Saturday, April 20, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ተፈተው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ


የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ተፈተው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢሳት በሰበር ዜናው ካቀረበ በሁዋላ ፣ ሶስቱም አመራሮች ማምሻውን ተለቀዋል።
አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል መንግስት፣ ከክልል መንግስት እና ከዞን ባለስልጣናት ወደ ወረዳው ገብተው ሰዎችን ለማነጋገር የሚችሉበትን የፈቃድ  ወረቀት ይዛችሁ አልመጣችሁም ተብለው መሆኑን ምህረት ተደርጎላቸው ከእስር ተፈተው ወደ አዲስ አበባ በበመለስ ላይ ያሉት ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል::
ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለፈቃድ ሄዶ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ለመነጋገር አይቻልም፣ በዚያ ላይ እናንተ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ናችሁ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ኢ/ር ይልቃል ፣  እንዲህ አይነት ስራ ለመስራት በቅድሚያ ከክልል ፣ ከዞንና ከወረዳ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ፣ ይህን አለማድረግ ደግሞ የብሄረሰቦችን የራስን በራስ የማስተዳደር መብት  መናቅ ተደርጎ እንደሚታይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። ኢ/ር ይልቃል ከሚመለከታቸው አካላት ህጋዊ ፈቃድ መያዛቸውን ገልጸው ዋናው አላማቸው ጉዳቸው እንዳይወጣ በመፍራት መሆኑን ገልጸዋል።
አንዳንድ ሰዎችን በማናገር ያዘጋጁት ቪዲዮ በወረዳው ባለስልጣናት ትእዛዝ እንዲደመሰስ መደረጉን ኢንጂነሩ ተናግረው ይሁን እንጅ በአይናቸው ያዩት፣ በጆሮዋቸው የሰሙት በቂ መረጃ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።
መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ለመሸፋፈን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። የመንግስት ባለስልጣናት የወሰዱት እርምጃ የመንግስት ባለስልጣናትን በአለማቀፍ ፍርድ ቤት በዘር ማጥራት ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን አለማቀፉ የህግ ምሁር ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማርያም መናገራቸው ይታወሳል።

Benishangul Region returnee Amharas suffering from discrimination


ESAT News
Around 8000 Ethiopians of the Amhara ethnic origin, who have been evicted from BenishangulRegion and deported in FinoteSelam and Chagni cities, have said that they are suffering from organized  discrimination as they return back to Benishangul Region though the pressures by Ethiopians across the globe.
 Natives and other residents of the Region have refused to employ the returnees in any kind of job. Some of the returnee farmers that ESAT spoke to said that the Zonal and Woreda officials ofBenishangul Region have lobbied the people not to employ any returnee.
Similarly, expired and contaminated flour that the government gave them to for food has affected many children, mothers and families. Most returnees are now affected by diarrhea and contaminated diseases. To go to the nearest health centre, according to the affected farmers, one has to walk four hours on foot. Some of the farmers said to ESAT that they would prefer to return to where they were deported if they did not to find job.  The farmers state that as they have lost most of their properties already they would not be able to pay for their own transportation this time if they were to go back to their native regions.
Hundreds of children are also out of school, it has been learnt. ESAT’s efforts to speak to Federal government officials were unsuccessful.
Deputy Minister of the Ethiopia Foreign Affairs, Ambassador Birhane Gebrekirstos said in a recent interview with the Amharic Service of the Deutsche Welle (DW) Radio that the citizens were evicted because they “invaded the land illegally”.  The State Minister also responded saying that he had no information if the evictees were again made to return when the journalist mentioned that the Benishangul Regional Government had already admitted that the evictions were “blunders on their side” and allowed them to come back, in a follow up question.

መኢአድ በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ጠየቀ


መኢአድ በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ጠየቀ

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመላው አንድነት ድርጅት ዛሬ በሊቀመንበሩ በኢንጂነር ሀይሉ አማካኝነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህገመንግስቱ በአንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ቢልም የአማራ ህዝብ ሀገርና ትውልድን ለመታደግ በተደረጉ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎች ሁሉ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ እንዳልኖረ ዛሬ በየደረሰበት ቦታ እንደ ውሻ ውጣውጣ እየተባለ ለአመታት ደክሞ ያፈራውን ንብረቱን እና መጠለያ ቤቱን ተነጥቆ መደብደብ፣ መባረር እና መገደል እጣ ፈንታው ሆኗል ብሎአል።
መኢአድ በ አፋር ህዝብ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ሲዘረዝር ደግሞ ” የአፋር ህዝብ ተወልዶ ካደገበት እና ለዘመናት ከኖረበት ቀየው ለራሱም ሆነ ለከብቶቹ ህለውና ወሳኝ ከሆነው የአዋሽ ወንዝ ተፈናቅሎ፣ የእርሳና ግጦሽ መሬቱን ተነጥቆ ጊዜ ለሰጣቸው አምባገነን ባለስልጣናት እና የአነሱ አጫፋሪ ለሆኑ አጊብዳጅ ባለሀብቶች ተሰጥቶበታል” ይላል።
የህዝቡ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከብት እርባታ መሆኑ እየታወቀ ምንም አይነት አማራጭ ሳየቀርብለት ተገቢውን ካሳ ሳይከፈለው የታጠቀ ሀይል በማሰማራት ህጋዊ መብቶቹ ተገፈው በቆ ውሀ በሌለባቸው አካባቢዎች እንዲሰፍር በመደረጉ ህዝቡ ለከፋ ረሀብ ሲጋለጥ ከብቶቹም በድርቅ እያለቁ ነው የሚለው መኢአድ ፣ አሳኢታ ውስጥ ከእነ ስድስት ህጻን ልጆቻቸው የታሰሩት እና በስቃይ ላይ የሚገኙት ወ/ሮ ሀሲና ሀመሩን በምሳሌነት ጠቅሷል።
መኢአድ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ ስለደረሰው ችግር ሲዘረዝር ደግሞ ” ከመጋቢት ወር 2005 ዓም ጀምሮ ከአሶሳ ዞን ባምቢስ ወረዳ 2 ሺ፣ ከከማሺ ዞን ያሶ ወረዳ ከ8 ሺ በላይ እንዲሁም ከቡለን ወረዳ ከ5 ሺ በላይ እንዲሁም ከሌሎች ወረዳዎች በብዙሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ተባረዋል ብሎአል።
በባምቢስ ወረዳ የከተማው ህዝብ ለአማራ ቤቱን እንዳያከራይ ፣ በሆቴሉ አማራ እንዳይስተናገድ ትእዛዝ መሰጠቱን፣ የአካባቢው ተወላጆችም መሬታቸውን ለአማራ እንዳያከራዩ ጥብቅ መመሪያ መተላለፉን ድርጅቱ አስታውሷል።
የክልሉን አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ናስርን ጨምሮ ሌሎች የህወሀት አመራሮችን ተጠያቂ ያደረገው መኢአድ ፣ ሰዎቹ ወደ መጡበት ቦታ እንዲመለሱ የተደረገው በመላው አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የደረሰባቸውን ተቃውሞ በማርገብ  ለማዘናጋት እንጅ አማራን ከእየአካባቢው የማጽዳቱን የቆየ እቅዳቸውን ተግባራዊ ከማድረግ አይመለሱም ብሎአል መኢአድ።
መኢአድ በመጨረሻም እንዲመለሱ ለተደረጉት ወገኖች የህግ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ ለደረሰባቸው አካላዊና ሞራላዊ ጥቃት ተገቢውን ካሳ እንዲከፈላቸው፣ ድርጊቱን የፈጸሙት ለህግ እንዲቀርቡ፣ ጥላቻንና ክፍፍልን የሚያራግቡ ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እንዲሁም ህዝብን በዘርና በሀይማኖት በመከፋፈል የስልጣን እድሜን ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ላለፉት 21 አመታት ደም ያፋሰሰ በመሆኑ በአስቸካይ እንዲቆም ጠይቋል።
የአማራውን ህዝብ እንወክላለን የሚለው ብአዴን እስካሁን አንድም ቃል አልተነፈሰም። ኢሳት የብአዴን ባለስልጣናትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ፣ አመራሮቹ  ለምሳ ወጥተዋል፣ ስብሰባ ላይ ናቸው፣ ከእንግዳ ጋር ናቸው ፣ የሻሂ ረፍት ላይ ናቸው” በሚሉ ምክንያቶችን ሊሳካለት አልቻለም።
በሰለጠኑት አገራት በአንድ ዜጋ ላይ ጥቃት ሲደርስ መሪዎች ጉብኝታቸውን በመሰረዝ ከህዝባቸው ጋር እንደሚቆሙ ቢታወቅም፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር ሀይለማርያም ደሳለኝ 10 ሺ ህዝብ በተፈናቀለበትና ህጻናት እና እናቶች እንደቅጠል መርገፋቸው በተነገረበት እለት የውጭ ጉብኝት ለማድረግ መነሳታቸው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያንን ማበሳጨቱን ለኢሳት የሚደርሱት መልእክቶች ያሳያሉ።