Sunday, October 21, 2012

ጁንዲን ሳዶ ከሃገር እንዳይወጡ ታግደዋል የበረራ ጉዞአቸውም ተሰረዘ!


ጁንዲን ሳዶ ከሃገር እንዳይወጡ ታግደዋል የበረራ ጉዞአቸውም ተሰረዘ!

Junedin-Sado
ጂነዲን ሳዶ ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸውን ኢንዲያን ኦሽን ዘገበ።እንደ ኢንዲያን ኦሽን ዘገባ፤በቅርቡ ከኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚነት በግምገማ የተሻሩት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአገር ሊወጡ ሲሉ በደህንነት ሀይሎች ተይዘው ተመልሰዋል።አቶ ጁነዲን ለህክምና ወደ ታይላንድ እንደሚሄዱ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአቶ ደመቀ መኮንን ያሳወቁ ቢሆንም፤ በረራቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል።ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀቢባ ከ ሳዑዲ ኤምባሲ የሀይማኖት አታሼ ቢሮ 50 ሺህ ብርና 500 ቁርዓን ይዘው ሲወጡ ተይዘዋል ተብለው በ እስር የሚገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ሳቢያ ከ ስራ አስፈፃሚነታቸው የተነሱት አቶ ጁነዲንም ተመሣሳይ ዕጣ ይገጥማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። የአቶ ጁነዲን ያለመከሰስ መብት እንደተነሳ ባሳለፍነው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል ::
የታገዱበትን ዋነኛ አላማ መንግስት ሊገልጽላቸው አልፈለገም …ለምን ያህል ጊዜ የቁም እስረኛ ሊያደርጋቸው እንደሚችልም ምንም ማረጋገጫ ባይኖርም ምናልባት የክስ ቻርጁ እስኪጠናከር ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።
አጠቃላይ የኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተርን ዜና በትላንትናው እለት አያይዘን በአፍሪካ ገጽ ላይ ማቅረባችንንም ልናስታውስ እንሻለን(source:maledatimes.com)

No comments:

Post a Comment