Tuesday, July 31, 2012

EMEYE MENYILIK: የውጭ ጉዳይ ዜናዎች በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁ...

EMEYE MENYILIK: የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁ...
: የውጭ ጉዳይ ዜናዎች በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012) *አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው! *አምባሳደር ...
የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)

*አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!

*አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!

*አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!

*መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!

ህወሃት በጫካ እያለ ጀምሮ የድርጅቱን ገንዘብ ውጭ ሃገር በማንቀሳቀስ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት በምክትል ሚኒስትርንት ስም ውጭ ጉዳይን የሚያዘው ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስ ዜናዊ ከታመመ ጀምሮ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ሄድ ኦፊስ) አካባቢ ጠፍቶ መክረሙን በቦታው ያሉ ሰራተኞች አረጋግጠዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች እንዳረጋገጡት ብርሃነ የከረመው ብራስልስ ውስጥ መለስ ዜናዊን በቅርብ ሲያስታምም ነው። የመለስ ዜናዊ የመሞት ዜና በውጭ ጉዳይ አካባቢ የመረበሽ ድባብ እንደፈጠረ የገለጹት የዜናው ምንጮች ብዙ ዲፕሎማቶች ለማምለጥ አጋጣሚ እያመቻቹ መሆኑን ጠቁመዋል። ብርሃነ ገብረክርስቶስ መጠኑ ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደብራስልስ ይዞ መሄዱም ተያይዞ ተገልጿል። መለስ ዜናዊ በጸና መታመሙ ከተረጋገጠበት የዋሽንገተን ቆይታ አንስቶ በቅርብ ሲያስታምም የከረመው አምባሳደር ብርሃነ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ ማወቅ ተችሏል። ይህም በራሱ የማስታመሙ ስራ በሰውየው ሞት ምክንያት ማለቁን ይጠቁማል ይላሉ የውጭ ጉዳይ ሰራተኞች። የሚመለሰው አስከሬን ይዞ ወይም ቀብሩን ለማመቻቸት ይሆናል የሚል ግምት አለ።