒስሩን እንደ ግዜ መግዥ ሊጠቀሙባቸው በማሰብና በማቀድ ነው።
5/ ሌላው ደግሞ የአቶ መለስ ሞት ያስደነገጣቸው ገዥዎቻችን ግራ ሲገባቸው፤ በሁለት እግራቸው የቆሙ ለመምሰልና ሁሉም ነገር በ’ነሱ ቀጥጥር ስር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፤ የተለመደው አሳፋሪ ፓለቲካ ግን ወያኔ ተወልዶ ያደገበትን የኢትዮጵያን ጥላቻና እርስ-በ’ርስ  ህዝብን የማባላት እኩይ የተለመደ ምግባር ለመግለጽ የታሰበ ነው። ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “አቶ ስብሐተና የተነኮል ፓለቲካ” በሚል ርዕስ እንደገለጹት “…..አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው።….” ግን  ፕሮፌሰር ይህ ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ላለፉት ዓመታት ወግቶናል! ቆርጦናል! ከፋፍሎናል! አሁንም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተሳለው የቂል ሰይፍ  መገዝገዙን ለማስቀጠል ደፋ-ቀና እየተባለ ነው።
ወያኔዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
ምንም ይበሉ ምን፣ ወያኔዎችና ተከታዮቻቸው እየመረራቸውም ቢሆን መዋጥ ያለባቸው ሀቅ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከየትም ጎሳ ይምጡ፣ ምንም አይነት ሀይማኖት ይኑራቸው፣ ኢትዮጵያዊ አስከሆኑ ድረስ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የግል ማንነታቸውን ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም። መግባትም ሆነ መታሰብም የለበትም። ኢትዮጵያዊነታቸው ከምንም በላይ በቂ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅማችን ያስጥብቃሉ ወይ? መብታችንና ነጻነታችን ያከብራሉ ወይ? በአጠቃላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ክብርና ልዕና መሉ ስልጣናቸውን (በህዝብ ያለተመረጡ ቢሆንም) ተጠቅመውና ሕግን አክብረው ይሰራሉ ወይ? ከወያኒያዊ አመለካከት የጻዳ አስተዳድር ይመሰርታሉ ወይ? በሚለው ላይ ነው ህዝብ ማውገዝም፣ ማወደስና መታገል  የሚፈልገው። በ’ርግጥ  እስከ አሁን ድረስ እንደታዘብነው ሰውየው ገና ”ከተገዥነትና ከተነጅንት’’ ያለመውጣታቸውን እያረጋገጡ ነው። የ’ኛም ትግል ይቀጥላል።
ፊልጶስ / ጥቅምት 2005

ጌታቸው ጀቤሳ (ያሬድ ጥበቡ)

ጌታቸው ጀቤሳ
ከቴዎድሮስ ሐይሌ
“ከአህያ የዋለች ጊደር ….ተምራ ትመጣለች” አበው እንዲሉ ዉሎውን ከቀጣፊ ጋር ያደረገ ምን
ያህል ቀና ሰው ቢሆን ያዋዋዩን አጉል ምግባር ማንጸባረቁ የማይቀር ነገር ነው ።ይህን ያነሳሁት ያለ
ምክንያት አይደለም ያኔ በሃገር ቤት እያለሁ በነጻ ጋዜጦች ላይ ሃሳቦቹነን አንብቤና በሠውየው ግርማ ሞገስ
ጭምር እምነት አድሮብኝ ትልቅ ግምትና አክብሮት እሰጠው የነበረው የቀድሞው የኢህዲን (ብአዴን)
መሪ የነበረው አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ)  ካለው ጥልቅ ተሞክሮ ልምድና እውቀት አንፃር
የማይመጥን እንደ ውሃ ላይ ኩበት የሚዋልል የረጋ አቋም እንደሌለው ስታዘበው የቆየሁ ቢሆንም እንደዚህ
ሰሞን ጽሑፉ ግን የወረደና ከአንድ ገበሬ ማህበር ካድሬ ያነሰ አመለካከትና አቋም ይኖረዋል ብዬ ፈጽሞ
ለመቀበል ቢያስቸግረኝም ግለሰቡ ግን ራሱን በዚህ ያህል ደረጃ ዝቅ አድረጎታል ።
አቶ ያሬድ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ግዜ በአካል ያገኘሁት የዛሬ አራት አመት አካባቢ
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገርና የጋራ ወዳጃችን ዶክተር አረጋዊ በርሔ መጽሐፉን ለማስመረቅና እግረ
መንገዱንም ሃገራዊውን ትግል ለማጠናከር መጥቶ በነበረበት በዚያን ወቅት በአንድ አክቲቪስት የሕግ
ምሁር ቢሮ ውስጥ ተሰባስበን በምንወያይበት ወቅት ዘግይቶ በመምጣት የተቀላቀለን አቶ ያሬድ ጥበቡ
ማናችንም አስቀድመን ያላደረግነውንና ያላሰብንበትን የዶክተር አረጋዊን መምጣትና ዶክትሬቱን
በማጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ገልጾ ይዞ የመጣውን ኬክ በመቁረስ በምርቃትና በጎ ምኞቱን በመግለጽ
ያሰየው ወንድማዊ ፍቅርና ወገናዊ አክብሮት ካስደመመኝ በላይ በእለቱ በነበረው ውይይት ላይ በአቶ
ያሬድ ይቀርብ የነበረው ፖቲካዊ ትንተና ስለ አገዛዙ ባህሪና ስለ መሪዎቹ ስብዕና በአጠቃላይ ይህ ቀረሽ
የማይባልና ጋዜጣ ላይ የማውቀው ሰው ከጠበኩትም በላይ የበሰለ ሆኖ በማግኘቴ በጣም ከመደንቄ የተነሳ
አወይ ያ ትውልድ በጎ ሲሉት መጥፎ ደግ ሲሉት ክፉ ሆኖ ጭራው የማይጨበጥ ግራ እንደተጋባና ግራ
እንዳጋባን የጎጥ የአንጃና የጥቅም መደቦች ተከፋፍሎ ዋና ተጋዮችን ስደት እየበላቸው ከዚህ ሁሉ
የፖለቲካ ገበያ የኔ ትውልድ ምን ይማር ይሆን የሚል ሃሳብ በግዜው ጭሮብኝ ነበር።
የአቶ ያሬድን ስብዕና እየካብክ ናድከው አትበሉኝና ግለሰቡ ሃገር ቤት በሚታተም ዕንቁ መጽሔት
ላይ የጻፈውን ከዘ ሐበሻ ድህረ ገጽ ላይ በስካነር ኮፒ ተደርጎ የወጣውን ጽሑፍ ሳነብ በወጣትነቱ በረሃ
የተንከራተተው በአቋም ልዩነት ለስደት የበቃው ያሬድ ጥበቡ የሰፈር አሮጊቶች እንኳ ጉልቻ ቢለዋወጥ
ወጥ አያጣፍጥም ብለው ያጣጣሉት የሃይለማርያምን ሹመት አወዳድሶና አንቆለጻጽሶ የሚካሄደው
የስልጣን ሽግግር ታሪካዊነትንና የወደፊቷን ኢትዮጽያ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ተደርጎ በአቶ ያሬድ
የቀረበው ውሃ የማይቋጥር ትንተና በእኔ አቅም ግለሰቡን አላዋቂ ለማለት የሚያስችል አቅም ባይኖረኝም
የጽሁፉ ጽንሰ ሃሳብ ከመነሻ እስከ መድረሻው የውሸት አባት የሆነው በረከት ስሞን ጽፎ ያሬድ በሚል ስም
ያወጣው የሚል የዋህ ግምት የሚያሰነዝር አለያም የባልቴቶች ተረት ተረት የሚሰኝ አይነት ነው የሆነብኝ።
የአቶ ያሬድን ታሪክ ከራሱም አንደበትና ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ለመረዳት እንደቻልኩት
እናት ድርጅቱን ከአሲንባ ከድቶ የያኔውን ተጋድሎ ሐርነት ትግራይ (ተሐት) የዛሬው ሕወሐት ጉያ ገብቶ
የሃገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር ከገንጣይ አስገንጣይ የወንበዴ መንጋ ጋር ለመተናነቅ የተመመውን
ህዝባዊ ሰራዊት በመውጋት የሻብያና የወያኔ ጨለምተኛ ቡድን ለስልጣን መብቃት ያሬድና ጓዶቹ2
2
በትግሬው ነጻ አውጪ ሸበጥ ስር ተንበርክከው የፈጸሙት ታሪካዊ ስህተት ሂሳቡ ሳይወራረድ በምርጫ
ዘጠና ሰባት የቅንጅት የሰሜን አሜሪካ አመራር አባል በመሆን አቶ ያሬድ ያደረገው ተሳትፎ ያለ ውጤት
በትርምስና በሁከት ተበትኖ የህዝብን ተስፋ ያጨለሙት አንሶ ሠው በላው መለስ ዜናዊ ያስፈጃቸው
ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ ያለቁት ወገኖቻችን ትዝታው ባልጠፋበት ቁስላችን ፍትህና ርዕትህ አግኝቶ
ባልሻረበት ሁኔታ ላይ አቶ ያሬድ እነዚህን ግፉዐን ዘንግቶ ያለበትን ሞራላዊ ሃለፊነት ረስቶት ለመለስ
አምርሮ ለማልቀስ የአንዲት መበለት ደረት መምታት ምክንያት ሆነኝ ሲል ያቀረበው ሃተታ አሳፋሪነት
የሚያጠናክረው ግለሰቡ ይህን ሲል በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የእንቦቃቅላ ደረት በጥይት የተነደለው
አሳዝኖት አልነበረም ማለት ነው ወይስ ሌላ ? ለኔ እንደገባኝ የአቶ ያሬድ አዛኝ ቅቤ አንጓችነት ምንጩ
ለመለስ ካለው ፍቅር አለያም ከሰባዊነት የመነጨ ሳይሆን በዲያስፖራው ፖለቲካ ውስጥ ከቅንጅት
መፈረካከስ በኋላ በአቋሙ መዋዠቅ ተቀባይነት አጥቶ በመገፋቱ በተለያዩ ድርጅት ውስጥ ያሉ ጓዶቹን
ለማብሸቅና ዲያስፖራውን ለማናደድ ግለሰቡ የጨዋታውን መስመር አልፎ የፈጸመው የፖለቲካ ዝሙት
ታረኩን የሚያቆሽሽ ብቻ ሳይሆን በወዲያኛውም ሰፈር ተቀባይነት የማይስገኝለት ከንቱ ድካም ከመሆን
የዘለለ አንዳችም ትርፍ የማያስገኝ የሞራልና የስብዕና ክስረት ነው።
በመሰረቱ አቶ ያሬድ ሁኔታዎች መለወጥ ሲጀምሩ እንደለመደው መልሶ እንባዬን መልሱልኝ
ላለማለቱ ማረጋገጫ ባይኖረንም እንደ ቀደመ ባህሪው ግን በረከት ስምዖን ናፈቀኝ የአዲሱ ለገሰ ሳቁ ትዝ
አለኝ ያለው የሚታወስ ሲሆን ወዲያው ብዙም ወራት ሳይቆይ ናፍቆቴን መልሱልኝ ሲል ተሰማ አክሎም
የበረከት መጽሃፍ በሃሰት የተበረዘ መሆኑን በመግለጽ ለውሸታምነቱ ወደር የማይገኝለትን እውነት መናገር
ለዛ የአሞራ አፉ አለርጂ የሆነበትን በዚህም ምግባሩ ህጻን አወቂ የሚያውቀውን የወያኔውን ቃል አቀባይ
አቶ ያሬድ እንደ አዲስ ነገር ለቀባሪው ሊያረዳ ሞክሯል ፤ ሰውዬው በዚህም ባበቃ መልካም ነበር የመለስን
ሁኔታ አስመልክቶ ኢሳት አስተማማኝ ምንጮቹን በመጥቀስ መለስ መሞቱን ያቀረበውን ዘገባ
ለማስተባበል በረከት ስምዖን ለአዲሱ አመት ዋዜማ ስራ ይጀምራል ሲል የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ
በመመርኮዝ አስተያየቱን የተጠየቀው አቶ ያሬድ የኢሳትን ዘገባ ለማኮሰስ የምንጮቹን ማንነት አጣርቶ
ውሳኔ ላይ ከመድረስ ይልቅ በረከት ያለውን ለመቀበል ያቀረበው ምክንያት የበረከትን አይኖች
አውቃቸዋለሁ የሚል የመጽሃፍ ገላጭ የደብተራ መልስ ሲሰጥ በአግራሞት ታዝቤዋለሁ።
ካፈርኩ አይመልሰኝ የሆነው የያሬድ ሙልጭልጭ አመለካከትና አቋም አልባነት ካንጸባረቀበት
ከዚህ መጽሄት ጽሁፍ የመለስ ህልም ብሎ ሊተነትነው የፈለገው ነገር ፈጽሞ ሊገባኝ ያልቻለና ግራ
የሆነብኝ በለጋ እድሜው በረሃ ለበርሃ የተንከራተተለት ድርጅት ራዕይ የሌለው የተነሳለትን አላማ የሳተ
ነው ብሎ የተለየውን ይህን ህልም አልባ ስርዓት ለማስወገድ ከቅንጅት እስከ ኦነግ ሁሉን የሞከረ የስደት
ፖለቲከኛ ጓደኞቹ ምኒስትርና አንባሰደር ሆነው አለማቸውን ሲቀጩ ጊዜውን ከአንዱ ጥግ ወደሌላው
በሚል ያሰለፈው በእውነቱ ሊቆጨው ይገባል ለምን ቢባል አቶ ያሬድ መለስ በጎ ሕልም አለው ብሎ
ያምን ከነበረ የበረከት ሳቅ የአዲሱ ለገሰ ጨዋታ ትዝታ ከሚሆንበት ለምን የማምሻ እድሜውን በስደት
ለመግፋት እንደተገደደ ሳስበው ሳስበው መልስ የለኝም። የቀድሞ የትግል ጓዶቹ ባለሳቆቹና ህልመኞቹ
ኢትዮጽያ በመዳፋቸው ውስጥ እንዳለች ወፍ አድራጊና ፈጣሪ አሳሪና ፈቺ ሻሚና ሻሪ ፍርድም እውነትም
ሃይልም እነሱና እነሱ ብቻ በሆኑበት ሃገር ለያሬድ ቦታ ጠፍቶ ነበር እንዴ ፤ እንድ አድርጎኛል።
ያ በወጣትነቴ ጋዜጣ ላይ አይቼ ተስፋ እጥልበት የነበረ ሰው እንዲህ ሲምታታ ሳየ በጣም
አዝኛለሁ። አቶ ያሬድን መነሻ ስላለኝ እሱ ላይ ብዙ አልኩኝ እንጂ በደምሳሳው የያሬድ ዘመን ትውልዶች
መለስ ዜናዊ በረከት ስምዖን የደርጉ ግስላ የኢሃፓው ፋኖ የወያኔው ቀበሮ በአጠቃላይ የኔ የዚህ ዘመን3
3
ትውልድ ካለፈው ትውልድ ከተማረው በጎ ነገር ይልቅ የቀሰመው አሉታዊ ነገር ይበዛዋል።እሱም
ቡድናዊነት ዘረኝነት አንጀኝነት ኢዲሞክራሲያዊነትና አቋም አልባነት ጠቅሶ ማለፉ ተገቢ ይመስለኛል።
በእርግጥ ከዛ ካለፈ ትውልድ ውስጥ በቅንነትና በታማኝነት እስከመጨረሻው የፀኑ ለዐርያና ተምሳሌትነት
የሚጠቀሱ አያሌ ወገኖች ቢኖሩም አሉታዊያኑ ግን ደምቀው እንደ አቶ ያሬድ ያሉት በመታየታቸው
የትውልዱን በጎ ታሪክ በማወየብ አስተዋፅዖ አድርጓል። እዚህ ላይ አቶ ያሬድን ልብ እንዲለው
የምመክረው በተናጥል የሁለታችንም ልባዊ ወዳጅ የነበረውና በሞት የተለየን ሙልጌታ ሃይሉ ሁለታችንም
በመቃብሩ ላይ አምርረን ያለቀስንለት እስከመጨረሻው ከአቋሙ ስንዝር ሳይነቃነቅ ጓደኝነት ጥቅም
ምቾትና ሌላም ሌላም ነገር ሳያታልለው እስከሞት ለሚያምንበት አቋም የታመነ  በመሆኑ እንደነበር ከኔ
ይልቅ አቶ ያሬድ ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ምንም በእድሜ የአባትና ልጅ ያህል ብንራራቅም በድፍረት
ግን አቶ ያሬድ ወጥና ጽኑ አቋም እንዲኖርህ እመክራለሁ።
ለማጠቃለለ ምንም በአቶ ያሬድ ላይ የራሴን ግንድ የሚያህል ሃጥያት ሳላጠራ ወቀሳና ትችት
ብሰነዝርም አሁንም የታናሽነት ጥልቅ አክብሮት እንዳለኝ መግለጽ እወዳለሁ። ሌላው ሳልገልጽ
የማላልፈው አቶ ያሬድ ስለ ሃይማኖቱ ተጠይቆ የሰጠው መልስና ሌሎችም የሱ ዘመን ሰዎች ያየሁትና
ያደመጥኩት ከዛ ሁሉ አበሳና መከራ በኋላ እንኳ የእግዚያብሄርን ሕልውና ለመቀበል መቸገራቸውንና
ሃይማኖት አልባ ጉግማንጉግ መሆናቸውን ሳስብ ለበረከት መቀላመድ ለመለስ ጨካኝነት ለያሬድ መዋዠቅ
አንዱ ምክንያት የመንፈሳዊ ህይወት ድርቀት የፈጠረው ምክንያት ይሆን ወይ እንድል አድርጎኛል ፤
ሃይማኖት የሞራል ልጓም መሆኑን ሳይንሳዊው አለም እንኳ የተቀበለው ሃቅ እንደመሆኑ የማይዳሰሰውና
የማይጨበጠው ተምኔታዊው የማርክሲስቱ አስተምህሮ ካስከተለብን የማንነት ቀውስና የባህል ጉዳት
ባሻገር ዛሬም ድረስ ከማጡ ልንወጣ ያልቻልነው ምድራዊያን ፈላስፎቹን አምነንና ተቀብለን ዘላለማዊውን
አምላክ በመካዳችን በመሆኑ ፤ ወደ ልቦናችን ተመልሰን መቅሰፍትና መዓቱን እንዲያበርድልን ሃገራችንንም
ከትርምስ ክእርስ በእርስ ግጭት አርቆ ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንዲያሸጋግርልን ሁላችንም ከልቦናችን ላይ
የተሰካውን የጥላቻ የሐሰተኝነት የመለያየት የክፋትና የዘረኝነት አሽክላ ነቅለን ፤ የፍቅር የእምነትና የበጎነት
አፀድ እንተክል ዘንድ እግዚያብሄር ይርዳን።አሜን!!!