Monday, February 17, 2014

“ከኛም ቤት እሣት አለ !!” (ይፍሩ ኃይሉ)

 “ለወደቀ ዛፍ ምሣር ይበዛብታል” እንደሚሉ ሆኖ ነው መሰል አገራችንን እትዮጵያንና ሕዝቧን ከያቅጣጫው የገጠማቸው ችግር ከመቼውም የበለጠ የሚያስደነግጥና፤ ሊታመንም በማቻልበት ሁኔታ በጆሮ ለመስማት እንኳ የሚቀፍና የሚዘገንን ነው። በአባቶቻቸን፤ በአያቶቻችንና በቅድመ አያቶቻቸን ደም ፍሳሽና አጥንት ክስካሽ ተፈርቶና ተከብሮ የነበረው ዳር ድንበሯ ዛሬ “የምትፈግ ገብተህ እግርህን ዘርግተህ ተዝናንተህ ፈንጪበት፤ ሁሉም በጅህ ሁሉም በደጅህ ይሁንል” የተባለ ይመስላል። የቤልጅየምን የቆዳ ስፋት የሚበልጥ ለም የኢትጵያ መሬት፤ ከግማሽ ጎንደር እስከ ጋንቤላ ድረስ ለሱዳን መንግሥት በገጸበከትነት ከመሰጠቱም በላይ እንደገና በዚሁ ባልታደለ አካባቢ የሚገኝ ለም መሬት፤ ከነዋሪው አርሶ አደርና አርብቶ አደር ሕዝብ፤ ያለ ፈቃዱና፤ለተነጠቀው ንብረቱና ሃብቱ ያለምንም የዋጋ ክፍያ፤ ለዘመናት ከኖረብት ከአያት ቅድ መአያቱ ቀዬ እየተፈናቅለ፤ በሱ ቦታ ዛሬ  በአንድ ጀንበር ለተፈለፍሉ የወያኔ ቱጃሮችና፤ ለአረብ፤ ለሕንድና ለሌሎች የውጪ አገር ባለሃብቶች እጅግ በሚገርምና በማይታመን ዝቅ ባለ ዋጋ እየተቸረቸረ ይግኛል። በአገር ማስገንጠሉና አገራችንን ያለ ባሕር ወደብ አስቀርቶ፤    ለዘመናት ተከብራ ከኖረችበት ዙፋኗ አሽቀንጥሮ አውርዶ፤ ዛሬ፤ኢትዮጵያን ያለ ቦታዋ  የጂቡቲ ደጀ ጠኚ እንድትሆን የወያኔ መንግሥት ዳርጎአታል። ለዚህም ጥቁር ጠባሣ፤ የኢትዮጵያ አምላክና ታሪክ የወያኔን መንግሥት ይፋረዱታል፤ ወንጀሉንም  ይመዘግቡታል፤ ትውልድም ሲያስታውሰው ይኖራል። ይህ ትውልድም ሆነ መጪው ጥርሱን መከስና ከንፈሩን መምጠጥ ብቻ ሳይሆን ፤አንድነቱን አጠናክሮ፤ ያለ የሌውን አቅሙን አቀነባብሮ፤የተነጠቀውን የባሕር ወደብና የተዘረፈውን ለም መሬት የማስመለ ግዴታ ብቻ ሳሆን  የታሪክም ሃላፍነት አለበት።   
ሰለወያኔ መንግሥት ዓይን ያወጣ የአድለዎና የዘረኛነት ፖሊሲና፤እንደዚሁም ይሉኝታ በሌው የሌብነትና የዘራፊነት ጠባዩ በማስረጃ የተድግፉ፤ወያኔን እርቃነሥጋውን የሚያስቀሩ ብዙ መረጃዎች ተጽፈው ቀርበዋል። እኔ ስለዎያኔ ሌብነትና ቀማኛ ዘራፊነት፤ ብዙ ወገኖች በቁጭትና በመንገብገብ የሚጽፏቸውን በአድናቆትና ሁልጊዜም በአንከሮ እመለከታቸዋለሁ።ለነዚህ እጅግ የሚደነቁ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ወግኖቼ ያለኝ አክብሮትና አድናቆት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የወያኔን ሌብነትና ዘራፊነት፤አምባገነናዊ ጨካኝነትና “የከፋፍለህ ግዛው” ፖሊሲውን ስመለክትና ሥራውን ሁሉ ሳገናዝበው ከአንድ ከውጪ አገር የመጣ ወራሪ ጠላት አድርጌ ነው የምመለከተው። ወይኔና ሥራውን፤በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቅጽበት ተመንጥቆ ዛሬ ከሮኬት በቀደመ ፍጥነት ቆጥሮ የማይዘልቀው ባለሃብት መሆኑን ስመለከት፤ ድሮ በልጅነቴ የሰማሁት ሴቶች ልጆት ሕጻናት ሲያጫውቱና ሲያባብሉ ይዘፍኗት የነበረቺው ዘፈን ትዝ ትለኛለች።  
  “ አሽሩሩ!  እሽሩሩ! አባባ መጡ ከዘቻ! ብሩን ይዘው በስልቻ! ወርቁን ይዘው በስልቻ!!...” እያለች የምትሄድዋ!!  
ታዲያ ከውጪ ከመጣ ጠላት ምን ይጠበቃል? የወያኔ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማሸሽ፤ የኢትዮጵያን ለም መሬት እንደ ቅርጫ ሥጋ እየሸነሸኑ ለግል ገቢ መቸርቸር ምን ያስገርማል? ዛሬ እኮ ወያኔ ሰማይ ከመድረሱ የተነሳ ልጆቹን የሚያስተምረው  ሓርቫርድና ኦክስፎርድ ወይም ስታንፎርድና ካምብሪጅ ነው። ልጆቹን እኮ ዛሬ እንኳን አማርኛና ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማስተማር ይቅርና የራሱንም የናት አባቱን ትግርኛውም ላይ እንዲያተኩርበት አይፈልግም። ዛሬም በዚያው በለመደው፤ በባንዳነት፤ ተለማማጭነትና አጎንባሽነት ጠባዩ፤ በፈረንጅ ባሕልና በፈረንጅ አኗኗር ልማድና ሥረዓት እንደተደነቀና እንደተገረመ ይኖራል። ያንን የሚያኮራውን ባሕሉንና ወግ ላምዱን፤ ቋንቁውንና ዘይቤውን እያፈረበት የመጣ ይመስላል። ዛሬ እኮ ወያኔ የሚዝናናው ሶደሬና ወዶገነት፤ መቀሌና አዲስ አበባ ወይም ድሬዳዋና ባሕር ዳር አይደለም። ፓሪስንና ለንድንን፤ ዱባይንና ታይዋንን ማን ወስዶበት? ዛሬ እኮ ወያኔ ባብዶ እግሩ አይኳትንም! እሱማ የእኛ የአማሮች ድርሻ ነው። እንደዱሮውም ዛሬ ካሮሳ አይዘውርም! ሬንጅሮቨሩና ማርሴዲ ቤንዙን፤ ሌክሰሱንና ቢአምደብይው ለማን ሊሆን? ስንቱን እንቁጥረረው!! ይህ ነው ካንድ ወራሪ ጦር የሚጠበቀው፤ከድሃ አፍ ውስጥ አውጥቶ የራስን ከርስ መሙላት፤ የራስን ባንክ አካውንት ማዳበር!! ወራሪ ጦር ይዘርፋል፤ ይገድላል፤ አስሮ ያሰቃያል፤ንብረት ያወድማል፤ ያነዳል፤ ያቃጥላል፤ ሲበቃው፤ወይም ተሸንፎ ሲባረር ነዋሪውን ሕዝብ ከአመድና ከአቧራ ጋር ደባልቆ ነው።
የወያኔና የሻቢያ መዘዝና ለሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ላይ የረጩት የመከፋፈልና የማጋጨትና የማፋጀት መርዝ በጥቂት የኦሮሞ ተወላጅች ወንድሞችንና እሆቻችንን ቀና አስተሳሰብንና አመላካከትን እየበከለ መጥቷል። የኦሮውን ሕዝብም ሆነ የማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ሕዝብ የመብት ጥያቄ የሚጋፋና የሚቀናቀን፤ ከወያኔ በስተቀር ያለ አይመስለኝም። 
ሰሞኑን ግን በተላያዩ ድረገጾችና የሕዝብ መግናኛ ሜዲያዎች፤የሚለቀቁት እጅግ በጣም የሚአሳፍሩና፤ ለማመን የሚያዳግቱ፤ በሃሰትና በማስረጃ ባልተደገፈ ወንጀል፤ በስመጥሩው ጀግና በዳማዊ ምንሊክ ላይ በተለይ ያተኮረ፤ በአማራው ተወላጅ ላይ በጠቅላላ የሚወርደው መረን የለቀቀ ዘለፋና የቅሌት ውርጅብኝ፤ ከዚያ ከጨዋውና ከአንደበተ መልካሙ ከጀግናው የኦሮሞ ሕዝብ አብራክ ከወጡ ልጆቹ ከቶ የማይጠበቅ ነው። አንዳንድ ልባቸውና ጭንቅላታቸው በቂምና በጥላቻ የተልከፉ የተስፋዬ ገብረአግብ ደቀመዛሙርትና፤ የኦሮሞን የመብት ጥያቄ አወላግደው የሚያቀርቡ፤ በጃዋር መሃመድ ቀደኛነት የሚመሩ፤ የሚናገሩትና፤ከአፋቸው የሚወጣው መርዝ የሚያስከትለውን መዘዝ አርቀው የማይመለክቱ ፤እራሳቸውን ‘”የቁቤው ትውልድ “ ብለው የሚጠሩ፤ ለኦሮሞው
ሕዝብ ጥያቄ ከባድ ሸክሞችና ዕዳዎች እንጂ፤ እንኳንስ የኦሮሞው ሕዝብ የመብት ጥያቄ ሊያራምዱ ቀርቶ ለራስቸውም የማይጠቅሙ እንቅፋቶች ናቸው። እነዚህ መላቅጡ የጠፋባቸውና የተምታታባቸው ፤ያልነበረን” ነበረ፤ ያልሆነን ሆነ” ሆነ ብለው ከኢትዮጵያ የተለችና ተገንጥላ የምትኖር ኦሮሚያ ለመፍጠር ከላይ እታች የሚዳክሩ፤ ስምንት ሺ ማይልስ እርቀት ላይ ሆነው የፕሮፓጋንዳ ናዳና የስድብ መድፍ ለሚተኩሱ እራስ ፈጠር ጀግኖች ልትገነዘቡት የሚገባ አንድ  ሃቅ አለ። ይኸውም የኢትዮጵያ ማሕጸን ዥንጉጉር መሆኑን አትርሱ! አያችሁ! እናንተ በኢዮጵያ ከፍተኛውን ሕዝብ የምንወክል ነን ብላችሁ የምትመጻደቁበት የቁጥር ብዛት ከጋማሽ የሚበለጠው ሕዝባችሁ ከጉራጌው፤ ክትግሬው፤ ከወላይታው፤ ከስልጤው ከምትጠሉትም አብዛኛው ከማራው ሕዝብ ጋራ የተደባለቀ ነው። ለማስረጃ ያህል ስለራሴ ልንገራችሁና ወደዋንው፤ ወደተነሳሁበት ነጥቤ እመለሳለሁ።
አንድ ቀን የሰማኒያ ዓመት አዛውንት አጎቴን ለመጠየቅ ዋሽንግተን ፤ ዲሲ ሄጄ ከአጎቴና ከንልጆቻቸው ጋራ ስለቤተስብ ታሪክና የዘር አመጣጥ ስናወራ ፤ ሲያቀብጠኝ “ እኔ የጎጃሜም ዘር የለብኝም ፤ ኦሮሞውም አይዳሠሰኝም፤ ጥርት ያልኩ መንዜና ይፋቴ ነኝ “ እያልኩ ስመጻደቅ፤ አዛውንቱ አጎቴ ቀበል አደርጉና “ አልሰሜን ግባ በለው! ቅድመ ዓያትህ ወይዘሮ እህተ ማርያም ከየት የመጡ ይመስልሃል? አጼ ምንሊክ ( ዛሬ እናንተ  ከሂትለር አይለዩም የምትሏቸው) ደቡቡን ሲያቀኑ፤ አስታውሱ ሲወጉ አይደለም፤ የኔ አያት፤ ያንተ ቅድመ አያት፤ አቶ ያዩ የመጀመሪያ ሚስታቸው  ወይዘሮ አጥረሽዋል ሞተውባቸው በሃዘን ላይ እያሉ፤ ከዳግማዊ ምኒልክ፤ “ሰንጋ ፈረስህን ፤ ሰጋር ሲናርህ በቅሎህን ጭነህ ፤ አሽከሮችህን አስከትለህ  መጥተህ ተከተለኝ” የሚል መልክት ለአቶ ያዩ ደረሳቸው።የኔም አያት እንደታዘዙት በፍጥነት ወደመናገሻው ገሰገሱ። ንጉሰ ነገሥቱንም ተከትለው ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ። አቶ ያዩ ከግዳጃቸው ሲመሉ በውበቷ የትምደነቅ የኦሮሞ ሙሽራ ከነደንገጡሯና ከናሽከሮቿ  ይዘው መጡ። ያቺ ሸጋ ክርስትና ተነስታ እህተምርያም ተብላ በሕግና በይፋ የአቶ ያዩ ሁለተኛ ሚስት ሆነች። ከዚህም የተቀደሰ ጋብቻ አስራሶስት ልጆች ተወለዱ። ከነዚህም መሃል የኔ አባት አቶ ይጥናጋሻውና፤ የአንተ አያት አቶ ጣሰው ሁለቱ ናቸው።” ብለው ጫወቱኝ። ከዚህም በላይ የወይዘሮ እህተ ምርያም ገንደጡር ወይዘሮ ትሁኔና ፤ ወልደማርያም የሚባለው አስከትለት የመጡት የኦሮሞ ጎልማሳ ፤ ለአቶ ያዩ ልጆች ተድረው ብዙ ዘር ተክተዋል፤ አብዛኞቹም ዛሬም በሕይወት አሉ።
እኔም ከአገሬ ስወጣ እንኳን ስለዘር ግንድ አቆጠጠር ይቅርና ከህይወትም ጋራ በደንብ ሳልተዋወቅ ገና የሁለተደረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ስልሆነ፤ አጎቴ ዐይኔን ከገለጡልኝ በኋላ፤ ስለ እናቴም የዘር አመጣጥ ደግሞ አጥብቄ መጠየቅ ጀመርኩ። ከዚህም ያገኘሁት ውጤት እንደመጀመሪያው የሚያስገርምና ልብን በፍቅር ሰመመን የሚያሰምጥ ድንቅ ታሪክ ነው። የናቴ አያት አቶ አንዳርጋቸው ዩሱፍ በሰገሌ ጦርነት የወሎን ጦር እመሩ ከመጡት የጦር አበጋዞች መሃል አንዱ ነበሩ። የንጉስ ሚካኤል ሠራዊት በአጼ ኃይለስላሴ ሠራዊት(በኦሮሞው በፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ጦር የሚመራው) ድል ተምትቶ፤የወሎ ጦር ወደ መጣበት ወደ ወሎ” እግሬ አውጪኝ”እያለ ሲገሰግስ ይፋት ቆላ ላይ፤ ሲድረስ፤ የኔ ቅድመ አያት አቶ አንዳርጌ ዩሱፍ ከዘጠኝ የታጠቁ ተክታዮቻቸው ጋር በናቴ አያት በአቶ ወልደየስ ይማርካሉ። አቶ ወልደየስም አኚህን የወሎ መኳንንት፤ ለበቅሎና ለፈረሶቻቸው መኖውን አቅርበው፤ ለአቶ አንዳርጌም ከነተክታዮቻቸው የሚገባቸውን ክብር እየሰጡ በሚገባ እያስተናገዱ፤ ቁስላቸውን እየጠገኑ፤ ከድካማቸውም ተዝናንተው እፎይ እንዲሉ ያደርጋሉ። አቶ አንዳርጌም በዚህ ትህትናና አክብሮት በተሞላበት፤ እንደ ምርኮኛ ሳይሆን ልክ እንደ የቅርብ ወዳጅና የሹም እግዳ ያህል አድርገው ስላስተናግዷቸው ልባቸው በጥል ይነካል። አቶ ወልደየስም ከአንድ ፈሪሃ እግዚብሄር ካደረበት ክሪስቲያን እንድሚጠበቀው፤ለምርኮኞቻቸው ስቃቅቸውን አሰንቀው ወዳግራቸው ሲያሰናብቱ፤ የምርኮኞቹ አለቃ የኔ ቅድመ አያት አቶ አንዳርጌ ይነሱና ለማረኳቸው ለአቶ ወልደየስ “ እንደርሰዎ ያለ ጌታ አጥንቱን ይቆራኙታል እንጂ፤ እንዴት ተደርጎ እኔ ከርሰዎ እርቄ እሄዳልሁ! ይሉና አልሄድም ብለው ይቀራሉ። አቶ ወልደየስም ‘” ካልክስ እኔም ቀልቤ ወዶሃል” ይሉና ፈቃገኛ ይሆናሉ። እየዋሉ ያደሩም ሲሄዱ በሁሉም ነገር እየተግባቡ ይሄዳሉ።   
እኝህ ቁምና ዛላቸው ያመረ የወሎ ጉብል ዐይናቸው ከአቶ ውልደየስ ሴት ልጅ ላይ ያርፍና ልጃቸውን እንዲድሩላቸው አማላጅ ቢልኩ አቶ ወልደየስ “ልጄን ለእስላም አልድርም” ይሉና እምቢ ይሏቸዋል።አቶ አዳርጌም ለዚህ ችግር የለም ይሉና አጋምበር ማርያም ክርስትና ተንስተው የኔን ሴት ቅድመ አያት አግብተው ሁለት ወንዶችና፤ ሶስት ሲቶች ይወልዳሉ። ከሶስቱ ሴቶች ልጆች መሃል ወይዘሮ ሸዋረጋ አንዳርጌ የኔ አያት፤ የናቴ እናት ነች። አሁን ሁሉንም ነገር በጽሞና ሳገጣጥመው፤ አቶ አንዳርጌ በሃይማንት እስላም ብቻ ሳይሆኑ፤ ኦሮሞም ሳሆኑ አይቀሩም ብዬ እገምታለሁ። እንግዲህ የኔ ጥርት ያለው መንዜና ይፋቴነት እዚህ ያቆምና፤ከጎንደር ከትሁን ዘር በቅኔና በዜማ ከተካኑመካንንት ይጀምርና ከጋራው ከመገዘዙ ከመንዝ የገብስ ጥሬሾውንና፤ የገብስ ቆሎውን ቆርጥሜ፤ስንዴ ዳቦውን ገምጬ፤ ከጀግንነቱና ከጨዋነቱ ተክኜ፤  የይፋትን ትርንጎ በልቼ፤ነጭ ጤፉን በሰከነ ዶሮወጥ አጣጥሜ፤ ወደወሎም ሻገር ብዬ ውበቱንና ደግነቱን ወርሼ የቦርከናን ውሃ ጠጥቼ፤ከዚያም ፤ መሃል ኦሮሞ ገብቼ፤ በቀዘቀዘ እርጎና፤ እጅ የሚያስቆረጥም  ጨጨብሳ ተመግቤ፤በዳማ ፈረስ ጉግስ ለስጫወትና፤ ሽምጥ ለመጋልብ ሙሉ መብት ያለኝ ምንም የማይወጣልኝ ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ነኝ። 
ይህም ብቻ ሳይሆን ከትውልድ መንደሬ ዘመናዊ ትምህርት ለመከታትል በአሥር አመቴ ለአባቴ ታናሽ ወንድም ለልጅ አሥራት ታችበሌ በአደራ ልጅነት ሳደግ ተከባክበውና አንቀባረው አብረው ያሳደጉኝ የአጎቴ ባላቤት ወይዘሮ አበበች ዳባ  የኦሮሞ እመቤት ከምሆናቸውም በላይ፤ የእህቴ የሰበወንጌልና የውንድሜ የዶችተር መላኩ አሥራት እናት ናቸው። ከዱሮው  የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት የተማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያት እህቶቼ፤ ወይዘሮ ብርቄ ዳባንና ወይዘሮ አበበችን የማያውቅ የለም። 
ይህን ሁሉ ለመዘርዘር ያስገደደኝ ምክንያት በአጼ ምንሊክና በአማራው ተወላጅ ላይ የሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና፤ አጥንት የምሰብር ስድብና ዘለፋ፤ ዛቻና ፉከራ፤  መቆም አለበት፤ ገደብ ሊበጅለትም ይገባል  ብዬ ስለማምን ነው። ለመሆኑ የሻቢያ ቅጥረኞችና የተስፋዬ ገብረአብ ደቀዝሙሮች በኛ ላይ ጦር የሚያውጁትና፤ ምኒልክን የሚያህል አንጋፋ ባለታርክ ከፍ ዝቅ እያደረጉ የሚዘልፉት ከየትኛው ተራራ ላይ ቆመው ነው?  ትላንት በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ተምረው ዛሬ እይናቸውን የገለጡ እንደ ጃዋር መሃመድ ያሉ አፈ ጮሌዎች፤ የግብጽና የአክራሪ ዕስላም አገሮች ተመጽዋቾች፤ በኦሮሞ ወጣቶች ደም ለመነገድ ሲሞክሩ ይታያሉ። ይህ በጣም ያሳዝናል። በታሪክም፤ በሕግም ያስጠይቃል። አንድ “አውቃለሁ፤ ተምሬአለሁ” ከሚል እራሱን የቁቤ ትውልድ ብሎ የሚጠራ፤ እንዴት እንደ ተስፋዬ ገብረአብ ከመሰለ፤ የለየለት የመንደር ዱርዬና ጠመንጃ አንጋች፤ሥጋውንና ዕምነቱን ለማኛውም ከፍተኛውን ዋጋ ለሚክፍል ተጫራች ለሚሸጥና ለሚለውጥ አገር ካወቀው ቀላዋጭ ያበደ ውሻ ምን ዓይነት ትምህርትና መመሪያ ይቀበላል?
ኤርትራን ከናት አገሯ ከኢትዮጵያ አስገንጥሎ፤ ዛሬ የሚላስ የሚቀመስ የጠፋባትን ድሃ ኤርትራን ከፈጠረና የኤርትራን ሕዝብ በርሃብ አለንጋ ከሚገርፍ ከለየለት እብድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ምን ዓይነት ሰው ነው የሱን ምክር የሚሰማ? 
ስለ እብዶች ከተነጋገርን ዘንዳ፤ ማኑኤል ሆስፒታል በሕክምና ላይ ተግናኝተው የተዋወቁ ሁለት ጓደኛሞች  ነበሩ። ደህና ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ሳለ ፤በአንደኛው አነሻሽነት ከሆስፒታሉ አምልጠው ይወጡና ወደ ከተማ ይገባሉ። ከለታት አንድ ቀን ከረፋዳው ላይ አንደኛው ከአንድ ፎቅ ባልኮኒ ላይ ቆሞ፤ጓደኛው ከታች ከደረጃ ላይ ቁጭ ብሎ ጸሃይ ሲሞቅ፤ ከፎቅ ላይ ያለው ሽንቱ ይመጣበትና ከላይ ሆኖ ይለቀዋል። ከታች ያለው ቀና ብሎ ሲያይ ጓደኛው ሽንቱን እየለቀቀበት ነው። በዚህን ጊዜ ከታች ያለው ፈጥኖ ይነሳና እራቅ ብሎ ይቀምጣል። ከላይ ያለው “ አይዞህ !  አልሸናብህም፤ አርፈህ ተቀምጥና ጸሃይህን ሙቅ” ይለዋል። ሁለተኛውም “ እንግዲያውስ እሺ!” ይልና ተምልሶ ይቀመጣል። ልክ ከታች ያለው ሲቀመጥ፤ ከላይ ሆኖ ሲሸና የነበረው ከመቅጽበት ሽንቱን ቀጥ አድርጎ ያቆማል። አሁንም ካታች ያለው” ምን ነካህ ሽንትህን ቀጥል እንጂ!” ይለዋል። ከላይ ያለው “ አይ ብልጦ፡ዛሬስ ነቃሁብህ፤ ሽንቴን ይዘህ ጎትተህ ለጥለኝነው።”ብሎ ይመልስልታል። አዎ ዕውነቱን ነው ከዚያም ደህና ከሚታከምበት ሆስፒታል ያስኮበለልው እሱ ስለነበረ። ስለዚህ ወዳጆቼ የኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ ኢስያስን  ከሚያህል የለየለት እብድና ከናት አገራችሁ ከኢትዮጵያ ጠላቶች፤ ምክርም ሆነ የገንዝብ ችሮታ አትቀብሉ። ጠፍተው፤ ያጠፏችኋል። የሠይጣን ምክር ለአደምና ለሃዋም(አዳምና ሄዋን) አልጠቀመም፤ለናንተም አይበጅም።  
ደግሞስ ዛሬ በኛና በኢትዮጵያ ላይ ጦር አንስታችሁ በትዘምቱ እንደኔ አይነቱ ጉራምይሌ፤ሚስቶ በማን ላይ ጠመንጃ ደግኖ የሚተኩሰው? በረጋሳ ላይ ወይስ በጉግሳ? በጫልቱ ላይ ወይስ በአመቴ? ሁሉም ወገኔ ነው። ሕሊና ያለውና የሚስተውል ሰው ደግሞ በወንድሙ ወይም በእህቱ ላይ ጠመንጃ አይደግኖ፤አነጣጥሮ ተኩሶ ወገኑን አይገድልም። ታዲያ ወገኖች፤ እረጋ ብለን አለ ለምትሉት ችግር በጋራ፤ በመከባበርና በመቻቻል መፍትሔውን ብንፈልግ አይሻልም? 
ዛሬ ዓለም እየጠበበች፤ ሕዝብ እየተቀራረበ በጋራ አብሮ በመሥራት፤ በሚያስደንቅ ፍጥነት በሥልጣኔ እየገሰገሰ በሄደበት ዘመን ለናንተ ተገንጥሎ መኖር ለምን አስፈለገ? ደግሞስ አንድ ሰፊ የሕዝብ ብዛት ያለው ብሔር አናሳውን ለማቀፍ ይሞክራል እንጂ እንዴት እራሱን ዝቅ አድርጎ ፤ ከፋኝ፤ ከረፋኝ ብሎ ያኮርፋል? መገንጠልና መከፋፈል ለነማ በጀና? ለኤርትራ ወይስ ለሶማሊያ? ይታሰብበት እንጂ!!
እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ከጭንቅላታችሁ ሊገባና ልትረዱት ያልቻላችሁት አንድ ቁም ነገር አለ፤ ይኸውም በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ፤ ይኸ የሱማሌ መሬት፤ ያኛው የአማራ ክልል፤ ይኸ ደግሞ የኦሮሞ መሬት፤ ይኽ የጉራጌ፤ ሰሜኑ የትግሬ ደቡቡ የወልይታ፤ ምሥራቁ የከንባታ… ወዘተ የሚባል ነገር ጨሮሶ  እንደሌለ ወደፊትም እንደማይኖር ለመርዳት አለመቻላችሁ ነዉ። ሑሉም የኢቶጵያ መሬት ስለሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ የትም ሄዶ፤ ሕግና ሥረአትን አክብሮ፤ ሠርቶ የመበልጸግ፤ አርሶ የማምረት፤ ነግዶ የማትረፍና ተዝናንቶ የመኖር፤ ከማር ከወተቱ፤ከሥጋው ከሸቱ፤ የናት አገሩን እረደኤትና በረከት እኩል  ተካፍሎ የመብላት መብት አለው። ስለዚህ ይህን የቀን ቅዠታሁን አቁሙ። 
እንኳንስ የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና፤ የዓለም ሕዝብ የወደዳቸውንና ያደንቃቸውን፤ የጥቁር አፍሪካ ንጉሥ የነበሩትን፤ ገናናውንና ስመ ጥሩውን፤ ብልሕና አስተዋይ ጀግና፤ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ”ጊዜውን ቀድሞ የሄደ፤ እንደ ሰለሞን ጥበበኛ፤ እንደ ዮሐንስ ባለ ራእይ፤ እንደ ኢዮብ ትእግሥተኛ ነበሩ” ብሎ ግሩም ድንቅ የሆነውን ታሪካቸውን ከታሪክ መዝገብ ውስጥ በወርቅ ቀለም ስለጻፈላቸው ዘለዓለም ስማቸው ሲዘከርና ሲደነቅ ይኖራል። እናንተ ሂትለርም አላቸኋቸው፡ ሙሶሊኒ ፤ በድንጋይ ላይ የተቀረጸውን ስማቸውን መፋቅ አትችሉም። 
‘”ምኒልክ ሰለበ፤ የሴት ጡት ቆረጠ፤ በሰው ጭንቅላት እሩር ተጫወተ… እያላችሁ የምትነዙትን የማይመስልና የማይታመን የውሸት ውርጅብኝ እያወረዳችሁ ጆሮአችንን አታደንቁሩት። ምኒልክ ለዘመናት ተሸጉጣችሁ ከነበረበት ጫካና ጉር ውስጥ፡አውጥቶ፤ ዓይናችሁን የገለጠና ያስተማራችሁ፤ ለም መሬታችሁን አርሳችሁ፤ጥራጥሬ ዘርታችሁ፤ ጭ፡ንኩርትና በርበሬ ተክላችሁ መብላትን ያስተማራችሁ ምኒልክን መሆኑን አትርሱ።
ለመሆኑስ የወንድን ልጅ ብልት መስለብ ከየት የመጣ ልማድ ነው? የአማራው ወይስ የኦሮሞው? ይህ በአማራው ባሕል ፈጽሞ ያልተለመደና እጅግ በጣም የሚዘገንን፤ በሰው ልጅ ጭንቅላት የማታሰብ፤ በእግዚብሔርም ፊት የሚያስጠይቅ ኃጢአት ስለሆነ በክርስቲያን አማራ መጽሞ አይከጀልም። በናንተ በኩል ግን ወንድ ልጅ ገድላችሁ፤ ብልቱን ሰልባችሁ፤ ሰለባውን ካላሳያችሁ ማግባት እንኳን አትችሉም ነበር። እንዲያውም ይህ ድርጊት የጀግንነት ምልክታችሁም ብቻ ሳይሆን፤ ከሕብረተሰቡም መሃ በኩልነት መቀላቀል የምትችሉት ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ከፈጸማችሁ በኋላ ነበር። ሠይፍና ጎራዴ፤ ዱቢትና ወንበርቲ መታጠቅ የምትወዱት እናንተ ነበራችሁ። አማራውማ ነፍጡን ማን ወስዶበት? የአገሩን ድንበር ጥሶ የመጣውን ጠላቱን ግንባሩንና ደረቱን እየመታ አገሩን ሲያስከብር የቆየ ጀግና ሕዝብ ነው። ከሬሳ ላይ ቆሞ ዳንኪራ መርገጥና እጅና እግርን መቆራረጥ ግን በጣም ይዘገንነዋል፤ በጣም ይጸየፈዋል። ለውሸችትም ልክ ይኑረውና፤ ከቅሌታችሁ ትንሽ ቆጠብ በሉ።
አጼ ምኒልክ ከዚሀ ዓለም በሞት  ከተለዩ እኮ ከመቶ ከዓመታት በላይ አለፋቸው። ታዲያ የተረሳና የበሰበሰ ቂም በቀል ከመቃብር እየቆፈሩ ማውጣትና የሻረን ቁስል እየጎረጎሩ ማላዘን ምን ይባላል? የምንስ ያዙን! ልቀቁን ነው? ከትላንቱ ከዶክተር ማርትን ሉተር ኪንግ ጁኒዬርም፤ ከኔልሰን ማንዴላም ምንም የተማርነው የለም ማለት ነው? ይቅር መባባልን፤ መቻቻልን፤ ተከባብሮ አብሮ ለመኖርን የተሻለ ምርጫ መሆኑን ተዘነጋን? ደግሞስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ጠላት የሆነው ማነው? ወያኔ እኮ ነውነ ዛሬ ሁላችንንም ቁም ስቅላችንን እያሳጣ ፤ የሚገድለን፤ በስራት የሚያሰቃየን፤ በረሃብ አለንጋ እየገረፈ ለስደት የሚዳርገን።  ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት አጼ ምኒልክ ናቸው ወይስ ውያኔ?
እናንተ የኦሮምን ሕዝብ ነጻ እናወጣለን ብላችሁ ከተነሳችሁብት ዕለት ጀምሮ ማነው እንደ ዱር አውሬ እያደነ፤ ከተሸጎጣችሁበት ጉድጓድ ውስጥ እያወጣ እንድሪያ (ከርከሮ) ግልገል ጭንቅላታችሁን በክላሽ ጥይት እየበተነ ለአሞራ ምሣ፤ ለጅብ እራት የሚዳርጋችሁ? ወያኔ ወይስ አጼ ምኒልክ? ማነው ተወልዳችሁ ካደጋችሁበት ከያት፤ ከቅድመ አያቶቻችሁ መሬት እያፈናቀለ መድረሻ እያሳጣችሁ ያለው? 
“የኦሮሞን መሬት መውጫና መግቢያን፤ ዱር ገደሉን  እናውቀዋለን፤ ሰፊው  የኦሮሞ ሕዝብም ሙሉ ድጋፉን ሰጥቶናል፤ የማይገበር የጦር ኃይልም አለን እያላችሁ ስታደንቁሩን ይኸው ከአርባ ዓመታት በላይ አስቆጠራችሁ። በጣም የሚገርመው ግን በዚህ ረጅም ጂዜ ወስጥ፤ እንኳንስ በጠቅላላ ኦሮምን ነጻ ልታወጡ ቀርቶ አንዲት ፖሊስ ጣቢያ እንኳ አስለቅቃችሁና ተቆጣጥራችሁ አታውቁም። ሚኖሶታ ተቀምጦ አካኪ ዘራፍ ማለትና ኬንያ ተሸጉጦ መፎከርና መሸለል ምንም ፋይዳ አይሰራም።
የስንቱ ጀግና ደም የፈሰሰባትና፤ አጥንቱን የተከሰከሰባትን ኢትዮጵያን “‘ምስቅልቅሏን አውጥተን፤ እንደቀድሞው የሶቬት ሕብረትና ዩጎዝላቪያ እንበታትናታለን፤ ኦሮሞንም እናስገነጥላለን” የሚለውን ቅዠታሁን ብዙ ሳትርቁ ብታቆሙት ይመረጣል። ከኢትዮጵያ መሬት እንኳን ኦሮሞን የሚያህል ሰፊ ግዛቷ ይቅርና አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ ለማስገንጠል ማንም አይችልም። ዛሬም እኮ የጎበና፤ የባልቻና፤የኃብተጊኦርጊስ ዘር አለ! የናት ሃገሩን ሕልውና፤ የሕዝቧን አንድነት የሚያናጋ ጠላት ከውጪም ሆነ ከውስጥ ከተነሳ፤ ጀግናው የኦሮሞ ሕዝብ፤ እንደቀድሞው፤ በዳማ ፈርዳ እየጋለበ ሳይሆን፤በአዳፍኔና በታንክ ይጨፈልቀዋል። እናት አገሩ ከተንካችበት የጋምቤላው ጥቁር ነብር፤ እንደ ቀትር ዘንዶ በደርቱ እየተሳበ፤ እንድቀስት ተስፈንጥሮ ከጠላቱ ጉሮሮ ላይ ይጠመጠማል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ጀግናው የበላይ ዘር እንደሮኬት ተወርውሮ ከተገጣይ ምሽግ ዘሎ ይገባል። የመይሳው ዘር ጎንደሬ፤ የአሉላ ልጆች ከትግሬ፤የወሎ ጀግኖች የአዘቦ እራያ፤ ከመሃል ሸዋ መንዝና ይፋት፤መሬ፤ ሸንኮራ፤ቡልጋና ተጉለት፤አፋር፤ ወላይታው፤ ከንባታው፤ ቀፎውን እንደነቀነቅብት ንብ በቁጣ ተንስቶ፤ እንደ ማዕበል እየተውዘገዘገ ጠላቱን ይነድፋል። እናት አገሩ ኢትዮጵያ ከመገነጣተሏና ከመበታተኗ በፊት፤ጠላቱን ይዞ በሕይወቱ ያልፍላታል።
“ኢዮጵያዊነት በግድ ተጫነብን እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም “ ለምትሉ ፤ኢትዮጵያም እንደናንተ ዓይንቱን ስለማትፈልግ፤ የምትገቡበትና የሚወስዳችሁ፤  ካግኛችሁ፤ቅቤ እየለቀለቃችሁ በታመልኩበት አድባር ይሁንባችሁና፤ ሳትውሉ፤ ሳታድሩ፤ ዛሬ ኢትዮጵያን ለቃችሁ የመውጣት መብታችሁ የተጠበቀ መሆኑን እወቁ።ኧረ ጉድ ነው እናንተ! ያቶ መልስን “መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ” የሚለውን ምርቃታቸውን እረሳችሁት እንዴ? ይገርማል! ወያኔን የሚያህል ጠላት ዓይኑን አፍጥጦ፤፡ጥርሱን አግጥጦ፤ ሁላችንንም ፍዳችንን እያሰየን፤ በጠላት የተባብረ ክንድን በማሳት ፈንታ፤ እርስበራሳችን ስንናቆር፤ምን ያህል በጥላቻ ብንመረዝ ነው? የምርጫ ቅደም ተከተል መምታታት ማለት ይህ ነው።
አማራን አንገቱን እንደሩር እየቀላን ከኦሮሞ ክልል ወስጥ እናሶጣዋለን እያሉ ከመደንፋት በፊት፤የሚጠይቀውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት ያስፈልጋል።እኛ ግን ለኦሮሞ ተወልላጆች፤ ወንድሞችና እህቶቻችን ያለን ፍቅርና አክብሮት እንጂ፤ የተመረዘ ጥላቻ አይደለም። ከኦሮሞ ከሚያስደንቀው ባሕሉ፤እስከ ጀግነቱና በጠንካራ ሠራተኛነቱ፤ በደግነቱና በንግዳ ተቀባይነቱ፤ ልባችን የሚማረክ፤ ሙዚቃውና የሚያስደንቅ ዳንኪራውን እያዳመጥን አብረን በስሜት የምንደሰት፤ እኩል አብረን የመጣብንን መከራና ስቃዩንም፤ዓለምና ደስታውንም የተካፈልን፤ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች በመሆናችን እንወዳችኋለን።ከዚህ አልፎ ተርፎ ግን፤ጦር ሰብቆ፤ ጎራዴ መዞ፤ በአንገታችን እሩር ሊጫወት የሚመጣውን ከማንኛውንም ጠላት፤ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት እራሳችንን ለመከላክል ዝግጁዎች ነን።
ማንም ቢሆን  በጭንቅላቱም ሆነ በጉልበቱ እራሱን ለመከላከል ሁልጊዜ መዘጋጀት አለበት ብለን እናምናለን;።  “ከኛም ቤት እሳት አለነና” ሊያጠፉን የሚያደፍጡ ጠላቶቻችንን በቅድሚያ ሊያስቡበት ይገባል።  
ይፍሩ ኃይሉ 02/15/2014 Yhailu05@yahoo.com