_ልዋጭ___
መልካም አባት ለፍቶ
...ጥሮ..ተጣጥሮ..
ጥበብን..ዕውቀትን..
...እውነትን አስተምሮ
ልጁን ማየት ሽቶ
...በትምህርት በልጽጐ
በሕይወት መንገድ ላይ
...ለቀቀው ነጻ አ'ርጐ::
"ለወግ..ለማዕረግ..
...ደርሶ ለቁምነገር
ኩራትና ክብር..
...ይሆናል ለሀገር::"
ብሎ ሲጠብቀው..
ድንገት ቢያዳምጠው
...ልጁ ሐሰት ሲናገር
አባት ተጨነቀ
ራሱን ጠየቀ::
"ማነው ያስተማረብኝ?..
እውነተኛው ልጄ..
ለምንድ ነው የዋሸው?.."
ሰበቡን ለማወቅ..
ነገረ-ጉዳዩን..በጥልቀት ፈተሸው::
እስከመንፈቅ ሌሊት..
እንቅልፍ አልባ ሆኖ..
...ቁጭ ብሎ እሚያመሸው
ወዲያው ግልጽ ሆነለት
ኢቲቪ እንደሆነ..ልጁን ያበላሸው::
እሳት ጐርሶ ለብሶ
...አባት ተቆጥቶ
ያንድ ልጁን እናት..
...ባለለቤቱን ጠርቶ
በፍጥነት እንዲህ አላት;
"የዛሬው ሳያንሰው..
ደ'ሞ የነገውን ሰው..
...መጻኢውን ተስፋ
ውሸት በማስተማር
...ይዞት ከሚጠፋ
ልዋጭ ፈልጊና..
ይኼን ቴሌቪዥን..
...ለውጪው በሳፋ::
ከሳፋ ካነሰ..
ዋጋው ከረከሰ..
...ቀይሪው በጭልፋ!!!"
* * *
__ፋሲል ተካልኝ አደሬ__
No comments:
Post a Comment