Saturday, March 25, 2017

መቃብሩን ፈንቅሎና ደረማምሶ የተነሳው አማራ
_____________________________________
(ቬሮኒካ መላኩ)
………………………………
የዚህ ርእስ መነሻ ሃሳብ በመለስ ዜናዊና በአቦይ ስብሃት ነጋ በአንድ ወቅት የተነገረው " አማራንና ኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰብረን ቀብረነዋል " ከሚለው ፍሬ አልባ ንግግር መሰረት ያደረገ ነው።
የሩሲያ ህዝብና የአማራ ህዝብ በብዙ ነገር ይመሳሰሉብኛል ። የሁለቱን ህዝቦች የባህልና የሃይማኖት አምሳያነታቸውን ትተን በስነ ልቡና ከፍተኛ መመሳሰል አላቸው። ይሄን ነገር ሩሲያዊ ደራሲ አሌክሳንደር ቡላቶቪች " From Entoto to river Baro " በሚለው መፅሃፉ ውብ አድርጎ ገልፆታል ።

በታሪክ የተነሱ የአለም ሀያላን አገሮች የወደቁት የሩሲያን አፍንጫ ሊያሸቱ ሲሞክሩ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል። ከአውሮፓ እስከ ላቲን አሜሪካ ፣ከኤዥያ እስከ አፍሪካ አለምን ተቆጣጥሮ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት ሲያቀብጠው ወደ ሩሲያ ድንበር ማለፉን ተከትሎ በሩሲያ ጀግና ህዝብና በሩሲያ ጀግና በረዶ ከተሸነፈ በኋላ የአለም ሃያል መሆኑ አክትሞ ነበር።
በሁለተኛው የአለም ጦርነት አውሮፓን በደም እያጠበ የገሰገሰው አዶልፍ ሂትለር መቃብሩ ሳጥን ላይ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ሚስማር የገጠገጠችበት የሩሲያው ቀይ ጦር ነበር ።

የአንድ ህዝብ ብሄራዊ ሞራል በአንድ አጋጣሚ ፣በአንድ ሁኔታና በአንድ የታሪክ ወቅት ሊሰበር ይችላል።የሞራል መውደቅ ለልዩ ልዩ ህዝቦች በልዩ ልዩ ሁኔታወች ሊያጋጥም የሚችል ነው። ይሄን ብሄራዊ የሞራል ውድቀት ተከትሎ አንዳንድ ህዝቦች ዘጭ ብለው ሲወድቁና ሲንኮታኮቱ ሌሎች በጣም ጥቂቶች ህዝቦች ደሞ ሞራላቸው ንክች አይልም ።
እነዚህ ህዝቦች በከባድ ችግር ውስጥ ወድቀው ከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነውና ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳ ሞራላቸው አይወድቅም ።

በአስቸጋሪ ወቅት የዚህ አይነት የሞራል ልእልና አላቸው ተብሎ እንደ ማስረጃ ሊቀርብ የሚችለው የአማራ ህዝብ ነው ። ይሄን ነገር እኔ ያልኩት ሳይሆን ምእራባውያን ነጮች በደንብ ፅፈው ያስቀመጡት ሃቅ ስለሆነ ነው ።
እነዚህ የውጭ ፖሊሲ አውጭዎች የአማራ ህዝብ መንፈስ (Spirit) በቀላሉ እንደማይወድቅ አስረግጠው ለመንግስታቸው ሲገልፁ ነበር ።

እስኪ ይሄን የአማራ ህዝብ የሞራል ልእልና ጉዳይ በማስረጃ ለመደገፍ ልሞክር ። ሩዶልፍ ግራዚያኒን መቼም የማያውቅ ይኖራል ብዬ አልገምትም ። ቀደም ብሎ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት የሊቢያ አስተዳዳሪ የነበረውና በኋላም በኢትዮጵያ የጣሊያን አስተዳደር የበላይ የነበረው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ስለ አማራ ህዝብ ለበታች ሹሞቹ መመሪያ ሲሰጥ የሚከተለውን ተናገረ ………
" አማሮች ለጊዜው የተሸነፉ ይመስላሉ። ነገር በፍፁም አይሸነፉም ። ጊዜ ጠብቀው ቀን ቆጥረው የተሸነፉ የመሰሉት አማሮች ሳይታሰብ ብቅ ይላሉ ። "……… በማለት እንደተናገረ ፕሮፌሰር አልቤርቶ ስባኪ " Ethiopia under Mussoloni and Fascist experience " በሚል ርእስ በፃፈው መፅሃፍ ላይ አስቀምጦታል ።

ሌላው አስረጅ የምእራባውያን የኢትዮጵያ የፖሊሲ ጋይድላይን እየተባለ የሚጠቀስለት የኦስትሪያዊው ናዚ ባሮን ሮማን ፕሮችዝኪ የፃፈው "Abysiniya the powder barrel " የተባለው መፅሃፍ ነው።
ይሄ መፅሀፍ አውሮፓውያን ተረባርበው ጊዜ ሳያልፍባቸው አማራ የተባለውን ህዝብ አንገቱን ካላስደፉ በቀር ይሄ አማራ የተባለ ህዝብ አፍሪካን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ለአውሮፓ ስጋት እንደሚሆን " ይዘረዝራል (ገፅ 3)

አሁን አገራችን ወደአለችበት ተጨባጭ ሁኔታና የአማራ ህዝብ የሞራል ልእልና ጉዳይ እንመለስ ። በ 1983 የደርግ ውድቀትን ተከትሎ በሸአቢያ አንቀልባ ታዝሎ በለስ ቀንቶት አገሪቱን የተቆጣጠረው ወያኔ የመጀመሪያ ጥቃቱን የጀመረው በአማራ ህዝብ ላይ ነበር።
ያ ሁሉ የምድር መከራ ሲደርስበት ዝም ያለው አማራ የተሸነፈ የመሰላቸው መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ፊሽካ በመንፋት "አማራንና ኦርቶዶክስን ቀብረነዋል ። ከእንግድህ አይነሳም " በማለት አዋጅ አስነገሩ ። ይሄን ተከትሎ እውነትም አማራ የተቀበረ መሰለ ። ብዙ ህዝቦችን ሸወደ ። "ትንቢት ይቀድሞ ለነገር " ነውና አማራ በድንገት ሳይታሰብ መቃብሩን ፈነቃቅሎና ደረማምሶ ተነሳ ። "ሺንታም " እያሉ ሲዘባበቱበት የነበረው ህዝብ ረጋ ብሎ የራሳቸውን ሽንት ከሽንት ጨርቃቸው ላይ እየጨመቁ እንደጠጡና ዳይፐር ሳይረሱ እንድለብሱ አስገደዳቸው ።
አገሪቱ ተጠብቃ የቆየችው በሚስት፣ በርስትና በሃይማኖት ቀልድ የለም ብሎ ሲያምን በኖረው የአማራ ህዝብ ነው። የአማራ ነገስታቱ ችግር ሲገጥማቸው የመፈክር ጋጋታ፣ የመግለጫ ወረርሽኝ ወይንም ሲቻል አፍኖና አስፈራርቶ ህዝቡ ላይ ቀንበር ጭኖ ግንባር ወስዶ መማገድ፤ በዚህም እነርሱ ለሚበሉት እንጀራ የእንጨት ለቃሚዋ ልጅ ትሪ(ሰሃን)የሚሆንበት ስርዓት አልነበረም። የአማራ ነገስታት ማንኛውም ወረራ ሲያጋጥም ከቤተመንግስት ፣ ታቦታቱ ከቤተመቅደስ ወጥተው ከፊት ይመራሉ። እንደ ክርስቶስ መሆኑ ነው። ህዝቡ ከሁዋላ ይከተላል። እነርሱ ሳያደርጉ ሌላው እንዲያደርግ ያዘዙበት ግዜ የለም።
አዋጃቸውም በጣም ቀላልና ግልጽ ነበር። "ሚስትህን የሚደፍር፣ እርስትህን የሚቀማ ሃይማኖትህን የሚለውጥ ባእድ ወራሪ መቶብሃል። የቻልክ ተከተለኝ፤ ያልቻልክ በገንዘብህ ወይ በጸሎትህ እርዳኝ፤ ይኽንን ሰምተህ ዝም ያልክ ብትኖር ግን ማርያምን ብየሃለሁ ኋላ ትጣላኛለህ" አራት ነጥብ፤ የሚል ነበረ። ይሄ የአንድን ጀግና ህዝብ የሞራል ልእልና የሚያመለክት ምሳሌ ነው።
ወያኔ የሚባል የትግሬ እፉኝት ወደ አማራ ህዝብ ሲጠጋ የበግ ለምድ ለብሶ ፃድቅ መስሎ ነበር። የአማራ ህዝብም ቸር ህዝብ ነውና እቅፍ ድግፍ አድርጎ አጉርሶ ማላመድ ጀመረ ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ የመንፈስ ልእልና ፣ጀግንነትና ነፍጠኝነት ማንነቱ በሆነው ህዝብ ላይ መርዙን መትከል ጀመረ ። የአማራ ህዝብ ዘግይቶ መታለሉን አወቀ ።
ዛሬ ግን በዚህ ሁሉ የመንፈስ አርምሞ ሲታዘብ የኖረው የአማራ ህዝብ ከዓመታት ቦሃላ ተቀበረ ከተባለበት የአቦይ ስብሃት "መቃብር "ደረማምሶ ተነሳ ። ወደ ሃዲዱ በድል ለመመለስ የሚያስችለውን የብርሃን ፍኖት ፈልጎ ማግኘቱን ምልክት ማየት ተጀመረ ። ትናንት ከማንም በፊት የሳባን መንግስት ያቆምን ባለታሪክ የአማራ ህዝብ ዛሬም ተንኮታኩተን የማንወድቅ ህዝቦች መሆናችንን አሰረመሰከርን ።

FOOT NOTE
ቡላቶቪች From Entoto to river Baro በሚለው መፅሀፉ ስለአማራ አጠቃላይ ባህሪይ በገፅ 58 እንደሚከተለው አስቀምጦታል " If I allow myself a rather free comparison, this is how I would characterize the Amhara. He is talented and receptive, like a Frenchman. With his practicality, with the way he deals with those he has conquered and his governmental abilities, he is like an Englishman. His pride is like that of a Spaniard. By his love for his faith, his mildness of character and tolerance, he is like a Russian. By his commercial abilities, he is like a Jew. But in addition to all these characteristics, he is very brave, cunning, and suspicious ".

No comments:

Post a Comment