Sunday, August 11, 2013

ስንቅና ውሸታም እያደር ይቀላል!

 ፈቃዱ ለሜሣ (ፕሮፌሰር)

በኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የሚሠነዘሩ የፈጠራ ወሬዎችና ተጨባጩ ሃቅ

(ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል - በቅርቡ በእንግሊዝኛ ተጽፎ በኢትዮሚድያ ታትሞ የነበረው የፕሮፎሰር ፈቃዱ ለሜሳ ጽሁፍ በአማርኛ ተጽፎ
ቀርቧል። በከፍተኛ ጥንቃቄ የተረጎሙት የዘወትር አምደኛችን ይነጋል በላቸው ናቸው። ልባዊ ምስጋናችንን በአንባቢያን ስም እናቀርባለን!)

ማሳሰቢያ፡- አሁን እዚህ ያቀረብኩት የትርጉም ሥራ ከወቅቱ የፖለቲካ ንፋስ አኳያ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን አውቃለሁ፡፡
በቃላት የምንዛሬ ትርጉም ዜጎች እየተላለቁ በሚገኙባት ሆደባሻ ዓለም ውስጥ ይህን መሰሉን ጉዳይ በቀላሉ መተርጎም
እንደማይቻል እረዳለሁና ማንኛውም ዓይነት በዋናው ጽሑፍ ላይ ያልተጠቀሰ ሃሳብ በዚህ ትርጉም ውስጥ በስህተት ቢገኝ ኃላፊነቱ
ፕሮፌሰሩ ሣይሆን የኔ የተርጓሚው መሆኑን ለአንባቢያንና ለፕሮፌሰር ፈቃዱ ከታላቅ ይቅርታ ጋር በትህትና እገልጻለሁ፡፡ በተቻለኝ
መጠን የዋናው የእንግሊዝኛ ጽሑፍ ወዘና እንዳይጠፋ ጥረት አድርጌያለሁ - የኔ የራሴ ሥነ ልሣናዊ ‹የተፈጥሮ ለዛ›ም እንዳይከፋብኝ
ከሚል ቅን አስተሳሰብ በመነሣት የተጠጋጋ ግን ከዋናው እምብዝም የማያፈነግጥ ‹ኮዝሞቲክስ› እጅግ አልፎ አልፎ በጣም በስሱ ፈንጠቅ
ለማድረግ ሞክሬያለሁ - ለዚህ ደግሞ ፕሮፌሰርን በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ - እንዲህ የማደርገው እንግሊዝኛው ወዳማርኛ ሲመለስ
ድርቅ እንዳይልብኝና መሸጋገሪያ ድልድዩ ቢጠናከር ትርጉሙ ይበልጥ እንደሚያምር ሳምንበት ነው ፤ ለማንኛውም ግን ሰው ነኝና ብሳሳት
በቀናነት እዩልኝ እንጂ ልፋቴን በሚያጣጥል የከፋ ደረጃ እንዳታብጠለጥሉኝ አደራ እላለሁ፡፡ ዛሬም መልካም ንባብ፡፡
(ኦሮሞዎችንና የኢትዮጵያን ታሪክ በሚመለከት ዳሰሳ ለሚያደርጉ የውጭ ጋዜጠኞች የመነሻ ግንዛቤ መጨበጫ ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀ) ኦሮሞና
ኢትዮጵያ፤ ምሥጋና ለ: ayyaantuu.com ድረ ገጽ)
(ናዝሬት፣ ኢትዮጵያ) - መሠረቱን ኳታር ያደረገው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ኦሮሞዎችን በሚመለከት በርካታ ዝግጅቶችን በቅርቡ አየር
ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡ የሕዝባችንን ገጽታ በመሰለው መልክ ለዓለም ማኅበረሰብ በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ ይህ የሚዲያ ተቋም
የመጀመሪያው በመሆኑና እያደረገ ያለውም አስተዋጽዖ ቀላል ባለመሆኑ ሊወደስ ይገባዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ ሕዝብን የማስተዋወቅ ሥራ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ውስጥ አንደኛው፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በነሱና በተከታዮቻቸው
አማካይነት በሕዝቡ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ግፍና በደል እንዲሁም የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የሚከታተል ገለልተኛ ወገን መኖሩን ተገንዝበው
የሚያካሂዷቸውን የሰብኣዊ መብት ረገጣዎች በቀላሉ እንዳይመለከቱ ማስገደዱና በዚያም ሳቢያ እነኚሁ ባለሥልጣናት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ
የወቅት ሁኔታ የዓለም ሕዝብ በግልጽ እየተከታተለው መሆኑን እንዲያውቁት ማስቻሉ ነው፡፡ ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው
ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው መከበር ላለፉት በርካታ አሠርት ዓመታትና አሁንም ድረስ ሲታገሉ ቆይተዋል፡፡ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጥንተ
አመጣጥና ታሪካዊ ዳራ የመዘገቡ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ይህ ሲደረግ ግን በትክክል መዘገብ እንደሚኖርበት መረዳት
ለማንኛውም ወገን ጠቀሜታ አለው፡፡ ትክክለኛ ያልሆነና የተጣመመ መረጃን ወይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ አንድ ወገን የሚያጋድል ዘገባን
ማቅረቡ ለዴሞክራሲ የምናደርገውን ሁለንተናዊ ትግል ይጎዳብናልና ከዚህ መሠረታዊ ነጥብ አንጻር ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡
ይህ የተንሻፈፈ አካሄድ ብሔራዊ መግባባትንና ሰላምን ከመፍጠር ይልቅ ቁጣንና አንዱ ባንዱ ላይ መንገፍገፍን እያስከተለ ቅራኔን ያባብሳል፡፡
በቅርቡ አልጀዚራ ትክክል ያልሆነ ወይም የተሳሳተ ዘገባ እንዲያርቀብ ከተገደደበት ምክንያቶች አንደኛው የመረጃ ምንጩ ግራና ቀኙን
ያማከለ ሣይሆን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማለትም በአብዛኛው በዉጭ የሚንቀሳቀሱ ኦነግንና ኦ.ኤፍ.ዲ.ኤምን የመሳሰሉ የኦሮሞ ድርጅቶች መሆናቸው
ነው፡፡ በዚህ ግን አልጀዚራ ብዙም ሊወቀስ አይገባውም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ትክክለኛውን መረጃ የሚያውቁ ሰዎች ወይም ድርጅቶች
የሚያውቁትን እውነት ቢናገሩ የሚደርስባቸውን ያውቃሉና ለደኅንነታቸው ይሰጋሉ፡፡ ስለዚህም አልጀዚራን የመሳሰሉ የውጪ የመገናኛ ብዙኃን
የተሻለ አማራጭ ሲያጡ በመረጃ ምንጭነት ለመጠቀም የሚገደዱት በውጭ ሀገራት በስደትና በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ
እንቅስቃሴዎች ላይ ተሠማርተው የሚገኙ ሰዎችን ወይም ቡድኖችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የሦስተኛው ዓለም ሀገራትን ሁኔታ
መዘገብ ለሚፈልጉ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ የውጭ የመረጃ ተቋማት ትልቁ የራስ ምታት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ወገን የሚያገኙትን መረጃ
ሊያረጋግጡ የሚችሉባቸው የሀገር ውስጥ በሮችና መስኮቶች በሚዲያ አፋኝ አምባገነን መንግሥታት ስለሚዘጉባቸው በአብዛኛው ያልተረጋገጠና
የአንድ ወገን መረጃ ለመዘገብ ይገደዳሉና፡፡
ለዛሬው ለመማማር ያህል እንዲጠቅመን ሰሞኑን አልጀዚራ በኦሮሞ ሕዝብ ታሪክና ለዴምከራሲያዊ መብቶቻችን መከበር በምናደርገው
ትግል ዙሪያ ያስተላለፋቸውን ዘገባዎች በሚመለከት መታረም የሚገባቸው ዋና ዋና ህፀፆችና እውነትነት ጨርሶውን የሚጎድላቸው አሳሳች ጉዳዮች
ስላሉ በነዚያ ላይ አንዳንድ የማስተካከያ ነጥቦችን ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡ የሚከተሉት የማስተካከያ ሃሳቦች ከፖለቲካዊ አስተሳሰብ በጸዱ ሃቀኛ
ምሁራን የሚደገፉ ቢሆኑም በፖለቲካ ጠበል የተጠመቁ የማንኛውም ጎራ ‹ምሁራን› ግን ላይደገፏቸው ወይም ተቀባይነት ሊያሳጧቸው ይችላሉ፡፡
ይሁንና እነዚህን ሃቆች ማንም ይገፍትራቸው ወይም ይቀበላቸው ዋናው ጉዳይ እውነታዎቹ ስሜት ወለድ ሳይሆኑ የታሪክ መዛግብትን፣ የአውሮፓ
ተመራማሪዎች የደከሙባቸው የታሪክ መጻሕፍትንና በዕውቅ ምሁራን የተዘገቡ የታሪክ ማስታወሻዎችን መሠረትና ዋቢ ያደረጉ በመሆናቸው
የትኛውም ወገን ሊጠራጠራቸው አይገባም፡፡
ልቦለድ ቁጥር አንድ:-
“ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1868 እስከ 1900 ከጠቅላላው የኦሮሞ ሕዝብ መካከል ግማሹ የሚሆነውና ወደ አምስት ሚሊዮን
አካባቢ የሚገመተው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ [በሀበሾች ንጉሥ በአጤ ምኒልክ ጦር]ተገደለ፡፡”
ሃቅ ቁጥር አንድ፡-ይህ መነሻና መድረሻ የሌለው ተራ አሉቧልታ እንጂ እውነት አይደለም፡፡ ይህንና ሌላም ይህን መሰል መሠረተቢስ ወሬ ተደጋግሞ የሚነገረውና
እንደማለፊያ ዜማ ዘወትር የሚቀነቀነው በአብዛኛው የኦሮሞን መገንጠል በሚደግፉና ዓላማውንም በሚያራምዱ ‹ተምረናል› በሚሉ የተወሰኑ
የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ውጪ ባሉ አክራሪ የጎሣ ፖለቲካ አቀንቃኞች እንዲሁም ‹gadaa.com›ን በመሳሰሉ የኦነግ ደጋፊ ድረ ገፆች
አማካይነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን እነዚህ ወገኖች በዚያን ዘመን የተገደለው የኦሮሞ ቁጥር አምስት ሚሊዮን ማለታቸው የቁጥር ዕውቀታቸው ዜሮ
መሆኑን ከማመልከቱ ባሻገር የሚያስተላልፈው መልእክት ሚዛን የሚያነሳ እንዳልሆነ ታሪክንና የሕዝብ ብዛት ዕድገትን የሚያውቅ ይረዳዋል፡፡ በዚያን
የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ 90 የሚደርሰውን የኢትዮጵያን ዘውጎች ሁሉንም ሥሌት ውስጥ ባካተተ የሕዝብ ቆጠራ ጠቅላላው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ሚሊዮንም በጣሙን የሚያንስ እንደነበር በታሪክ መጻሕፍት ሠፍሮ ይገኛል፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ
ከዘጠናው ዘውግ ውስጥ የኦሮሞው ማኅበረሰብ ብቻ ተነጥሎ “10 ሚሊዮን ይደርስ ነበር፤ ከዚያም ውስጥ አምስቱ ሚሊዮኑ በ‹ጨካኝ ንጉሥ
ተጨፍጭፎ› ተገደለ” ማለቱ በራሱ የጤናማነት ጉድለት እንጂ አንድም ተጠየቃዊ አመክንዮ የለውም፡፡ ለመዋሸት ደግሞ ይህን ያህል ረጂም ርቀት
መሄድ ለምን እንዳስፈለገ ለማንም ግልጽ አይመስልም፡፡ ስለዚህ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ጦር ተገደሉ የሚለው የተሳሳተ መረጃ
የማንንም ቀልብ የማይስብና የትኛውንም ዓላማ ለማራመድ የማያገለግል ተራ የፈጠራ ወሬ ነው፡፡ እውነቱ ግን በዚያን ዘመን በተቀሰቀሱ የገብር
አልገብርም የርስ በርስ ግጭቶችና ጦርነቶች ሳቢያ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውን - በሁለቱም ጎራዎች - ለሕልፈት
መዳረጋቸው ነው፡፡ አንዳንድ ፖለቲከኞች ለራሳቸው ጠባብ አጀንዳ ሲሉ የዚያን ጊዜውን ዕልቂት ‹ጄኖሣይድ› እንደሆነ ቢፈርጁም እውነቱ ግን ሌላ
ነው፡፡ እውነቱ ታዲያ የጄኖሣይድ ሣይሆን በዘመኑ በአውሮፓ መሣሪያና በሰለጠነ የሰው ኃይል ተደራጅቶ የነበረው በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ
የሚታዘዘው የሸዋ ጦር በኋላቀር መሣሪያና ካለበቂ የጦር ልምድና ሥልጠና ለጦርነት ከተሰለፈው የደቡቡ ኃይል ጋር በተፈጠረ የኃይል ሚዛን
መበላለጥ ምክንያት በተከሰተው ግጭት በተለይ በደቡቡ በኩል ብዙ ወገን ማለቁ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ባልተመጣጠኑ ኃይሎች መካከል የተከሰተን
ጦርነት ወይም ግጭት ያመለክታል እንጂ አንድ የታጠቀ ዘመናዊ ጦር ለልዩ ተልእኮ ወደ አንድ መንደር ወይም ቀየ ገብቶ ባዶ እጃቸውን በቤታቸው
የተቀመጡ ንጹሓን ዜጎች እንደፈጀ በማስመሰል የዚያን ጊዜውን የርስር በርስ ውጊያ ወደ‹ጄኖሳይድ›ነት ለውጦ የተለዬ ስዕል መፍጠር ተገቢ
አይደለም ብቻ ሣይሆን ጥፋት ነው፡፡ ታሪካዊ እውነቱ የዚያን ዓይነት መልክና ቅርጽ የነበረው አይደለም፡፡ እንዲያውም በነዚያ ያለፉ የመከራ
ዓመታት ኦሮሞ ባልሆኑ ሰዎች ከተገደሉ ኦሮሞዎች ይልቅ በኦሮሞዎች የተገደሉ ኦሮሞዎች ቁጥር በጣም ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም በኦሮሞ የተለያዩ
ነገዶች ውስጥ በሀብትም ይሁን በአስተዳደር የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክርና መቀናቀን ስለነበር ከጎረቤቶቻቸው ኦሮሞዎችና ከሲዳማዎችም
የነበራቸውን ሽኩቻ በጠረጴዛ ዙሪያ የቃላት ድርድር ሳይሆን አንዱ አንዱን በኃይል በመጨፍለቅ የበላይነቱን ለማረጋገጥ ሲል በጦር መሣሪያ
ይፋለሙ ስለነበር ነው፡፡የዚያ ዓይነቱ ወንድም በወንድሙ ላይ ‹የሚቀዳጀው› ግንጥል ጌጣዊ ድል ደግሞ በአፍሪካ የመጀመሪያው እንዳልሆነና
የተፈጥሮ ሀብትንም ይሁን ሌላ ጥቅም የሚያስገኝን ነገር ለመቀራመት ሲባል በሚደረግ ፍልሚያ በሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎችና ነገዶች መካከልም
የከረሩ ግጭቶች ይካሄዱ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፤ ስለሆነም በደቡቡ ይበልጡን ኦሮምኛ ተናጋሪ በነበረው ማኅበረሰብና በሸዋው ባመዛኙ
አማርኛ ይናገር በነበረው የአንዲት ሀገር ዜጎች መካከል የታዩ ግጭቶችን በሀገሪቱም ሆነ በሌላው ዓለም እንዳልታዩ ልዩ ተዓምሮች በመቁጠር ይህን
ያህል ግዘፍ ነስተው መራገባቸው ማንንም ስለማይጠቅም እውነቱን ከእውነተኛ ምንጮች መረዳት አይከፋምና በተለይ በዚህ ቅንነት በሚጎድለውና
የተንኮል ሤራ በተሸረበበት የጥፋት ጎዳና የሚራመዱ ወገኖች በአፋጣኝ ወደቀናው መንገድ በጊዜ እንዲመለሱ ይመከራሉ፡፡ ይህን ሃሳብ ጠቅለል
ለማድረግ፣ የጂማ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ጳውሎስ መንግሥቱ የቀኝ ክንፍ የኦሮሞ ነጻነት ጎራን ፍልስፍና በሚመለከት ውብ በሆነ አገላለጽ በጽሑፍ
ካስቀመጡት ሀተታ ውስጥ የሚከተለውን ቀንጨብ አድርገን እንመለክት፡-
የኦሮሞን ማኅበረሰብ ታሪክ በሚመለከት ሆን ተብለው ተንሻፍፈው የተጻፉ ወይም የሚነገሩ በርካታ የፈጠራ
ድርሰቶችና ልቦለዶች አሉ፡፡ እነዚህ በሬ ወለደ ዓይነት አሉታዊ ጥላ ያነገቡ የውሸት ታሪኮችን በጭፍን ተቀብለውና እውነት
እንደሆኑ አምነው በጭፍን የሚጓዙ ወገኖችም ሞልተዋል፡፡ የፖለቲካ ኪሣራ ያጋጠማቸውና ወደጎን የተተው እንደኦነጉ አሰፋ
ጃለታን የመሰሉ አስመሳይ ‹የታሪክ ተመራማሪዎች›ና ‹ጸሐፊዎች› በቤተ ሙከራዎቻቸው የፈበረኳቸው እነዚህ የሀሰት ወሬዎች
የየዋሃንን ቀልብ በመሳብና በማሳሳት ረገድ የተጫወቱትና እየተጫወቱ ያሉት አሉታዊ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህ በስም
የተጠቀሰ ግለሰብ በተለይ፣ አንድን ነገር ሆን ብሎ በማጣመም ለራሱ በሚያመቸው መልክ በመጥቀስና ቃላትን ወይም
አባባሎችን ከቆሙለት ዐውዳዊ ፍቺ ሌላ ያልተፈለገ ትርጉም በማሸከም ሰውን የሚያወናብድ አሳሳች ሰው ነው፡፡ አንድ ምሳሌ
ወስደን እንይ፤ አሌክሳንደር ቡላቶቪች የተባለ የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሩሲያዊ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ተከሰተ ባለው
በሽታና ርሀብ እንዲሁም በኦሮሞ ጎሣዎች መካከል ተካሄደ የተባለን ግጭት ጨምሮ ኦሮሞዎች ከሌሎች የሀገሪቱ ጎሣዎች
በተለይም ከአማራው ጋር አካሂደዋል በሚላቸው ጦርነቶች ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ በግማሽ እንዳለቀ ‹ምሁራዊ
ግምቱ›ን ሰጥቶ ነበር፡፡ አጅሬ አሰፋ ጃለታ ይህን ዘገባ ካነበበ በኋላ ከአንድ ጤናማ ሰው በጭራሽ በማይጠበቅ ሁኔታ አጣምሞ
በመተርጎም “ግማሹ የኦሮሞ ሕዝብ በ‹ክፉዎቹ› አማራዎች ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡” በማለት በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የግል ፈጠራ
ድርሰቱን ሰንቅሯል፡፡ ይህ ተራ ነገር አይደለም፤ የአንዲት ሀገር ዜጎችን ጥርስ ለማናከስ በተንኮል የታቀደ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡
በዚህ ደግሞ ማንም አይጠቀምም፡፡ ይህ የልቦለድ ታሪክ በአቶ ጃለታ የተፈለሰፈው ኦሮሞና አማራን በማጣላት ይገኛል ተብሎ
የሚገመትን የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ የጎሣ ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡ ከመነሻው ሚስተር ቡላቶቪችም ቢሆን
ያን በአኀዛዊ ግምት ያስቀመጠውን የኢትዮጵያውያን ዕልቂት ሊደርስበት የሚያስቸለው አንዳችም የሕግ ድጋፍም ሆነ በግሉ
የሚታወቅባቸው አቅምና ችሎታ የነበሩት ሰው አልነበረም፡፡ በሁለተኛም ያ ሰው የኦሮሞው ማኅበረሰብ ይኖርባቸው በነበሩ
የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዝኆንና ሌሎች የዱር እንስሳትን እያደነ በዛ ቢባል ለሁለት ወራት ያህል ብቻ ተዘዋወረ እንጂ ያን ከፍተኛ
ወጪና የተማረ የሰው ኃይል የሚፈልግ የሕዝብ ቆጠራና የዕልቂት መንስኤ ጥናት ለማካሄድ የሚያስቸለው መደላድል በነዚያን
በ1990ዎቹ ዓመታት ውስጥ ፈጽሞውን ሊኖረው አይችልም፡፡
ልቦለድ ቁጥር ሁለት፡-
“… አብዛኛው ሙስሊም የኦሮሞ ሕዝብ”
ሃቅ ቁጥር ሁለት፡-
ይህ ሐረግ በጥቂት የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዘወትር ባይሆንም ካለፍ ካገደም የሚስተዋል ነው፡፡ በመሠረቱ በኦሮሞ ሃይማኖታዊ ታሪክ ከጥንት
እስከዛሬ መቼም ቢሆን ‹አብዛኛው ሕዝብ እስልምናን ተከታይ ነው› የሚባል ሕዝብ ሆኖ አያውቅም፡፡ እንደእውነቱ ክርስትናም ሆነ እስልምና ከጊዜበኋላ የመጡ እንጂ የአያት የቅድመ አያት ጥንታዊ ሃይማኖቶቻችን አይደሉም፡፡ ለምዕተ ዓመታት ስንከተላቸው የነበሩና በትውልድ ሲወራረሱ የቆዩ
ሀገር በቀል ባህላዊ እምነቶች ነበሩን፡፡ (አሁንም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡) ቀስ በቀስ ግን በተለይ የኦሮሞ መስፋፋት በተጋጋለባቸው ዓመታት እነዚህ ሁለቱ
እምነቶች ወደኦሮሞው ሕዝብ ይበልጥ እየሠረጉ ገቡ፡፡ ሥርገቱም በፈቃዳችንና በተፅዕኖም እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት እንረዳለን፡፡ በፈቃዳችን
የሆነው እኛ በሰላምም ሆነ በጦርነት መልክ በሄድንባቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ ከነበረው የክርስቲያን ወይም የሙስሊም ሕዝብ ጋር ስንዋሃድ
ሲሆን በተፅዕኖ የሆነው እነዚሁ ኃይሎች የኛን ግዛቶች በሚወርሩ ጊዜ በሚያሳድሩት ተፅዕኖ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ያን ክስተት አሁን የኋሊት ዞረን
ስናየው ጉዳዩ የሁለትዮሽ እንጂ በብቸኝነት አንደኛው ሃይማኖት በሌላኛው ላይ የበላይነትን የሚጭንበት ሁኔታ ስላልነበረ አንዱ ከአንዱ ጎልቶ
የወጣበትና የኦሮሞን ሃይማኖታዊ ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይበት ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ በዚህ ረገድ አሁን እንኳን ብናይ በኦሮሞ ማኅበረሰብ
ውስጥ ያለው የሁለቱ ሃይማኖቶች የተከታይ ብዛት ተካካይ እንጂ ያን ያህል አፍን ሞልቶ ሊያናግር የሚያስችል የቁጥር መበላለጥ የላቸውም፡፡
(የመጨረሻው የ2000 ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ እንደሚያሳየው 48 በመቶ የሚሆነው ኦሮሞ የ(ማንኛውም ዘርፍ) ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን
47 በመቶው ደግሞ ሙስሊም ነው፡፡ እንደሚባለው ከሆነ ግን የእስልምና ሃይማት ተከታዩ ቁጥር በፍጥነት እያደገና በአንጻሩም የክርስትና ሃይማኖት
እየጫጫ በመሄድ ላይ ያለ በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኦሮሞዎች ዘንድ የሙስሊም ማኅበረሰብ ቁጥር ከክርስቲያኑ ሊበልጥ እንደሚችል ከፍተኛ
ግምት ተሰጥቶታል፡፡
ልቦለድ ቁጥር ሦስት፡-
“ሀበሾች ኦሮሞዎችን ለማንቋሸሽ አሉታዊ ትርጉም ባዘለ ቃል ‹ጋላ› እያሉ ይጠሯቸዋል፡፡”
ሃቅ ቁጥር ሦስት፡-
ይህን እብለትና ቅጥፈት የተሞላበትን የፈጠራ አባባል የሚጠቀሙበት ከፍ ሲል የተጠቀሱት መገንጠልን የሚያራምዱ የኦሮሞ ኤሊቶችና
አጫፋሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ይህን የሚያደርጉት በአባባሉ እውነትነት አምነው ሣይሆን በኦሮሞው ውስጥ የመረረ ስሜት ለመፍጠርና ሕዝቡ ሴማዊ
ሀበሾችን(አማሮችን፣ ትግሬዎችንና ጉራጌዎችን) ፈጽሞ እንዲጠላ ለማድረግ ነው፡፡ ይህን በማድረጋቸው ቅራኔውን ያከረሩና በአቋራጭ የመገንጠል
ዓላማቸውን ያሣኩ ይመስላቸዋል፡፡ የዚህ ቃል ጥንተ አመጣጥና ትርጉሙ ግን እንደዚህ ነው፡- ይህ አንቋሻሽ የሚመስል ‹ጋላ› የሚባል ቃል
ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በዐረቦችና በሙስሊም ሶማሌዎች ሲሆን ኦሮሞዎችን ‹ጋል› በማለት መጥራታቸው በቃሉ ትርጉም መሠረት
ኦሮሞዎች ‹ሃይማኖት የሌላቸው›ና ከነሱ የተለዩ ‹ባዕዳን› መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ሙስሊሞች በዚህ ቃል
ኦሮሞዎችን መጥራት የፈለጉት ኦሮሞዎች የነበራቸው ባህላዊ ሃይማኖት/እምነት ከተለመደው የእስልምና ወይም የክርስትና ሃይማኖቶች የሚያፈነግጥ
ሆኖ ስላገኙትና ያንንም በግዑዝ ነገሮች እንደማምለክ ወይም ከነአካቴው እንደሃይማኖት የለሽነት ስለቆጠሩት ነበር ተብሎ ይገመታል፡፡ እየቆዬ ግን
ይህ አሉታዊ ፍቺ እንዲይዝ ጫና የተደረገበት ‹ጋላ› የሚል ቃል የኦሮሞን ማኅበረሰብ አባላት በቡድንም ይሁን በተናጠል ለመጥራት ሌሎች
ኢትዮጵያውያንም ይጠቀሙበት ጀመር፡፡
ልቦለድ ቁጥር አራት፡-
“(በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ) ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወደቁ፡፡”
ሃቅ ቁጥር አራት፡-
የኦሮሞ ተገንጣይ ቡድኖች ከሚያናፍሷቸውና አንዳንድ የውጭ ጋዜጠኞችም በጭፍን ተቀብለው በተደጋጋሚ ከሚያራግቡላቸው የፈጠራ ወሬዎች
መካከል አንደኛው አንድ ኢትዮጵያዊ ዘውግ (አማራ) ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዘውግ (ኦሮሞን)በቅኝ ግዛት ሥር አስገብቷል የሚለው አስቂኝ ድራማ
ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ብዙውን ጊዜ “ሀበሾች ኦሮሞዎችን በቅኝ ግዛት ያዙ” ወዘተ. እየተባለ እንደመፈክር ይስተጋባል፡፡ ይህ የቅኝ ግዛት ነገር በኦነግና
በመሰል የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲሁም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት በሚገኙ የኦሮሞን ብሔርተኝነት አቀንቃኞች ዘንድ እንደእውነት ተወስዶ ለትግል
ማነሳሻነትና ማነቃቂያነት ሲባል በስፋት ይወሳል፤ በሕዝብ ውስጥም ውስጥ ውስጡን ይሰበካል፡፡ በተለዬ አገላለጽና የዕይታ አቅጣጫ ሊታይ
በሚችል መልኩ ይህ አንዱ ሌላውን ለመቆጣጠር የመሻትና የመሞከርም ሁኔታ ጨርሶውን ሊካድ ባይችልም … እንደአጠቃላይ ግን የኦሮሞ ብሔር
መቼም ቢሆን በሌላ (የኢትዮጵያ) ዘውግ ቅኝ ተገዝቶ አያውቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ወሬ ሰሚን ሣይቀር ግራ የሚያጋባ ተራ ወሬ እንጂ ቅንጣት
እውነትነት የለውም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሌላው ቀርቶ አንድ የተባበረ የኦሮሞ ብሔር፣ ተለይቶ ከሚታወቅ አንድ ወጥ የኦሮሞ ግዛት ጋር በነዚያ ሩቅ
ጊዜያት አልነበረም፡፡ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሌለባቸው የታሪክ መጻሕፍት ሁሉ የሚመሰክሩት አንድ እውነት አለ፡፡ ያም እውነት በኢትዮጵያ ውስጥ
በሚገኙ ቋንቋቸው አንድ በሆነ ነገር ግን የተለያዩ የጎሣ/የነገድ ስብጥር ባላቸው ማኅበረሰቦች መካከል ለዘመናት ጦርነቶች መካሄዳቸው ነው፡፡
በልማዳዊ አነጋገር የ“ሀበሾች” ሥፍራዎች ናቸው በሚባሉ የሰሜን ኢትዮጵያ ብዙ ቦታዎች ሳይቀር ኦሮሞዎች በመስፋፋት ከትግሬዎች፣ ከአማራዎች፣
ከአፋሮችና ከሌሎችም የክልሉ ነዋሪዎች ጋር በመቀላቀላቸውና በመዋሃዳቸው ይህ በአንዳንድ የዋሃን “የሀበሾች ምድር” እየተባለ አላግባብ የሚጠራው
የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ራሱ የአንዱ ወይም የሌላው ብሔር ወይም ዘውግ ብቸኛ መኖሪያ ሣይሆን የሁሉም እንደሆነ በታሪክ ምሁራን ዘንድ
ይታመናል፡፡ እርግጥ ነው በ1700ዎቹ ገደማ ራያ ኦሮሞዎችና የጁ ኦሮሞዎች የተወሰኑ የትግሬና የአማራ ግዛቶችን ተቆጣጥረው በነበረበት ጊዜ
ለተወሰኑ ዓመታት የኢትዮጵያን ኦፊሴል ቋንቋ ኦሮምኛ አድርገው እንደነበር ከታሪክ ማኅደር መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህም ማለት በኢትዮጵያ የተለያየ
ቋንቋና ባህል ያላቸው ጎሣዎችና ነገዶች እየተፈራረቁ ሥልጣን ይናጠቁ እንደነበረና በታሪክ ግምዶሽ እየተቆራኙ እርስ በርስ እንደተዋሃዱ፣ በዚህ
ሂደትም ይበልጥ ጉልበተኛ የነበረው ዘውግ ለአገዛዝ አመቺ ነው ብሎ የሚያስበውን ቋንቋም (ሆነ ባህል) በሌሎች ላይ ይጭን እንደነበር መረዳት
አይቸግርም፡፡ የዚያን ዘመኑ የአንድ ቋንቋ የበላይነት ግን እንደዛሬው ዘመን አጨቃጫቂና ከመጠን በላይ በተለጠጡ የቅራኔና ቁርሾ መዘዞች የታጨቀ
አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በንግድም ሆነ በሌላ ሥራ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ የነበሩ ዜጎች ለሥራቸው ስኬት ሲሉ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ የሌሎች ጎሣዎችን ቋንቋዎች ይናገሩ ስለነበርና ቋንቋን ማወቅም ከግል ጥቅም ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ በዚያን ዘመን ይስተዋል የነበረው ሥነ
ልሣናዊ ችግር እንዳሁኑ በፖለቲካዊ አስተሳሰቦች የተንኮል ድርና ማግ የተሸመነ አልነበረምና ያን ያህል ጎልቶ የሚታይ ለታሪክ መዝገብ ፍጆታም
የሚበቃ ቋንቋ ነክ ችግር አልነበረም፡፡ ይህ እንግዲህ ኦሮሞ የሠፈረበትን ግዛት የሚጠቁመን የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩም የሚያሳየን ኦሮሞ
ያልተዳረሰበት ኢትዮጵያዊ ሥፍራ እንደሌለና ነገር ግን በየሄደበት ባህልና ቋንቋ እየተዋጠ ከሁሉም ጋር እንደሰም ቀልጦ አንድ መሆኑን ነው፡፡ወደኋለኛው የአፄ ምኒልክ ዘመን ስንመጣ እንግዲህ የሚስተዋል አንድ ሃቅ መኖሩን እንረዳለን፡፡ ይሄውም ብዙዎች የታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍት
እንደሚከራከሩበትና አሳማኝም ነው ብለው በርካቶች እንደሚቀበሉት ጉዳዩ የአማራና የኦሮሞ ዝርያ ወይም የደም ትስስር ሣይሆን አማርኛን በዋናነት
የሚናገር ማኅበረሰብ ኦሮምኛን በዋናነት የሚናገርን ማኅበረሰብ በጊዜ ሂደት ሊያሸንፍ የመቻሉ ታሪካዊ አጋጣሚ መከሰቱ ነው፡፡ ይህ ሲሆን አማርኛን
በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥ ኦሮሞ አለ፤ ኦሮምኛን በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥም አማራ አለ ማለት ነውና ትግሉ ይበልጡን የኢኮኖሚና
የሥልጣን እንጂ የዘርና የቋንቋ አለመሆኑን ልብ ይሏል፤ እርግጥ ነው ግጭቶች ሁሉ የሀሰትም ይሁን የእውነት አንዳች የሚነገርላቸው ምክንያት
ስለሚያስፈልጋቸው በሁሉም ወገን የሚነገሩ ግን እውነት ውሸትነታቸው ሊጣራ የሚገቡ ሰበበ-ድርጊቶች መኖራቸው የሚካድ አይደለም፡፡ ጥንቃቄ
የሚያስፈልገው እንግዲህ በነዚህ ዓይነቶቹ የኋላ ዳፋ ሊኖራቸው በሚችል ጠንቀኛ ንግግሮችና ሰብቆች ላይ ነው፤ ምክንያቱም ‹አንድ ወሬኛ
ያባረረውን ሺ ጦረኛ አይመልሰውም› እንዲሉ ተጣሞ የተነዛን ወሬ ለማቃናት አስቸጋሪ ከመሆኑም በተጨማሪ ወሬው እየተበጠሰ እየተቀጠለ ይሄድና
ያልተጠበቀ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራልና ነው፡፡ ይህ ከፍ ሲል የተገለጸው የግጭትና አንዱ ሌላውን እያሸነፈ የማስገበር ሁኔታ የሚያመለክተን አማራ
ኦሮሞን ወይም ኦሮሞ አማራን የማሸነፍ ጉዳይ አለመሆኑንና ታሪካዊ አንድምታው ከዚህ የፊት ለፊት ሽፋን ረቀቅ ያለና የተለዬ መሆኑን ነው፡፡
በተቻኮለ ፍርደገምድልነት የተሳሳተ አመለካከት ከማዳበር በፊት እውነትን መረዳት ለሁሉም ይጠቅማል፡፡
ሰሜነኞቹ አማሮች ጎራ ለይተው እንደተጋጩና ለጉዳት እንደተዳረጉ ሁሉ ኦሮሞዎችም እንዲሁ ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡
ለዚህ አንዱ ግልጽ ማስረጃ የሚሆነን አፄ ምኒልክ በወጣትነታቸው ዘመን በአፄ ቴዎድሮስ ተይዘው ታስረው በነበረበት ወቅት በጎንደርና በሸዋ
የአማሮች መኳንንትና መሣፍንት መካከል የታየው ፍጥጫ ነው፡፡ ወጣቱ ምኒልክ በተፈቱ ሰሞንም የኦሮሞ ነገዶች ኃይለኛ የርስ በርስ ውጊያ ላይ
ነበሩ፡፡ የተቀናቃኞቻቸውን አከርካሪ በመምታት ያን ግጭት በአሸናፊነት ለመውጣት የፈለጉ የተወሰኑ የኦሮሞ ጦር ቡድኖች ከሸዋ አማሮች ንጉሥ አፄ
ምኒልክ ጋር ኅብረት ፈጠሩ፡፡ ቱለማ ኦሮሞ፣ ሊሙና ሜጫ ኦሮሞ የሚባሉት የኦሮሞ ጦሮች ከሸዋው ንጉሥ ከአፄ ምኒልክ ጦር ጋር በመተባበር
ሌሎችን የኦሮሞ ጦሮች በተለያዩ አስከፊ ዐወደ ዉጊያዎች በማሸነፍ ብትንትናቸውን አወጡት፡፡ ባጭሩ ኦሮሞዎች በኦሮሞነታቸው በአንድ ኦሮሞ
ያልሆነ ባዕድ አካል በቅኝ ግዛት አልተያዙም፡፡ እርግጥ ነው የኦነግ መሥራች አባላት ይህን የ”ቅኝ ግዛት” ተረት ተረት ስላላመኑበት በተለይ
በመጀመሪያ አካባቢ ይህን ያህል አፍ ሞልተው ሲናገሩት አልተስተዋለም፡፡ ይሁንና በ1960ዎቹ አካባቢ የኦነግ አመራሮች በግማሽ ኦሮሞ በሆኑት
የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ኦሮሞዎች እንዲያምጹባቸው ለማድረግ ስሜትን የሚማርክ አንዳች የመቀስቀሻ ዘዴ መቀየስ
አስፈለጋቸው፡፡ ለዚያም ሲሉ ይህችን መናኛ የ‹ቅኝ ግዛት› ካርድ በማንሣት ‹ለኦሮሚያ ነጻነት› ሁሉም ኦሮሞ በትግሉ እንዲሣተፍና “ከኢትዮጵያ ቅኝ
ግዛት” ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ይቀሰቅሱበት ጀመሩ፡፡ በዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ድንገተኛ የአቋም ለውጥ ምክንያት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን
ጋር ለበርካታ ምዕተ ዓመታት በሁሉም ረገድ ተዋህደን እንዳልኖርንና በደምና በአጥንት እንዳልተሳሰርን ሁሉ እኛ ኦሮሞዎች “በማያውቁንና
በማናውቃቸው አማሮች” አማካይነት እንደከብት በቅኝ ግዛት በረት ውስጥ የመገኘታችንን ምሥጢር ኦነግ ይፋ አደረገልን፡፡ ይህ ዓይነቱ የመጨረሻ
ውራጅና ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጭ የትግል ሥልት በሌሎች ሀገሮች ውስጥ በሚካሄዱ የነጻነት እንቅስቃሴዎችም ዘንድ ሥራ ላይ ሲውል ታይቷል፡፡
የኛን ሀገር ሁኔታ በሚመለከት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሚረዱት ገሃዱ እውነታ ግን በታሪክ ጥንቃቄ የተሞላበት ልዩ ሙያ ተዳውረው የተሸመኑት
የሸዋ አማሮችና ኦሮሞዎች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ መፈጠር ዋና መንስኤ መሆናቸው ነው፡፡ “ሸዋዎች እነማን ናቸው?” በሚለው በእንግሊዝኛ ቋንቋ
የተጻፈ መጸሐፉ ላይ፣ የታሪክ ምሁሩና የሰው ዘር አመጣጥ ተመራማሪው ዶክተር ጌሪ ሳሎል ይህን የመሰለ ጠቅለል ያለ ድምዳሜ አስፍሯል፤ “ ዘር
ቆጠራን በሚመለከት ሸዋ ውስጥ (ከዚያም በመላዋ ኢትዮጵያ) የፖለቲካ የበላይነትን የጨበጡትን ቡድኖች ብናይ ከአማራና ከኦሮሞ የተወለዱ
ቅዩጣን ዜጎች ናቸው፡፡”
ወደማጠቃለያችን ስንመጣ እንግዲህ በዋናነት መገንዘብ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ከፍ ሲል የተጠቀሱት አራት መሠረታዊ ስህተቶች
የኦሮሞን ታሪክና ኦሮሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት የሚጫወተውን ሚና በሚመለከት መዘገብ የሚፈልጉ በተለይ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችን
በማሳሳትና እውነቱን እንዳይዘግቡ በማወናበድ እያደናቀፉ መሆናቸውን ነው፡፡ አልጀዚራን የመሳሰሉ ዕውቅ የመገናኛ ብዙኃን የኦሮሞንና የሌሎች
ኢትዮጵያውያንን ችግርና እንግልት መዘገባቸው እሰዬው የሚያሰኝ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ያለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ይወጡ ዘንድ ዘገባው
ሚዛናዊ እንዲሆን ተጨማሪና ከፍተኛም ጥረት ማድረግ እደሚገባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ አለበለዚያ የሚሠሩት የተዛነፈ ሥራ በተለይ
ወጣቱን ክፍል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይመራውና ለችግሮች መፍትሔ ከማግኘት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ እንደውነቱ ከሆነ
በኢትዮጵያ ውስጥ እየመጡ በሚሄዱ የተለያዩ መንግሥታት አማካይነት ከፍተኛ የአስተዳደር በደልና ጭቆና የደረሰባቸውና የሚደርስባቸው
ኦሮሞዎች ብቻ ሣይሆኑ ሁሉም ዜጎች ናቸው፡፡ ከዚህ አስከፊ የብረት አጥር ወጥተው ወደተሻለ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘመን ሊሸጋገሩ
የሚችሉት ደግሞ የጎሣና መሰል ልዩነቶቻቸውን ትተው ለጋራ መብቶቻቸው መከበር በአንድነት ሲቆሙና በአንድነት ሲታገሉ ብቻ ነው፡፡ በጋራ
ሲሰለፉ ደግሞ የጋራ ጠላቶቻቸው በማር ለውሰው በመሃከላቸው በረጯቸው መርዘኛ አሉቧልታዎችና የሀሰት ወሬዎች መበርገግና በነጭ ውሸት
የመሠሪዎች መሠረተቢስ ወሬ መረታት የለባቸውም - ‹ተደጋግሞ የተነገረ ውሸት እንደ እውነት ይቆጠራል› የሚባለውን ምሳሌያዊ አባባል
በማስታወስ የሚነገረው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ማጤንና ሁሉም ትኩረቱን ከባርነት አገዛዝ ነጻ ወደሚያወጣው የጋራ መንገድ ማዞር ይኖርበታል፡፡
የውጭ የመገናኛ ብዙኃንም ያልተረጋገጠ የሀሰት ዘገባ በማቅረብ በሕዝብ መሀል ጥርጣሬንና መፈራራትን ከማንገሥ ተቆጥበው ትክክለኛነቱ በሁሉም
ወገኖች ዘንድ የተመሠከረለትን ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ከዚህ ቀደም ኅትመት ወይም አየር ላይ ባዋሏቸው መሰናዶዎቻቸው ላይ ስህተት
ካለም ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ማስተካከያ መቀበልና ማስተላለፍ፣ ለቀደመ ስህተታቸውም ይቅርታን መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ
ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ከአሁን በኋላ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ከቀሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ለዴሞክራሲ፣ ለልማትና ለፍትህ የሚያደርገውን
ትግል የሚያደናቅፉ ከፋፋይና መሠረተቢስ ዝግጅቶችን ከማቅረብ እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡
-- ፈቃዱ ለሜሣ የናዝሬት ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ፕሮፌሰርና ጸሐፊ ናቸው፡፡
ለማንኛውም አስተያየትና ሂስ የኔ አድራሻ፡- yinegal3@gmail.com
Original title of this translation:- History 101: Fiction and Facts on Oromos of Ethiopia
የኢትዮሚዲያ ምንጭ፡ Salem News
የኔ ምንጭ፡- Ethiomedia.com - An African-American news and views website.
Copyright 2013 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com 

አውራውን ፍለጋ…

በተመስገን ደሳለኝ
‹‹በድብልቅልቁ አምላክ››
መግቢያ
ዛሬ በስሱ ላነሳው ያሰብኩትን አጀንዳ አለቃ አፅሜ በምኒልክ ዘመን ካሳተሙት አንድያ መጽሐፋቸው ላይ ባገኘሁት ታሪክ ልጀምር፤
እንዲህም ይነበባል፡-
‹‹በሸዋ መርድ አዝማች ኃይሌ፣ በሣህለ ሥላሴ አልጋ ከተቀመጡ በኋላ ከአቶ ሰይፉ ጋር ቂሙ የማይበርድ የቅድስት ኃይማኖት ጦርነት
ተጀመረ፡፡
‹‹በዚያን ዘመን፣ በዚያች ወራት የነበረ ሰው እንዴት ያሳዝናል፤ ታላቅ ሽብር ሆነ፣ ልጅ ሲወለድ ስሙ ‹ሽብሩ› ወይም ‹አሳር አየሁ›› ይባል
ነበር፤ የሸዋ መንግስት ከሁለት ተከፈለ፤ አቶ ሠይፉ ከኦሮሞ ጋርና ቴዎድሮስን ከጠላ አባ ሰላማን ከነቀፈ ጋር ሆኑ፤ መርድ አዝማች ኃይሌ
ቴዎድሮስንና አባ ሰላማን የወደደን ተከተለ፤ እንደዚህ ጦርነት ሽብር፣ ዘረፋ መጋደል ሆነ፤ በየአውራጃው ‹የአጣ ምን አጣ?›፣ ‹የአገኘ ምን
አገኘ?› ተባለ፡፡
‹‹ዳኛ ጠፋ ‹በቴዎድሮስ አምላክ፣ በሰላማ አምላክ፣ በኃይሌ አምላክ፣ በሰይፉ አምላክ፣ በበዛብህ አምላክ› ቢሉ የሚሰማ ታጣ፤ አንድ
ባላገር ወንበዴዎች ሲደበድቡት ‹በድብልቅልቁ አምላክ› አለ ይባላል፡››
ይህ የእኛም ዘመን በአፄ ቴዎድሮስ አስተዳደር ወቅት እንደተፈጠረ ከሚነገርለት ‹‹ውጥንቅጡ የወጣ›› ወይም ‹‹የተከፋፈለ አመራር›› ጋር
የሚመሳሰልበት ገፅታ እጅግ በርካታ በመሆኑ ‹‹ለምን?›› ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል፤ አዎ! ከመቶ ሃምሳ አመት በኋላ ለምን ወደኋላ
ተጎተትን? የህዝባችን ንቃተ-ህሊና ለመዘመን ምቹ ስላልሆነ? ወይስ ጉልበተኛ አሳዳሪዎቻችን መብቱን የሚያውቅ፣ ለምን ብሎ የሚጠይቅ
ህብረተሰብ ሰጥ ለጥ ብሎ ለረዥም ጊዜ በዝምታ ሊገዛ አይችልም በሚለው መርሆዋቸው በፈተሉት ሴራ?
በታሪካችን የተሳካለት ለህዝብ የሚበጅ ብቁ አስተዳደር አግኝተን ባናውቅም፣ ቢያንስ በዮሐንስ ዘመን፣ በምኒልክ ዘመን፣ በመንግሥቱ
ዘመን፣ በመለስ ዘመን እያልን የምናማርረውና የምንኮንነው (የተጠያቂነቱን ኃላፊነት የምናሸክመው) ‹‹አውራ›› አጥተን ግን አናውቅም፤
ዛሬ ይህ የለም፡፡ በዚህ ፅሁፍም ከኢህአዴግ ውስጥ አውራው መውጣት ይኖርበታል ብዬ የማስበው ፓርቲው በመለስ ሞት ማግስት
ወዴት እንደሚሄድ መቸገሩ ራሱንም ሆነ ሀገሪቱን ወደገደል ይከታል ከሚል መነሻ ነው፡፡ የፓርቲው የገዥነት ዘመን እንደሚነግረን
ጡንቸኛ ሰው የሆነ ጊዜ ይመጣል፤ አሊያም በያዘው ግራ-ገብና የተበጣጠሰ አሠራር ባልታሰበ ወቅት የተለያዩ ክልላዊ የጦር አበጋዞችን
ፈጥሮ መዳረሻ ያሌላትን ሀገር ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ እንደልማዱ አንድ ጡንቸኛ ከመሀል ሌሎቹን ጨፍልቆ ከወጣ ምንም ያህል ደመ-
ቀዝቃዛ አምባገነን ቢሆን እንኳን ከዚህ ወደከፋ አዘቅጥ ከመንደርደር ይታደገናል ብዬ አስባለሁ፡፡ መቼም ማንኛችንም ብንሆን ይሄ ስርዓት
ካለአንዳች ኮሽታ እንዲቀየር እንጂ ከራሱ ሞት ጋር ህልውናችንን እንዲያፋጥን አንፈቅድም (በነገራችን ላይ በዚህ ፅሁፍ ‹‹አውራ››፣
‹‹መሪ›› የሚለውን ቃል ብቻ ለመተካት እንጂ ‹ምን አይነት መሪ?›፣ ‹ዴሞክራት-አምባገነን?›፣ ‹ቅን-ክፉ?› የመሳሰሉትን ትርጓሜዎችን
ለመወከል ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ተደርጎ እንዳይወሰድ አስቀድሜ እንዲህ አሳስባለሁ)
የመለስ ህልፈት በሀገሪቱ ላይ ካነበረው ድብልቅልቅ ሁኔታ አንፃር ከአራቱ የኢህአዴግ መስራች ድርጅቶች ‹የአጣ ምን አጣ?›፣ ‹የአገኘ ምን
አገኘ?› ብለን ብንጠይቅ በትክክል መልስ የሚሰጠን ማነው? ምክንያቱም ከመለስ በኋላ ሲደረጉ የምናስተውላቸው አንዳንድ ድርጊቶች
‹‹ከመለስ ራዕይ›› አንፃር የሚጣረሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገሚሱ የ‹‹መለስን ራዕይ አስቀጥላለሁ›› እያለ እንዳልተገበዘ ሁሉ፣ መለስ ያገደውን
ሰልፍ ሲፈቅድ ታይቷል፡፡ ከቤተሰብ አባላት በቀር ማንም እንዳይጠይቃቸው መለስ የከለከላቸውን የህሊና እስረኞች በዘመድ ወዳጅ፣
በአጋር ጓደኛ እንዲጠየቁ ፈቅዷል፡፡ በመለስ ዘመን ለይስሙላ እንኳ የተለየ ሃሳብ የማይነሳበት የፓርላማው ዝግ-በር፣ ዛሬ ተከፍቷል
ተብሏል፤ ፓርላማውም ጥርስ እንዳወጣ ተነግሯል - ተነካሹ ማን እንደሆነ ባይገልፅልንም፡፡በስልጣን ለመቆየት ወሳኝ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነው የመከላከያ ሚኒስቴርም ይህንን ያህል አመት ‹‹ባጀትህን አላግባብ አጉድለሀል››
የሚል ጠያቂ አልነበረበትም፤ ዛሬ ‹‹እየጠየቅነው ነው›› ተብሏል፤ እውነት ከሆነ መልካም ነው፡፡ እኔ በግሌ ግን የታጠቀው ሠራዊት በተነሳ
ቁጥር ብዙ ጊዜ ትዝ የሚለኝ የፓርቲውን ጥቅም ለማስከበር ወታደራዊ ትምህርቱንና የጠመንጃውን ብቃት ህዝብ ላይ እንዲፈትሽ ሲገደድ
ነው፡፡
የሆነ ሆኖ ይህ እስካሁን በቅጡ ያላወቅነው አዲሱ ኃይል (አመራር) ለውጥ እያካሄደ ነው በሚል እሳቤ፣ (ምንም እንኳን ሀገር ሊቀይሩ
የሚችሉ መሠረታዊ ለውጦች ባይሆኑም) ለለውጡ መግፍኤው ምንድር ነው? ብለን ብንጠይቅ ለጊዜው ከግምት የዘለለ መልስ ማግኘት
የምንችል አይመስለኝም፤ ምናልባትም የስርዓቱ የተለመዱ ‹‹ማስቀየሻ›› ዘዴዎች ወይም መጪውን ምርጫ ታሳቢ ያደረገ አደናጋሪ ስልት
ሊሆን ይችላል ብንል እንኳ ሰውየው የነበረው ‹‹ራዕይ›› ሳይሆን ‹‹ቅዠት›› ነበረ ወደሚል ድምዳሜ መገፋታችን አይቀሬ ነው፤ ይህም
ነው ‹‹በድብልቅልቁ አምላክ›› እንድንል የሚያስገድደን፡፡
መለስ በህይወት ሳለ ‹‹ጉልበተኛ ነኝ›› ብሎ ስለሚያምን ተቃውሞ ሰልፎች እና ህዝባዊ ሰላማዊ ንቅናቄዎች እንዳይደረጉ በራሱ አንደበት
እያስፈራራ ይከለክለበት የነበረው ስልት፣ ዛሬ በፖሊስ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ተቀይሯል፤ ይህንን የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
የእስልምና እምነት ተከታዮች በሰላማዊ መንገድ ከዓመት በላይ ያነሱትና አሁንም ድረስ እያነሱት ያለው ‹‹የሃይማኖት ነፃነት መብታችን
ይከበር›› ጥያቄ በየትኛው መዝገበ ቃላት ነው ‹‹የአክራሪ ኃይሎች የሁከት መንገድ›› የሚል ፍቺ የተሰጠው? በአርሲ፣ ኮፈሌ ከተወሰደው
የኃይል እርምጃ ጀርባስ የማን አጀንዳ (ፍላጎት) አለ? ደህና! ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ያስፈልጋል ከተባለ ከችግሩ ሁለት ቀን አስቀድሞ
የተሰማው የፌደራል ፖሊስ እብሪት አከል ማስፈራሪያ ይከተሉት ከነበረው ሰላማዊ መንገድ እንዲወጡ ገፍቷቸው ከሆነስ ከዚህ ውጪ
ምን አማራጭ ነበራቸው? የሚል ክርክር መነሳቱ አይቀርም (በኮፈሌ የተፈጠረውን ችግር የሰማሁት በኢቲቪ ቢሆንም፣ ብዥታ
የፈጠረብኝን አንድ ጉዳይ ልጥቀስ፤ ቴሌቪዥን ጣቢያው ተቀማጭነቱ ኮፈሌ የሆነ ዘጋቢ (ሪፖርተር) እንደሌለው አረጋግጫለሁ፤ ይሁንና
‹‹ሁከተኞቹ›› ዱላና ገጀራ መሰል ስለት ይዘው ተቃውሟቸውን በጩኸት እያሰሙ፣ ከፀጥታ አስከባሪ ጋር ፈጠሩ የተባለውን ግጭት፣
ኢቲቪ ቀርፆ፣ በዜና እወጃው ሰዓት ላይ አቅርቦልናል፤ ደግሞም ዜናውን በቦታው ተገኝቶ ያጠናቀረው ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነ፣
ያውም መዝናኛ ፕሮግራም ላይ የሚሰራ ኤሊያስ አማን የተባለ ጋዜጠኛ ሲሆን፣ በድምፅ መርዶውን ያሰማን ደግሞ ጋዜጠኛ ሳሙኤል ከበደ
ነው። እንግዲህ ብዥታ የፈጠረብኝ ወይም ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚል ጥያቄ ያጫረብኝ ይሄ በልቦለድ ዓለም እንኳ ለማመን ፍፁም
የሚያዳግት ሁኔታ ነው። ኤልያስ በዕለተ ቅዳሜ የኮፈሌ ነዋሪዎች ሁከት እንደሚፈጥሩ በምን አውቆ አስቀድሞ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ቦታው
ላይ ደርሶ ሁከቱን ሊዘግብ ቻለ? ምናልባት ለአካባቢው ቅርብ የሆኑት የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባልደረቦች ዜናውን ቢያዘጋጁት፣
ወይም እንደተለመደው ዘገባው የኢዜአ ቢሆን ኖሮ ይህ ጥያቄ ባልተነሳ ነበር፤ ግን…
‹‹ካፕቴኑ›› ማነው?
የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ፣ ሀገሪቱ ብቻ ሳትሆን ‹‹አውራው ፓርቲ›› ራሱ ‹‹አውራ›› አልቦ መሆኑን ለመረዳት ብዙ
አለመጠበቃችን እውነት ነው። እርሱ ያለፉትን አስራ አንድ ዓመታቶች (ከ1993-2004 ዓ.ም.) ኢህአዴግን በበላይነት ተቆጣጥሮ፤
ከድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ይልቅ ጠንካራ መዳፍን በመጠቀም ‹‹ብቸኛ ሰው›› (Strong man) የነበረ መሆኑም እውነት ነው፡፡
እንግዲህ እነዚህ ኩነቶች ናቸው ከመለስ ህልፈት አንድ ዓመት በኋላም የድርጅቱን አቅጣጫ በተመለከተ ለትንተና አዳጋች ያደረጉብን፡፡
ዛሬ የሰማነው መላ-ምት ከወር በኋላ ይቀየራል፡፡ የኃይለማርያም ደሳለኝን ስልጣን በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት
ገለልተኛ ለሆነ ጠባቂ እንደተሰጠ አድርገን ብንወስደው አሁንም ግንባሩን የሚዘውረው (የሚመራው) ‹‹ካፕቴን›› ማነው? የሚለው ጥያቄ
የግድ መልስ ይሻል፡፡
ለልዩነት መንስኤ፣ ከዚህ ቀደም ተደጋግሞ እንደተገለፀው ኢህአዴግ አራት ብሄር ተኮር ድርጅቶች የመሠረቱት ‹‹ግንባር›› ቢሆንም፣ አባል
ድርጅቶቹ በአንድ ሰው ጠንካራ መዳፍ ስር ቆይተው፣ በእንዲህ ያለ ያልታሰበ አጋጣሚ ነፃ ሲወጡ፣ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውም አብረው
ከጠርሙዝ የወጣ ‹‹ጂኒ›› መሆናቸው አይቀሬ ስለነበረ ይመስለኛል፡፡ የኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና የደመቀ መኮንን
ምክትልነት ይፋ በሆነ ሰሞን ‹‹ህወሓት ተገፋ›› የሚሉ ድምፆችን አስነስቶ ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ደግሞ የብአዴኑ ብርሃነ
ኃይሉ በደፈናው ‹‹የአፈፃፀም ችግር አለብህ›› ተብሎ ከሀላፊነቱ በተነሳ ማግስት ሌላኛው የድርጅት ጓዱ መላኩ ፈንቴ በ‹‹ሙስና››
መከሰሱ (ምናልባት ብርሃነ የፍትህ ሚኒስትር በመሆኑ መላኩን ለማሰር የወጣውን ‹‹የክስ ቻርጅ›› አልቀበል ብሎ ይሆን ‹‹የአፈፃፀም
ችግር›› የተባለው?)፤ እንዲሁም ‹‹የመለስ ተተኪ ባለጊዜ›› የሚል ግምት የተሰጠው በረከት ስምኦንም ከነበረበት ስልጣን ተነስቶ
(በተለምዶ ‹‹የስራ ፈት ቦታ›› በሚባለው) በ‹‹አማካሪ››ነት መመደቡ ‹‹የተሸነፈው የህወሓት ኃይል አንሰራራ›› ወደሚል ጠርዝገፍቶታል፤ ወይም ከ‹‹ኃይለማርያም ጀርባ›› አለ ተብሎ ይታሰብ የነበረው ኃይል እንደ ተሸነፈ የሚያስቆጥር መስሏል፡፡ በአናቱም
በአንዳንድ የሚኒስትርና የዳይሬክተር ቦታዎች ላይ የደኢህዴን አባላት መሾማቸው ኃ/ማርያም ‹‹የደቡብ ሰዎችን ወደፊት አምጥቶ
ራሱን/ስልጣኑን ለማጠናከር እየሞከረ ነው›› የሚል ጉርምርምታ እየፈጠረ እንደሆነ እዚህ ጋ መነሳቱ አይከፋም፡፡
እነዚህ ኩነቶች ናቸው ሀገሪቱን (ገዥው ኢህአዴግን) ማን እየመራ (እያሽከረከረ) ነው? የሚል ጥያቄ እንድናነሳ የሚያስገድዱን፤ ሌላው
ቀርቶ ህዝብን እያስፈራራ ያለውን ኃይል በቅጡ ማወቅ አልተቻለም፡፡ በቀኝ እጁ የአደባባይ ተቃውሞ ሠልፍ እየፈቀደ፣ በግራ እጁ
የሚያግደውስ ማነው? ፍትህ፣ ፍኖተ-ነፃነት እና ልዕልና ጋዜጦችን፣ አዲስ ታይምስ መፅሔትን ማነው በህገወጥ መንገድ ያፈነው?
የእስልምና እምነት ተከታዮች የሃይማኖት ነፃነታቸው እንዲከበር ጥያቄያቸውን ለመንግስት ያቀርቡላቸው ዘንድ የመረጧቸውን የኮሚቴ
አባላትስ በ‹‹አሸባሪ››ነት ከስሶ ያሰረው ማነው? …ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀርባ አድፍጧል ይባልለት የነበረው ብአዴንና በስሩ ያደሩ
የመሰሉን ኦህዴድና ደኢህዴን? ወይስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያንሰራራ ያለው የህወሓት ኃይል? ወይስ አንደኛውን የህወሓት ክንፍ ይዟል
ሲባል የነበረው የእነአባይ ወልዱ ቡድን? ወይስ ራሱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይሆን የ‹‹ወንበሩ››ን ስልጣን ተጠቅሞ ‹‹አሳር አየሁ››ን ታሪክ
የደገመው? ጥያቄዎቻችንም እነኚህ ናቸው፤ ወዴት አቤት እንበል? ‹‹ኧረ! በባንዲራው›› ብለንስ ማንን እንማፀን?
የ‹‹ራዕዩ›› ነገር
አቶ መለስ ህይወቱ ካለፈ ድፍን ዓመት ሞልቶታል፤ ለአጠፋውም ሆነ ለአለማው ታሪክ ካልሆነ በቀር፣ ህግም ሆነ ፖለቲካዊ አሠራር
ሊጠይቀው አይችልም፡፡ ሆኖም ዛሬ እንዲህ ድብልቅልቁ ከመውጣቱ በፊት ሲነግሩን የነበረው ‹‹ራዕዩ›› ዛሬም ቢኖር በወደድኩ፤ ራዕይ
የሌለው ህዝብ የትም አይደርስምና፡፡ ነገር ግን ይህ ባዶ ምኞት ብቻ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ጓዶቹም ያውቃሉ፤ ሌላው ቀርቶ መለስ ለእነሱም
ሳይቀር አስፈሪ መሪ ብቻ ሳይሆን ‹‹ጠቅላይ›› እንደነበረ ያውቃሉ) የመለስ አገዛዝ አስከፊነቱ ጉልበተኝነቱ ብቻ መች ሆነና፤ ከለታት አንድ
ቀን በእንዲህ ያለ መልኩ ማለፌ አይቀርም በሚል ተተኪ ማፍራት አለመቻሉም ጭምር ነው፡፡ ለአንድ ህዝብ የስኬት ጉዞ ‹‹ራዕይ››
ብቻውን የትም አያደርሰውም፡፡ ራዕዩን አሳምኖ እና አስተባብሮ የሚመራው ‹‹አውራ›› የግድ ይፈልጋል፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ሁለቱም
የሉም፤ ታዲያ ማነው ‹‹እናስቀጥለዋለን›› ሲባል የነበረውን ‹‹ራዕዩ››ን የሰለበው? ‹‹አውራ››ውንስ የሰወረው ማነው? ኢህአዴግ ወደ
ስልጣን ከመጣ ጀምሮ እስኪሰለቸን ከነገረን ‹‹ውጥኖቹ›› ስንቶቹ መከኑ? ስንቶቹስ ፖሊሲዎቹስ ከሸፉ? በፀደቀበት አዳራሽ በስሜት ንጦ
በጭፈራ ያዘለለው ‹‹ህገ-መንግስት››ንስ ስለምን ማክበር ተሳነው? ይህ ሁሉ ‹‹ሽብሩ›› እና ‹‹አሳር አየሁ›› መንስኤው ማን ነው?
በየተቋማቱ ኃላፊነቱን ከፖለቲካ አድልዎ በፀዳ መልኩ በታማኝነት እየተወጣ ያለው ማነው? ገንዘብ ሚኒስቴርስ በአስተዳዳሪነት
የተረከበውን ገንዘብ እንዲህ በዋል-ፈሰስ ሲባክን ማን ይጠይቀው? የእግር ኳስ አለቆች እንኳን ማንም ተርታ ተመልካች ሳይቀር
የማይሳሳተውን ስህተት ሰርተው፣ የሀገርን ጥቅም ጎድተው ሲያበቁ በእገሌ እና እገሌ አሳብበው፣ በስልጣናቸው ሲቀጥሉ ማን
ይጠይቃቸው? ህግ አስከባሪ የሚባሉት ዳኞችስ ስርዓቱ ያልወደደውን ‹‹ኧረ በሕግ!›› እያሉ ወህኒ ሲጥሉ ‹‹ሃይ›› የሚላቸው እንዴት
ጠፋ?
በሌላኛው ሰፈር፡- ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሳቸው ላፀደቁት መተዳደሪያ ደንብ የሚገዛ፣ ዲሞክራት አውራ ማብቃት ስለምን
ተሳናቸው? በየጊዜው በውሃ ቀጠነ የአመራር አባላቶቻቸውን ማገዳቸውስ እውን ለፓርቲው ጥቅም ሲባል ነው? ለውጥ እናመጣለን
ብለው የተቀላቀሏቸውን አባላትስ ግልፅ ያልሆነላቸውን በጠየቁ ዕለት ‹‹ወያኔ›› እያሉ የሚፈርጁበት ማስረጃ ምንድር ነው? ለግል ጥቅምና
ለዝና የተቀላቀለውን፣ ከልቡ ለውጥ ከሚፈልገው መለየቱ ይህንን ያህል ከባድ የሆነባቸው ምስጢሩ ምን ይሆን?
ሀገሪቱ በሁሉም ረገድ አውራ አልቦ ሆናለች፤ የምድሪቱ ማህፀን ይህንን ጉድለት መሙላት ያልተቻለው ስለምንድር ነው? ‹‹መሲሁ››ስ
መቼ ይሆን የሚመጣው? ወይስ በሰሜን አሊያም በባሌ ተራራ መሽጐ የተፃፈለትን የመከሰቻ ቀን እየጠበቀ ይሆን? አደባባዩስ ስለምን ጭር
አለ? ሌላው ቢቀር የጥንቱን የጎበዝ አለቃ ያህል ‹‹አውራ›› እንኳ ስለምን አጣን? ‹‹ደጋፊ አጨብጫቢ›› ሳይሆን ‹‹መካሪ ለሀገር
ተቆርቋሪ›› አዛውንት ስለምን ጠፋ? የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ጠማማን የማቅናት፣ ትውልድን የማነፅ፣ ጥፋትን የማረም
የአስተምህሮ መንገድ የሚከተል አቻስ ከወዴት መሽጓል? እኮ! ስለምን ረቢ አልቦ ሆንን?
በመጨረሻም መውጫ፡-በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ማን በበላይነት እየመራ እንደሆነ ማወቅ አለመቻላችንን የምትገልፅ ተመሳሳይ ታሪክ አሁንም
ከአለቃ አፅሜ መጽሐፍ ልጥቀስና ልሰናበት፡- ነገሩ በራስ አሊ (ወራ ሸይክ ስርወ-መንግስት) ዘመን የተፈፀመ ነው፤
‹‹በራስ ዓሊ ዘመን ሰሜንና ትግራይን የሚገዛ ደጃች ውቤ የሚባል በኦሮሞዎች ተቆርቆሮ፣ አቡነ ሰለማን ይዞ፣ ራስ አሊን ሊወጋ ዘመተ፤
ደብረ ታቦር አጠገብ አጅባር ላይ ተዋጉ፣ ራስ ዓሊም እስከ የነጆ፣ እስከ ገራገራ ሸሹ፤ ደጃች ውቤንና አቡኑን ብሩ አሊጋዝ ማረካቸው፤ ድል
የራስ ዓሊ ነበረ፤ አንዱ ሰው ላንዱ ወሬን ጠየቀው፤ ያም ‹ራስ ዓሊን ደጃች ውቤ ተዋጉ› ሲል መለሰለት፤ ‹እህስ› አለው ‹ራስ ዓሊ ሸሹ፣
ደጃች ውቤ ተማረኩ፣ ተያዙ› አለው፤ ‹በወግ አታወራም› ቢለው ‹እነሱ በወግ ያልሆኑትን እኔ ምን ብዬ ላውጋው› አለው››
እናስ! ብዙዎቻችን የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ሊሄድበት ይችላል እያልን የቢሆን ዕድሎችን (Scenarios) ከመናገር ውጪ ጥብቀት ያለው
መደምደሚያ ላይ መወያየት ብንቸገር ምን ይገርማል!?

Dishonor Among African Elections Thieves

by Alemayehu G. Mariam

Unfree and Unfair Elections in Zimbabwe
Zimbabwe had its presidential elections last week. Elections as in rigged. Robert Mugabe, the senile octogenarian and the only president since Zimbabwe gained independence in 1980,  “won” for the seventh time by 61 percent of the vote. His Zimbabwe African National Union – Patriotic Front (ZANU–PF) clinched a supermajority in parliament that will allow it to change the constitution. This past May, Mugabe signed a new constitution which sets a term limit of two five-year terms for president (not retroactively applicable to Mugabe) and eliminated the post of prime minister. In 2009, following a violent election aftermath, a coalition government of national unity was formed designating opposition leader Morgan Tsvangirai as Prime Minister.Zimbabwe had its presidential elections last week.
General Olusegun Obasanjo, the former president of Nigeria, who led the African Union Election Observer team (69 observers) in Zimbabwe certified the election as valid declaring, “I have never seen an election that is perfect. The point has always been and will always be, how much the infractions, imperfections have affected the reflection of the will of the people and up to the point of the close of the polls our observation was that there were incidents that could have been avoided. In fact, up to the close of the polls we do not believe that those incidents will amount to the result not to reflect the will of the people.” Bernard Membe of Tanzania who led the Southern African Development Community (SADC) election observer mission (442 observers) chimed in declaring that the election was “free and peaceful”.  The observer mission from the Common Market for Eastern and Southern Africa (COMESA) likewise gave its approval and urged all parties to accept the election result. None of the observer missions used the phrase “free and fair” to describe the elections outcomes.
The Zimbabwe Election Support Network (ZESN) (7,000 certified domestic monitors) declared the elections were “seriously compromised” and pointed out a number of serious irregularities.  Prime Minister Morgan Tsvangirai called the election “a huge farce” and a “sham that does not reflect the will of the people.”
Only Botsawna called for an investigation 
Botswana’s observer team did not buy Mugabe’s election victory or the AU/SADC’s affirmation of it.  After reviewing the preliminary report of its 80-member election observer team led by former Botswanan vice-president Mompati Merafhe, the government of Botswana issued an official statement advising that “there is a need for an independent audit of the just concluded electoral process in Zimbabwe. Such an audit will shed light on the conduct of the just ended election and indicate any shortcomings and irregularities that could have affected its result, as well as the way forward.”
This is in sharp contrast to the conclusions of the  60-person African Union (AU) observer team led by former Botswana president Ketumile Masire which concluded that the 2010 “election” in which the ruling regime in Ethiopia claimed a 99.6 percent victory was “free and fair”. Masire said his team found no evidence of intimidation and misuse of state resources for ruling party campaigns in Ethiopia and proclaimed, “The [elections] were largely consistent with the African Union regulations and standards and reflect the will of the people … The AU were unable to observe the pre-election period. The participating parties expressed dissatisfaction with the pre-election period. They did not have freedom to campaign. We had no way of verifying the allegations.”
Masire’s report was a travesty of election observation. At the time, I took issue with Masire’s findings and challenged his conclusions:
With all due respect to Masire, it seems that he made his declaration clueless of the observation standards he is required to follow in the AU Elections Observation and Monitoring Guidelines.  If he had done so, he would have known that there is no logical, factual or documentary basis for him to declare the ‘elections were largely consistent with the African Union regulations and standards’. For instance, pursuant to Section III 9 (e) of the guidelines (‘MANDATES, RIGHTS AND OBLIGATIONS OF THE OBSERVERS’), Masire’s team had a mandatory duty to ‘observe the political parties and groups as well as the population at large in the exercise of their political rights, and the conditions in which such rights are to be exercised’. Masire by his own admission made no such observation: ‘The AU were unable to observe the pre-election period’. Under Section V (13), the guidelines mandate that ‘AU Observers should ascertain that: … (b) all competing political parties have equal access to both the print and the electronic media (radio, T.V.).’ Masire said his team ‘had no way of verifying’ pre-election complaints, including complaints of unequal access to state-controlled media. Under Section V (B) (d), the AU observers had a mandatory duty to ascertain ‘the campaign process is conducted in conditions of serenity, and that there are no acts of provocation or intimidation capable of compromising’. Masire’s team failed to make such inquiries. Under Section B (24), the guidelines mandate: ‘The atmosphere during the campaign should be carefully observed, and among the factors to consider in this regard include … (iv) persistent or reported cases of human rights violations.’ Masire’s team does not appear to be aware of such a requirement, let alone actually make the observation. It is truly regrettable to say of a former African leader that he showed no evidence of having read or understood the numerous mandatory election observation duties set forth in minute detail in the AU guidelines before shamelessly and pathetically declaring the elections ‘were largely consistent with African Union regulations and standards.’
I am gratified that vice president Mompati Merafhe’s observer team in Zimbabwe made its recommendation for an audit investigation based not only on observed election irregularities but also because the “various incidents and circumstances [that] were revealed call into question whether the entire electoral process, and thus its final result, can be recognised as having been fair, transparent and credible in the context of the SADC Principles and Guidelines Governing Democratic Elections within the Community.” I would like to underscore that the Zimbabwe election also fails to meet the AU Elections Observation and Monitoring Guidelines.
No honor among African election thieves?
Are elections in Africa a colossal exercise in futility? Is it possible to have a free and fair election in any African country? Is the African Union (as “African Dictators’ Club”) capable of undertaking an independent and fair observation of elections in an African country? Is electoral democracy a quaint game played by African dictators for the amusement of Western donors and loaners? Is dictatorship in Africa by any other name democracy?
I have long argued that many African governments and regimes including those in Zimbabwe and Ethiopia are thugtatorships. In my February 2011 commentary Thugtatorship: The Highest Stage of African Dictatorship, I sought to explain in simple terms the nature of steroidal African dictatorships:
If democracy is government of the people, by the people and for the people, a thugocracy (thugtatorship) is a government of thieves, for thieves, by thieves. Simply stated, a thugtatorship is rule by a gang of thieves and robbers (thugs) in designer suits. It is becoming crystal clear that much of Africa today is a thugocracy privately managed and operated for the exclusive benefit of bloodthirsty thugtators. In a thugtatorship, the purpose of seizing and clinging to political power is solely to accumulate personal wealth for the ruling class by stealing public funds and depriving the broader population scarce resources necessary for basic survival.
Mugabe’s Zimbabwe is a classic thugtatorship. In March 2008, Mugabe declared victory in the presidential election after waging a campaign of violence and intimidation on his opponent Morgan Tsvangirai and his supporters. According to a Wikileaks cablegram, “a small group of high-ranking Zimbabwean officials (including Grace Mugabe) have been extracting tremendous diamond profits.” Mugabe is so greedy that he stole outright “£4.5 million from [aid] funds meant to help millions of seriously ill people.”  In 2010, Mugabe announced his plan to sell “about $1.7 billion of diamonds in storage”.  Today, Mugabe and his cronies have sucked Zimbabwe dry. Zimbabwe has no national currency of its own and uses the currencies of other countries. When the Zimbabwe Dollar was in circulation, it had denominations of insane  proportions. At one point in 2009, the Reserve Bank of Zimbabwe issued notes in the amount of 100 trillion dollars, which would not buy a bus ticket. In 2003, Mugabe boasted, “I am still the Hitler of the time. This Hitler has only one objective: justice for his people, sovereignty for his people, recognition of the independence of his people and their rights over their resources. If that is Hitler, then let me be Hitler tenfold. Ten times, that is what we stand for.” Mugabe with his trademark Hitler moustache (tooth brush moustache) remains President of Zimbabwe.
The regime in Ethiopia is also a thugtatorship. The ruling “Tigrean Peoples Liberation Front” (TPLF), its  handmaiden the “Ethiopian Peoples Democratic Revolutionary Front” (EPDRF) and their supporters pretty much own the Ethiopian economy. “According to the World Bank, roughly half of the national economy is accounted for by companies held by an EPRDF-affiliated business group called the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT). EFFORT’s freight transport, construction, pharmaceutical, and cement firms receive lucrative foreign aid contracts and highly favorable terms on loans from government banks.” In June 2012, the World Bank released its 448-page report, “Diagnosing Corruption in Ethiopia” with substantial evidence  showing that Ethiopia under the TPLF regime has become a full-fledged corruptocracy (a regime controlled and operated by a small clique of corrupt-to-the-core vampiric kleptocrats who cling to power to enrich themselves, relatives,  friends and supporters at public expense).
Ethiopia 2015: Any chance of a free and fair election?
A year before the 2010 Ethiopian parliamentary election, I predicted the obvious. The 2010 “election” “will prove to be a sham, a travesty of democracy and a mockery and caricature of democratic elections.” The ruling regime claimed a 99.6 percent victory in that election. The international powers that be accepted the results with muted expressions of concern.  The European Union Election Observation Mission- Ethiopia 2010 stated: “The electoral process fell short of certain international commitments, notably regarding the transparency of the process and the lack of a level playing field for all contesting parties.” The White House issued a statement expressing “concern that international observers found that the elections fell short of international commitments. We are disappointed that U.S. Embassy officials were denied accreditation and the opportunity to travel outside of the capital on Election Day to observe the voting.” Johnnie Carson, then-Assistant Secretary of State for African Affairs in the State Department told the U.S. House Foreign Affairs Committee that “we note with some degree of remorse that the elections were not up to international standards… The [Ethiopian] government has taken clear and decisive steps that would ensure that it would garner an electoral victory.” Even Herman Cohen, the former U.S. Assistant Secretary of State who served as “mediator” in the so-called May 1991 London Peace Talks which resulted in the establishment of the Zenawi regime decried the outcome: “This time opposition media and opposition groups were not given fair time on the media and opposition media tends to be suppressed and in that sense I don’t think it was a fair election.”
The outcome of the 2015 election in Ethiopia will be a repeat of the 2010 and 2005 elections. There will be no level playing field and no transparency and accountability in the electoral process. The regime will intensify its campaign of intimidation, harassment and jailing of opposition leaders, parties and dissidents in the run up to the “election”. The press will remain under even tighter control. The regime will intensify its demonization of  opposition parties and depict Ethiopian Muslims as “terrorists”. In short, the 2015 Ethiopina “election” will be a repeat of the Zimbabwean rigged and stolen election. After the daylight election robbery, the U.S., the European Union and the U.K.  will shed crocodile tears as they continue to hand over billions of dollars in aid and loans to the Ethiopian thugtatorship.  They will maintain their conspiracy of silence to see no evil, hear no evil and speak no evil of the regime in Ethiopia. In 2015, thugtatorship will once again rise triumphant in Ethiopia.
Change is inevitable even though African dictators believe they can remain in power indefinitely by stealing elections and harassing, jailing and killing their opponents. African thugtators believe they can use their military and police to crush their opposition out of existence.  Yet many African dictatorships have fallen from their own internal weaknesses and contradictions. Behind the tough and gritty exterior of regimes such as those in Zimbabwe and Ethiopia remain fragile structures and confused and ignorant leaders who are clueless about good governance and what to do to remain in power legitimately. Neither Mugabe’s regime nor the regime in Ethiopia have clear long term goals or strategies to achieve legitimacy. Their deepest aspiration is to transform themselves from bush thugs to urbane statesmen, but there is no political alchemy to do that. As long as the U.S. and Europe continue to provide endless handouts, Africa is doomed to remain a thugocracy.
Change could come through peaceful free and fair elections in Africa. It is more likely that real change in Africa will  come through the expression of the tornadic wrath of the people as seen in the “Arab Spring”. African thugtators would be wise to heed a simple advise. “Politicians are like diapers. They both need changing regularly and for the same reason.”Arrrrgh! The thought of poor Zimbabwe wearing the same diapers since 1980…
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.