Wednesday, December 19, 2012

ጂጂና ቴዲ፣ እንደ ቦብ ማርሊ እንደ ፌላ ኩቲ


(ክንፉ አሰፋ)
ጃማይካዊውን የጥበብ ሰው ጋሪሰን ሃውክን በመንተራስ አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ አፍሮ ሰሞኑን
የለቀቁት 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'´ ነጠላ ዜማ በብዙዎች አድናቆትን እየተቻረይገኛል።
ብዙዎችንም አነቀቅቷል። ሙዚቃው የተለየ ነው፣ የሚያበረታታ እና የሚያነቃቃም ነው።
'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'! “
ብዙውን ግዜ በጦር ጀብዱ የፈጸመን ወይንም ድል ያደረገን ሰው ጅግና ብለን እንጠራዋለን።
ጀግንነትን በዚህ መስፈርት ብቻ ከለካነው -
ይህ ቀላሉ ጀግንነት ሊሆን ይችላል። ከባዱ እናእውነተኛው ጀግንነት ግን ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ማሸ
ነፍ መቻል ነው።
ምንም አይነት ጅብዱ ቢፈጽም ራእይ ግን የሌለው ሰው ጀግና ሊሆን አይችልም።  ህይወት ካለ
 ተስፋ አለ። ተስፋ ካለ ህልም አለ። ህልም ካለ ራዕይ አለ። ራእይ ያለው ሰው ነው ጀግና። 'ጀግና አይ
ፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!
የኢትዮጵያ አርቲስቶች በተለያዩ ወቅቶች ከፍቅር ወጣ ያሉ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ሲጫወቱ አ
ስተውለናል። በአብዮት ዘመን፣ በጦርነት ዘመን፣  በድል ዘመን፣  ወዘተ ... አብዛኞቹ ዘፈኖችም ሆኑቀረ
ርቶዎች ታዲያ ፈረንጆቹ ኢንስፓሬሽናል እንደሚሉት መንፈስን የሚያነቃቁና የጀግነነት ሞራልን ከፍ የ
ሚያደርጉ አልነበሩም።
አንቱ የሚባሉ የሃገራችን አርቲስቶች ካቀነቀኗቸው የፍቅር ዜማዎች አንዳንዶቹ የሚደንቁ
ናቸው።
“ቆዳዬ ተገፎ፣ ይሁንልሽ ጫማ፣
ስጋየም ይደገም፣ ላንቺ ከተስማማ..”
“ፍየል ቅጠል እንጂ፣ አትበላም እንጉዳይ፣
በጥርሷ ሰላሳ፣ ባይኗ መቶ ገዳይ...”
“አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣  እስቲ ቁጥር ጥሩ፣
እኔ ልጣራ ነው፣ እናንተ ሞክሩ የሚሉ ስንኞችን እናያለን::”
አርቲስቶቹ ከፍቅር ወጣ ሲሉ ደግሞ፣
“ይለያል ዘንደሮ...ይለያል!”
“አባረህ በለው... ፍለጠው ቁረጠው..”
“አያ ሆሆ ማታነው ድሌ ..”
“ደም በደም ይሁን መረማመጃው!” ወዘተ የመሳሰሉትን ስራዎቻቸውን መጥቀስ ይቻላል።
በርግጥ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገሮች የድምጽ ተሰጥኦ ብቻውን የአንድ ጥበብ ሰው መመዘኛ
ተደርጎ ስለሚወሰድ መልዕክቶቹ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚያዳምጥና የሚተች እምብዛም አይኖርም።
ችግሩ ያለው የአርቲስቶቹ የአካዳሚ እውቀት እና የግጥም ስራ ችሎታ ማነስ ላይ ነው።2
በአርቲስቶቹ ላይ በሚደረጉ ተጽእኖዎች እና አምባገነን መሪዎች አስገዳጅ ሁኔታዎች
ሲፈጠሩባቸው አልያም የአርቲስቶቹ መሃል ሰፋሪነት ባህርይ ለችግሮቹ ምክንያቶች ሆነው ሊጠቀሱ
ይታያል።
አንዳንድ እንደነዚህ አይነት ዘፈኖችና ቅኝቶች የሰውን ስሜት በጊዜው እና ለጊዜው ሊቀሰቅሱ
ቢችሉም ዘላቂነት ላይኖራቸው ይችላል።  ግዜያዊም ሆነው የመጥፋት እድላቸው የሰፋ ነው።
በዚያኑ መጠን ደግሞ… “ቅንድቡ ያማረ…” ብሎ ወንዱ ለወንድ አቀንቅኖ ሲያበቃ፤ ቅንድቡም
ወደ አፈር፤ ዘፋኙም ወደ ማፈር ደረጃ የሚሸጋገሩበትን አጋጣሚ ታዝበን እናልፋለን። እንግዲህ
በአገርኛ ለአገር ልጅ የሚቀነቀኑ መልካም ዜማዎች እንዳሉ ሁሉ፤ ጭራሽ የሃፍረት ማቅ አጥልቀው፤
እኛንም የሚያሸማቅቁ አይጠፉም። በዚያው መጠን ደግሞ በአገራችንም ሆነ በውጭ አለም ተስፋ ሰጪ
ሙዚቃዎችን በመጫወት የህዝብን መንፈስ ከፍ ለሚያደርጉት ከፍ ያለ ክብር ያለን መሆኑ
ይሰመረበት።
በሌላ በኩል
የሬጌ ሙዚቃ ዘውግ ብዙውን ጊዜ የሚያጠነጥነው ተስፋን በሚሰጥ፣  መንፈስን በሚያበረታታና  የጀግ
ንነት ሞራልን በሚጭር የዜማ መልእክቶች ላይ ነው::  የሬጌ እና የአር. ኤንድቢ. ዘውግ በማቀላቀል የ
ሚያቀነቅነው አርቲስቶቹ ጋሪሰን ሃውክም ስለ ተስፋ ብዙ አዚሟል።
አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ ተንተርሰው ያዜሙትም  'ሰርቫይቭ'’ በተሰኘው የጋሪሰን አልበም ነው -
  የመኖርን እና የመቆየትን ተስፋ የሚያጭር የጋሪሰን የሙዚቃ ስራ። ጂጂ እና ቴዲ ውብ የአማርኛግጥ
ም ጨምረውበት ለሙዚቃው ሌላ ኢትዮጵያዊ ነፍስ ዘሩለት።
እነዚህ ሁለት አርቲስቶች የሚጋሯቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ሁለቱም ወደ ሬጌው ዘውግ የሙዚቃ
 ቅኝት ያዘነብላሉ።   ሁለቱም ልዩ የጥበብ ተሰጥዖ ያላቸው፣  በስራቸው የሌላ ጥገኛ ያልሆኑ፣
ሁለቱም የሚሰሩትን የሚያውቁ፤ የሚያውቁትንም የሚሰሩ አርቲስቶች ናቸው። ሁለቱም ለጥበብ ስራቸ
ው መስዋእትነትን የከፈሉ ናቸው።  የህዝብን ቀልብ ሊስቡ ፤ የህዝብን ልብ ሊገዙ ያስቻላቸውምስጢር
ም ይኸው ነው።  የኢትዮጵያው የሙዚቃ አባት አቶ አለማየሁ ፈንቴ በኢቲቭ ቀርበው የሚያደንቁትን
የሙዚቃ ሰው ሲጠየቁ ሳይግደረደሩ ነበር "ጂጂ" (እጅጋየሁ ሽባባው) ፤ ሲሉ የመለሱት።
የኦሮምኛ ሙዚቃ ባህሉን ሳይቀይር አገርኛና አለም አቀፍኛ ቃናና እውቅናን የሰጠው ታዋቂው ድምጻዊ
 አሊ ቢራ ደግሞ ከዘፋኞች ቴዲ አፍሮን እንደሚያደንቅ በዚሁ ቴሌቭዥን ተሰምቷል።
በአለማችን የጥበብ ሰዎች ሚና ጎልቶ የሚታየው ተፈጥሮ ባደላቸው የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፤
  እነዚህ ሰዎች በጥበብ ስራቸው ውስጥ ለህዝብ በሚያስተላልፉት መልእክትም ጭምር ነው።
ጥበብ አንድን ህብረተሰብ ይቀርጻል:: የሙዚቃ አርቲስቶች ስለ ስጋዊ ፍቀር ብቻ ሳይሆን ስለ ህዝብ፣ ስ
ለ ሃገር፣ ሰለ መብት ወዘት የሚቀኙዋቸው ቅኝቶች ህብረተሰብን የመለወጥ ሃይል አላቸው።
የናይጄሪያው ፌላ ኩቲ እና ጃማይካዊው የሬጌ አባት ቦብ ማርሊይ በዚህ ረድፍ ያበረከቱት ሚና ቀላል
አይደለም።
እናቱ በጸረ-
 ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ታጋይ ፤ አባቱ ደግሞ የቤተ ክርስትያን አገልጋይ ቄስ ነበሩ -
 ፌላ ኩቲ። እ.ኤ.አ. በ1958 ህክምና እንዲያጠና ቤተሰቦቹ ወደ ለንደን ቢልኩትም፣
የህክምና ዶክትሬቱን ወደ ጎን በመተው ሙዚቃ ማጥናትን መረጠ። ሁለቱ ወንድሞቹ በህክምና ተመር
ቀው ዶክተር ሲባሉ ፌላ ኩቲ ግን ዶክተር ሆኖ አንቱ መባልን አልመረጠም።
 የሙዚቃውን ትምህርት አጠናቅቆ ልዩ የጃዝ ባንድ መሰረተ። ፌላ ኩቲ ሃኪም ሆኖ ስጋዊ በሽ
ታን ከማከም የላቅ ህክምና እንዳለ የተረዳው ገና በለጋ እድሜው ነበር። የጥቁር ዘር መረገጥ እናየበታች3
ነት ስሜት ያመጣው በሽታም ህክምና እንደሚያስፈልገው ጠንቅቆ የተረዳ ባለ ራእይ መሆኑን የኋላ ኋላ
 ስራዎቹ መስክረዋል። የሰው ልጅ ጭቆና እንዲወገድ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በሙያውአበርክቷል።
ከነጮች የበላይነት እና ከአንባገነኖች ግፍ ህዝብ ነጻ እንዲሆን በሙዚቃው የታገለ ጀግና ነው።  ለዚህም
 መስዋእትነትን መክፈል ነበረበት።
ፌላ ኩቲ በሙያው ያመነበትን በማድረጉ ምክንያት ታስሯል፣ ተደብድቧል፣ ከሃገርም እንዲወ
ጣ ተደርጓል።  ፌላ ጥቁሮችን በመንፈስ ነጻ የማውጣት ህልም ነበረውና አሜሪካ በመጓዝ ‘ ብላክ
ፓወር’  የተሰኘ ንቅናቄን መድስርቶ ነበር። የኋላ ኋላ የአሜሪካ ባለስልጣናት ከሃገር እንዲወጣ
አደረጉት እንጂ።
አንባገነን መሪዎች በአካሉ ላይ ያደርሱት የነበረው ስቃይ ለሱ ኩራቱ ብቻ አልነበረም። የባሰ መንፈሰ ጠ
ንካራ አደረገው።  በአለም ዘንድ ዝናንና ከበሬታንም አተረፈለት።
ወደ ሬጌው ዘውግ ስንገባ ደግሞ የቦብ ማርሊ ስራዎች እናገኛለን። የቦብ ስራዎች በእጅጉ
የሚያንጸባርቁት በማህበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው። ቦብ ለጥቁሮች በተለይ ለአፍሪካ ነጻነትና
ሰላም ብዙ አቀንቅኗል። በተለይ ዋር፣ ጌት አፕ ስታንድ አፕ እና ኦነ ላቭ በሚሉት ስራዎቹ ሚሊዮኖችን
ከማነቃቃት አልፎ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።
ወደ ሬጌው ዘውግ ስንገባ ደግሞ የቦብ ማርሊ ስራዎች እናገኛለን:። የቦብ ስራዎች በእጅጉ
የሚያንጸባርቁት በማህበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው። ቦብ ለጥቁሮች በተለይ ለአፍሪካ ነጻነትና
ሰላም ብዙ አቀንቅኗል። በተለይ ‘ዎር’ ፣ ‘ ጌት አፕ ስታንድ አፕ’ ፣  እና ‘ ዋን  ላቭ’  በሚሉት ስራዎቹ
ሚሊዮኖችን ከማነቃቃት አልፎ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በቦብ ማርሊ ስራዎች የተነሳሱ
የሬጌ አቀንቃኞች ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሆነዋል።
 
ሙዚቃ በህብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንዳለው በተለይ አንባገነን መሪዎች ጠንቅቀው
ያውቁታል። በ1800ዎቹ ናፖሊዮን ንግስናውን ሲያውጅ በወቅቱ አንቱ የተባለው ሲንፎኒስት
ቤትሆቨንን ሰስተኛ ስራ በቦናፓርት ስም እንዲወጣ አዞት ነበር። ቢቶቨን ግን ከህይወቱ ይልቅ ጥበቡን
መርጦ አሻፈረኝ አለ:: አቶ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከትማ ከንቲባ በነበሩ ግዜም ከታፊ
አርቲስቶችን ሰብስበው አርከበ የሚል አልበም እንዲለቁላቸው ጠይቀው ነበር።  አርቲስቶቹ ግን
እንቢም እሺም ሳይሉ እንዳመለጡ አጫውተውኛል።  አርቲስቶቹ የተጠየቁትን ቢያደርጉ ኖሮ ህዝብ
ዋጋ ያስከፍላቸው እንደነበር ማጤናቸውም ትልቅ ነገር ነው።
እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ ተለቆ የነበረው We shall overcome (እንወጣዋለን) የሚለው የአፍሪካ
አሜሪካን የነጻነት መዝሙር በህዝብ አእምሮ ሰርጾ በመግባት ለጥቁሮች የነጻነት ትግል ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ነበረው።
ዛሬ እነ ጂጂ እነ ቴዲ ተስፋን ስለመሰነቅ አቀነቀኑ። ተስፋ ባለመቁረጥ ውስጥ ስለሚገኝ
ጀግንነት።  ተስፋ ያለው ሰው አይፈራም።  የሚገድል ሳይሆን የማይፈራ ሁሉ ጀግና ነው።
'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!