Tuesday, October 9, 2012

የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል


የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል
(ለኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራዊ ፍትህና መብት፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚታገል ድርጅት)
በመከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በቤት ውስጥ አገልጋይነት ለሚሠሩ ሴቶች ድጋፍ
የሚደረግ የእግር ጉዞ በዓለምአቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ሴቶች መብቶች ለማስከበር
የተቋቋመው ድርጅት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (የኢሴመማ)
ለኢትዮጵያዊያት ሴቶች ድጋፍ የእግር ጉዞ አዘጋጅቷል።
የጉዞው ዕለት የፊታችን ኦክቶበር 20/2012 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት
10/2005 ዓ.ም ከዋሽንግተን ዲሲው Freedom Plaza (14
th
& Penn. Ave
Northwest Washington DC.) ይነሣና United States Capitol ደርሶ ወደ
Freedom Plaza ተመልሶ ይጠናቀቃል። ጉዞው የሚጀመረው ከጠዋቱ በ9፡30
ሲሆን በ12፡30 ይፈጸማል።
የእግር ጉዞው ዓላማ በመካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በቤት ውስጥ አገልጋይነት
ከባርነት ባልተናነሰ ሁኔታ እጅግ አሠቃቂ ኑሮ ስለሚገፉ ኢትዮጵያዊያት ሴቶች
ለማሳወቅ ነው።
ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ በመካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በአገልጋይነት ስለሚሠሩ
ኢትዮጵያዊያን ኑሮ ተገንዝቦ እጅግ የደነገጠው የዓለም ደቻሳን ቪዲዮ ከተመለከተ
በኋላ ነው። ቪዲዮው ባለፈው መጋቢት ቤይሩት በሚገኘው በኢትዮጵያ ቆንሲላ
ደጃፍ ላይ ዓለም ደቻሳ በአሠሪዋ እየተገፈተረችና እየተደበደበች ያለ ፈቃዷ በግድ
መኪና ውስጥ ስትወረወር ያሣያል።
ያ ቪዲዮ መላውን ዓለም የሰቀጠጠ ነበር። በኋላም ዓለም “እራሷን ገደለች” ተባለ።
ሆኖም ዓለም ደቻሳ በመካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በሰው እጅ ከተገደሉ ወይም
እራሣቸውን ካጠፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያት ሴቶች አንዷ ናት።
ባለፉት አሥርት ዓመታት በመካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በቤት ውስጥ ሠራተኛነት
የሚያገለግሉ ኢትዮጵያዊያት ሴቶች ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ወደዚያ ለሥራ
የሚጎርፉ ሴቶች ቁጥር በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደማይቀንስም ይታመናል።
ለብዙዎች ሴቶች ከኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች ሄዶ በቤት ውስጥ
አገልጋይነት መተዳደር ብቸኛው የህይወት ተስፋቸው ነው። አብዛኞቹም ከድህነት
እንደሚያወቸው ብቸኛ መንገድ አድርገው ያዩታል።አሣዛኙ እውነታ ግን ሴቶቹ ልክ ወደሚላኩበት አገር ደርሰው ሥራ እንደጀመሩ ነው
በቀጣሪዎቻቸው የመብቶች ረገጣው የሚጀመረው። ይደበደባሉ፣ ይሰደባሉ፣
ይደፈራሉ፣ ደመወዝ አይከፈላቸውም፣ እረፍት ወይም ከቦታ ቦታ የመዘዋወር
ፍቃድ የላቸውም።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚሠሩበት ሃገርም ሆነ የገዛ ሃገራቸው መብቶቻቸው
እንዳይደፈሩ አይከላከሉላቸውም።
የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል - CREW በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች
ተቀጥረው ለሚሠሩ ሴቶች ፍትህ ለጠየቁ ቡድኖችና ድርጅቶች ሁሉ በዚህ አጋጣሚ
ምስጋናውን ያቀርባል።
የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል ይህን ግፍና በደል ለማስቆም፣ ዓለምአቀፍ
ትብብር በመጠየቅ ጭምር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ የዘመቻችን ዋና ዓላማ እነዚህ
ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ የሚማጠኑ ሴቶች ድምፅ እንዲሰማ ነው!
ይህንን ዘመቻ ከግብ ለማድረስ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል - CREW ፤
- - መንግሥታት ሁሉ በሃገራቸው ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ የባዕዳን
ሴቶችን መብቶች የሚያስከብሩ ሕጎችን እንዲያወጡ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፤
- -በሺሆች የሚቆጠሩ ሌሎች የቤት ውስጥ አገልጋይ ሴቶችን ወደ መካከለኛው
ምሥራቅ አገሮች ከመላኩ በፊት ሁኔታው ለደህንነታቸው ምቹ መሆኑን
እንዲገመግም፤
ሠራተኞቹን የሚረከቡ አገሮች፤
- ለማንኛውም ሠራተኛ እንደሚደረግ ሁሉ የቤት ውስጥ አገልጋዮች ሕጋዊ
ኮንትራትና የመብቶች ጥበቃ ሠነድ እንዲኖራቸው እንዲያደርጉ፤
በሃገር ውስጥ ኢትዮጵያዊያትን ለሥራው የሚመለምሉ ኤጄንሲዎች፤
-  - -ሴቶቹ ምንም ዓይነት አካላዊ ጥቃት የማይደርስባቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ፣
ኢትዮጵያዊት የቤት ውስጥ አገልጋይ ማናቸውም ጥቃት ከደረሰባት የኢትዮጵያ
መንግሥት ጊዜያዊ መጠለያ እንዲሰጣት፤- የሞቱ ሴቶች በምን ምክንያት እንደሞቱ ተገቢው ሁሉ ምርመራ እንዲደረግ፤
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል - CREW በመካከለኛው ምሥራቅ
የሚገኙ የሴቶች ድርጅቶችና የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅቶች ይህን አሣዛኝ
ድርጊት ለማስቆም ከኛ ጋር በመተባበር እንዲሠሩ ጥሪ እናቀርባለን።
የኢሜል አድራሻችን፡- ethiowomen@gmail.com ነው፤ ፃፉልን።

No comments:

Post a Comment