Saturday, March 30, 2013

የዐማራውን ዘር የማጥፋቱ ዘመቻ በስፋት ቀጥሏል


የዐማራውን ዘር የማጥፋቱ ዘመቻ በስፋት ቀጥሏል
ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተላለፈ “ለወገን እንድረስ” ጥሪ
ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ነፃ አውጪ ድርጅት ዐማራውን ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የጀመረውን ተልዕኮ አሁንም ያለማሠለስ
ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ከጎንደር በወልቃይት ፣ በጠገዴ እና በስሜን አውራጃዎች፤ እንዲሁም በወለጋ፣ በኢሉባቦር፣ በከፋ፤ በአርሲ፣
በሐረርጌ፣ በባሌ እና በአፋር አካባቢዎች ሲፈፅም የቆየውን ዐማራን ከምድረ-ኢትዮጵያ የማጥፋት ሥራ ማስታወስ ይገባል። ሠሞኑን
ደግሞ የጥፋት አድማሱን ይበልጥ በማስፋፋት ቤንሻንጉል-ጉሙዝ ብሎ በሠየመው አካባቢ (በቀድሞው የጎጃም ክፍለ ሀገር የመተከል
አውራጃ እና በወለጋ ክፍለ ሀገር የአሶሣ አውራጃ) በሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች ላይ አነጣጥሯል። የግፉ ብዛት እኒህን ለፍቶ አዳሪ
ዐማሮች ለዓመታት ከኖሩበት አካባቢ ኃብት ፣ ንብረታቸውን ነጥቆ ማባረሩ ሣያንስ ሰብዓዊ ክብራቸውን አዋርዶ በተለምዶ “አልቃይዳ”
ተብለው በሚታወቁት የአይሱዙ የጭነት መኪናዎች እንደከብት እያጎረ ማፈናቅሉን ቀጥሏል። ክእኒህ ተፈናቃዮች መካከል ከትላንት
ወዲያ ከአሶሣ ወደ ነቀምት ሲያጓጓዘቸው ከነበሩት መካከል 60 ሰዎችን አጭቆ በፍጥነት ሲከንፍ የነበረ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና
ትከሻ በሚባል ቀበሌ ጀቤሣ ወንዝ ውስጥ ተገልብጦ በመግባት የ59ኙን ሕይወት አጥፍቷል። ትላንት ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሕፃናት በጉዞ
ላይ ታፍነው እንደሞቱ፣ ሁለት አዋቂ ሰዎች ደግሞ በስለት ታርደው እንደተገደሉ የደረሡን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህ መግለጫ
በወጣበት በዛሬው ዕለትም ከ3,000 የማያንሱ ተፈናቃዮች ፍኖተ ሠላም ከተማ (ጎጃም) በሜዳ ላይ ተበትነው በችግር እየተጠበሱ
እንደሆነ ከነፃው ሚዲያ የደረሡን ዘገባዎች ያስረዳሉ።
ይህ ችግር ሥር ሠድዶ እየተባባሰ የሄደውና ወያኔ የልብ ልብ የተሠማው የእኛን ቆርጦ ለመታገል ያለመቻል በመገንዘቡ ነው።
ስለዚህ ይህ ጥሪ የደረሳችሁ የአማራ ወገኖች፤ ከዚህም በላይ ሰብዓዊነት የሚሠማችሁ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤ ቢያንስ
ቢያንስ ለእኒህ ግፉዓን ሕልፈተ-ሞት መታሠቢያ ይሆን ዘንድ በየቤተ-እምነታችሁ በጸሎት እንድታስቧቸው እናሳስባለን። በዋሽንግተን
ዲሲ እና አካባቢው ለምትኖሩት እሑድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. (April 7, 2013) ጠዋት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን የመልአከኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል (DEBRE HAILE KEDUS GABRIE CATHEDRAL ETHIOPIAN
ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH፤ 2601 Evarts St. NE Washington, DC.) ፀሎተ-ፍትኀት ስለሚደረግ በሥፍራው
ተገኝታችሁ የሥነሥርዓቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ የእኒህን ሠማዕታት ነፍስ ይቀበልልን።
ወስብሐተ-እግዚአብሔር።