Saturday, April 6, 2013

የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ

የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ

ክፈሌ ስንሻው አኔሳ
ዳዊት ከበደ ያለተቀናቃኝ አውራምባ ታይምስ የተባለ ጋዜጣን ሲያስትም ቆየ። እንደ ዳዊት ለ2 አመታት ታስረው የተፈቱት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና እስክንድር ነጋ የጋዜጣ
Journalist Dawit Kebede, Awramba Times editor
ከፌስ-ቡክ የተገኘ
ህትመት ፈቃድ ተከልክለው ለእሱ  ተፈቀደ። ለምን ለእሱ ተፈቀደ ብሎ የጠየቀ አልነበረም፤ በእስር ቤት ተፈትኖ የወጣ በመሆኑ ለወያኔ ያድራል ብሎ የሚጠረጥር  ሰው አልነበረምና። ዳዊት  አውራምባን ማሳተም ቀጠለ። ጋዜጣው ጥሩ ስራ እየሰራ ባለበት ጊዜ ዋና አዘጋጁ “ልጁን አላምነውም ብሎ” ጥሎት ጠፋ። ዋና አዘጋጁ በወቅቱ ይናገር የነበረውን ማንም አላመነውም ነበር፤ ቀጥሎም ተረበኛው አቤ ቶክቾው ድርጅቱን ለቀቀ።
አውራምባም፣  ሄደች ሄደችና  ገበያዋ ሲደራ፣ መሀል መንገድ  ቀረች ቆማ ተገትራ ተባለች፤ “ጠንካራ ዘገባዎችን” ማውጣት አቆመች፣ ዜናዎቿ ሁሉ ” ጁነዲን ምሳ በላ፣ አባዱላ ውቅሮን ጎበኘ” ወዘተ ሆነ ። “ዳዊት ከበደ መፍራት ጀምሯል” ተብሎ በአዲስ አበባ መወራት ጀመረ፤ በመሀሉ ሲፒጄ የሚባል ድርጅት የአመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ ሸለመው፤ የዳዊትም ስም እንደገና  ከፍ ከፍ አለ። ሁላችንም ዳዊት በመሸለሙ (የመጀመሪያው የሲፒጄ ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ በመሆኑም) ደስ አለን፤ እኔ በግሌ በጣም ተደሰትኩ። ዳዊት ግን አንድ ፈተና ገጠመው- በአገር ቤት። ዳዊት ሽልማቱን ለመውሰድ እዚህ አሜሪካ ሲመጣ መቀናጣት አበዛና ስራውን ዘነጋው። በአሜሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሰጠውን ድጋፍ ሲመለከት  “ፕሬዚዳንት ኦባማን” የሆነ መሰለው። ስራውን ትቶም አሜሪካ ማውደልደል ጀመረ። እናም በአገር ቤት፣  አንድ ተመስገን ደሳለኝ የተባለ ጋዜጠኛ “ፍትህ” የሚባል ጋዜጣ አዘጋጅቶ ዳዊት እየፈራ የማያወጣቸውን ዘገባዎች እያተመ ማውጣት ጀመረ። ሁሉም ፊቱን ከዳዊት ወደ ተመስገን አዞረ፤ አውራምባ ወደቀች፤ ኪሳራ ውስጥም ገባች፤ ዳዊትም “ወያኔ አስፈራራኝ” አለና ከአገር ኮበለለ። እንዴት እንደወጣ እግዚአብሄር ይወቅለት፤ ራሱን ወደ እስር ቤት በመወርወር፣ ሲፒጄ የሰጠውን ሽልማት ትክክል ነው በማስባል፣ ለሲፒጄም መኩሪያ ይሆናል ስንል፣ እነ እስክንድርን ነጋን ወይኒ ሸኝቶልን መጣ።
አሜሪካ ላይ መንጎማለል ያለመው ዳዊት በኢሳት ላይ ቀርቦ መግለጫ ሰጠ፤ እኛም ሰምተን፣ በሆዳችን ሲፒጄን እንዳዋረደ ቢገባንም፣ እዚህም ሆኖ ከታገለ አንድ ነገር ነው ብለን ድጋፋችንን ሰጠነው። ኢሳት ልጁን በተደጋጋሚ በማቅረቡም፣ ኢሳትን አምነን አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽን ሲጀመር፣ ድረገጹን እየከፈትን በማንበብ በገንዘብ እራሱን እንዲደጉም እገዛ ማድረግ ጀመርን።
ዳዊት እንዳለመው በአሜሪካ እንኳንስ “ኦባማ”ን ሊሆን ቀርቶ፣ አንድ ተራ ሰው መሆን አቃተው፣ በምን ምክንያት እንደሆን አይታወቅም እነ ኢትዮ-ሚዲያን መጥላት ጀመረ። ትንሽ ቆይቶም በኢሳት ላይ ዘመቻ ጀመረ፤ “እንዴት ሰው የበላበትን ወጪት ይሰብራል?” ብለን አይተን እንዳላየን አለፍነው። ኢሳት አሳድጎት፣ ኢሳት አስተዋውቆት፣ በኢሳት ላይ መዞሩ በጤናው ነው ስንል ጠየቅን፤ ኢትዮሚዲያስ ቢሆን ስንት ክብር ሰጠው? ቀጠለና አቤ ቶክቾውን በፓልቶክ  ቀጠቀጠው። ይህ ሲገርመኝ እንደ “ፋና ወጊ” የማየውን አርበኛውን ታማኝ በየነን መነካካት ጀመረ፤ የት ይደርሳል የተባለ ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው ሆነ ነገሩ። እኔም  ሲፒጄን፣  ኢሳትን፣  ኢትዮሚዲያን መርገም ጀመርኩ፣ አይጥ የሆነውን ልጅ አንበሳ አድርገው በማቅረባቸው። “እኛንም ጎዱን፣ እሱንም ጎዱት”። አንድ ሰው የማይገባውን ክብር ሲያገኝ መሸከም ያቅተዋል፤ ዳዊት ላይ የታየውም ይህ ነው። ሽልማቱ ለሲሳይ ወይ ለእስክንድር ቢሰጥ ኖሮ እነሱ አያያዙን ያውቁበት ነበር፤ ሲሳይ የፔን ኢንተርናሽናል ተሸላሚ ነው፣ እስክንድርም እንዲሁ፤ ሁለቱም ግን እንደ ዳዊት አልፎለሉም፤ ወይም ልታይ ልታይ አላሉም፤ የበለጠ ለመስራት የበለጠ መስዋትነት ለመክፈል ተዘጋጁ እንጅ።
ከስንት ጊዜ በሁዋላ ዛሬ አንዱ ደውሎ “አውራምባን አየኸው” አለኝ?  “ዌብሳይቱ አለ እንዴ? ብየ መለስኩለት። “በኢሳት ላይ የሰራውን ተመልከተው” አለኝ።  ተመለከትኩት። ይህን የሰራው  የሲፒጄው ተሸላሚ ዳዊት ነው? ብየ ራሴን ጠየቅሁ። ዘገባው በ59 የአማራ ተወላጆች ላይ ስለደረሰው አደጋ ነው፤ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ትዝታ በላቸው፣ አንድ ዘገባ አቅርባ ነበር፤ “ኢሳት የዘገበው ትክክል አይደለም” ለማለት ፣ ጋዜጠኞች እንደሚሉት “ለማስተባበል” የፈለገችች ይመስላል፤ ኢሳትም የማስተባበያው ማስተባበያ ዜና ለመስራት የፈለገ ይመስላል። ኢሳት፣ የትዝታን ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ የራሱን ሰው አቅርቦ አሰማ፤ የቪኦኤም የኢሳትም ያልሆነው ዳዊት ከበደ  የኢሳትን ግማሹን ዜና በመቁረጥ (ገበሬው የሚናገሩትን) ትዝታ የምትናገርበትን ክፍል ብቻ በማቅረብ ኢሳትን ለመወንጀል ሲሞክር ይታያል፤ የኢሳት ዜና ስሜት የሚሰጠው ገበሬው የሚናገሩበት ክፍል ሲገባ ነው። ዳዊት ግን ያንን ክፍል ሆን ብሎ ቆረጠው። ዳዊት ቢዘቅጥ ቢዘቅጥ በዚህ ደረጃ ይዘቅጣል ብየ አላስብም ነበር፤ ወይ የሲፒጄው ተሸላሚ!
ይህንን በማስመልከት በድረገጹ ላይ ከታች አንድ አስተያየት ጻፍኩ። ዳዊት የሚጋለጥ መሆኑ ሲገባው ወዲያው ጽሁፌን አነሳው። አሁን ይህንን የጉድ ጋዜጠኛ ስራ ታዩት ዘንድ የእሱን ሊንክ እና እውነተኛውን ዜና አያይዤ አቀርባለሁ፤ ፍርዱን ለናንተው ልተወው።
ምንአለበት እንዲህ ፣ እንደ ኢቲቪ፣ የዘቀጠ ስራ ሰርቶ ራሱን ከሚያዋርድ ፣ ትንሽ ስለ አማራ ተፈናቃዮች ዘገባ ቢሰራ።

No comments:

Post a Comment