Sunday, December 29, 2013

“ነፃ እስክትወጡ በደሌ አትጠጡ” ጃዋር መሀመድ


ሁኔ አቢሲኒያዊ
መቼስ ለአገር የሠራና የደከመ ቢያጠፋም እንኳን የቻለውን ያህል በመሞከሩ በክብር ማኖርና መንከባከብ የውዴታ ግዴታ ነው። የሚያሳዘነኝ ነገር ይሄ ሳይሆን እስካሁን እንዲህ ያለውን ነገር ሰምተንና አይተን ያለማወቃችን ነው ስንት የለፉላትን አገር በእነ መለስ እንዲህ መሆኗን ሳያዩ ማለፋቸው ሳይቀር ዛሬም ድረስ ቢያንስ ስራዎቻቸው በክብር እንደቅርስ አለመያዛቸው ሳያንስ በየጊዜው የሚነሱ የታሪክ ነቃፊዎች የትችታቸው ማሟሻ አድርገዋቸው ማየት ያስዝናል ለዚህም ይመስለኛል አገሪቷ የሠራላትን፣ የደከመላትንና የተቆረቆረላትን ማዋረድ እንጂ ማክበር እንደማታውቅ የሚለፈፈው። በዚያም ተዞረ በዚህ የውዷ ኢትዮጵያ ታሪክ ‘የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’ በመሆኑ ምንም ማለት ልናዝን አይገባም።Ethiopian singer Teddy Afro, Bedele controversy
ከሰሞኑ ደግሞ እነ ጃዋር መሀመድ ተከታዩን ስብከት ነጻ ሊያወጡት ቃል ገብተውለት ለነበረው ኦሮሞ የኢትዮጵያ ልጆች መንፈሳዊውን ስብከታቸው ጀባ ብለዋል፡፡
የኦሮሞ ህዝብ ገንዘቡን እና ንብረቱን ለእነ ጃዋር መሐመድ ሰጥቶ ነፃ ያወጡናል ብሎ ሲጠብቅ ሰባኪ ወ ኮሜዲያኖቹ እነ ጃዋር እና የኦነግ አባላቶች በደሌ አትጠጡ የሚል ትዕዛዝ እያስተላለፉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ነጻ አውጪዎቹ ይህንን ያሉት ከአልኮል ነጻ የሆነ ትውልድ ለማየት ካላቸው የልብ ፍላጎት እና ሀሳብ ሲሆን በተጨማሪም ዘፈን ስንሰማም እየመረጥን መሆን እንዳለበት መክረዋል፡፡
በእነ ጃዋር ትእዛዝ መሰረት ከውጭ ማለትም ከኦሮሚያ ክልል ውጪ በተለይም በእነ ጃዋር እና መሰሎቹ ቅኝ ገዢ ተብለው ከተመደቡት ክልሎች በተገኙ አርቲስቶች የተዜሙ ዘፈኖችን መስማት የተቀደሱትን እና የተባረኩትን የእነ ጃዋር ስብከቶች የመስሚያ ጊዜ እንደሚሻማ የገለጹ ሲሆን ይህም የኦሮሚያ ህዝብ እርኩስ ሀጢያት እንደፈጸመ ተቆጥሮ በሜንጫ አንገቱን ሊባል እንደሚቻል አስጠንቅቀዋል፡፡
በዲያስፖራም ሆነ አሉ እጅግ የተባረኩ የአለም ቅዱስ ጃዋር መሀመድ በዲያስፖራም ሆነ ሀገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድብቅ አላማ በቅኝ ገዚዎች የተፈጠረች እና ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀውን ሀገር ከኢህአዴግ ነጻ ለማውጣት ስለሆነ ይህንን ድብቅ ኢትዮጵያን ነፃ የማውጣት አላማቸውን ተረድቶ በሜንጫ አንገታቸውን ሊላቸው ይገባል ካሉ በኋላ ኢትዮጵያ ነጻ ከምትወጣ ከእነ ጃዋር ጋር ተመሳሳይ አመለካከት እና አላማ ያለው ወያኔ ኢህአዴግ ከነሙሉ አላማው እና ክብሩ ለዘላለም ይንገስ ብለው ሲያበቁ ብዙዎች ታሪክን የኋሊት ብለው በሰየሙት የታሪክ ቡራኬያቸው ዳግማዊ ምንሊክ የተባሉ ከመቶ አመት በፊት የፈጠሯት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሜንጫውን ማንሳት እንዳለበት ሰብከዋል፡፡
ከጃዋር ስብከት እንውጣና ከስብከቱ መለስ ብሎ ከሰሞኑ በፌስ ቡክ ገጹ ለፈረንጁ ገና አክባሪዎች እንኳን አደረሳቹህ ሲል መልእክቱን አስተላልፏል ይህም ኢትዮጵያውያኑ ከሳውዲ ሲባረሩ የተባረሩት የኢትዮጵያ ልጆችን በመከፋፈል ሙስሊም የኦሮሞ ልጆችን ብቻ የሚመለከት ያደረገ ግለሰብ ለፈረነጆቹ ክርስቲያኖች መልካም ገና ብሎ መልካም ምኞት ማስተላለፍ ምን የሚሉት እብደት እንደሆነ ጃዋር እና መሰሎቹ ብቻ ነው የሚያውቁት እና ፍርዱን ለእነርሱ እንተወው፡፡
በመጨረሻም እነ ጃዋርን የመሳሰሉ ጃዋር ወ መለሶች የወያኔ ተምሳሌቶችን እየሰማን አለማውገዝ እንዲሁም እውነታውን አለማሰየት የታሪክ ተወቃሽ ከማድረጉም በላይ ዝምታችን ትክክል እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጃዋርን አላማ በመረዳት ድጋፍ ከመስጠት ሊቆጠብ ይገባል፡፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ “ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ”


ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ “ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ”
ከጥቂት ሳምንት በፊት የዳግማዊ ሚኒሊክን መቶኛ አመት የሞት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በእንቁ መጽሔት ተጋብዤ ቃለ ምልልስ አድርጌአለሁኝ። ይኸዉ Ethiopian Artist Teddy Afroዉይይታችን በ “አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል” እርዕስ ስር ለህዝብ እንደቀረበ አዉቃለሁ። ከዚህ ዉጪ እኔ በማላዉቀዉ ሁኔታ መጽሔቱ በሰራዉ ስህተት ፎቶዬን በሌላ አነጋገር አጅቦ ያወጣዉን ከኔ እምነትም ሆን ጉዞ ጋር የሚራመድ ጉዳይ አይደለም። ይህንኑ ለማረጋገጥ “አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል” በሚል ርዕስ ስር በወጣዉ መጽሔት መልክቶቼን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። ያም ሆኖ መጽሔቱ በሰራዉ ስህተት እርምት አድርጎ ይቅርታም ጠይቆናል። ጉዞዬ የፍቅር የአንድነት እና የይቅር ባይነት ነዉና ይህንንም ጉዳይ በዚሁ ስሜት ውስጥ እናስተናግደዋለን።
ፍቅር ያሽንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን