ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከቤተመንግስት ላለመልቀቅ እያንገራገሩ ያሉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ተለዋጭ ቤተመንግስት እንዲሰራላቸው የጀመሩትን ጥያቄ በመግፋት ቦታ እያማረጡ ከቆዩ በሁዋላ ስድስት ኪሎ የሚገኘው አዲስ አበባ ስብሰባ ማዕከል እና የቀድሞ የአቅም ግንባታ ሚኒሰቴር ጊቢ ውስጥ ወደ 60ሺካሬ ሜትር በአንድነት እንዲሆን በመወሰን የግንባታ ጥናት ለማካሄድ የቤተመንግስት
አስተዳደር በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
አስተዳደር በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጅ ቦታው በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ አመራር ሰጪነት የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ባህሎች የሚጎለብትበት ማእከል እንዲሆን ባለፈው አመት በአዋጅ የተመሰረተው የብሄራዊ የባህል ማዕከል ሕጋዊ ይዞታ መሆኑ ታውቋል
ከአውሮፓ ህብረት በተገኘው የገንዘብ ዕርዳታ በቦታው ላይ የዕደጥበብ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የመሰረት ግንባታው ተጠናቋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስት ተቀምጠው የአገሪትዋ ጠ/ሚኒስትር ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው እየሰሩ የመሆኑ ጉዳይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ በኃላ ወ/ሮዋ ባለፈው ሳምንት ይህንኑ ቦታ በአካል ተገኝተው ጊቢውን
ተዘዋውረው ከተመለከቱ በሑዋላ ግንባታው ስምምነታቸውን በመግለጻቸው ወዲያውኑ ከአዲስአበባ አስተዳደር ግንባታው
እንዲቋረጥ የሚያዝ መመሪያ ተላልፎአል፡፡
ተዘዋውረው ከተመለከቱ በሑዋላ ግንባታው ስምምነታቸውን በመግለጻቸው ወዲያውኑ ከአዲስአበባ አስተዳደር ግንባታው
እንዲቋረጥ የሚያዝ መመሪያ ተላልፎአል፡፡
ግንባታውን የሚቆጣጠረው መንግስታዊው የኮንሰትራክሽን ዲዛይን አክሲዮን ማህበር ከፍተኛ ኃላፊዎች በተፈጠረው ሁኔታ ተደናግጠዋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት የማሰልጠኛው ግንባታ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በመገለፁ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ኮንትራክተሮች ተመርጠው ህንፃውን ለመገንባት በውስን ጨረታ እንዲወዳደሩ ተደርጎ እንደነበር፤ ግንባታውም ከፍተኛ ወጭ ፈሶበት መሰረቱ ከወጣ በኋላ እንዲቆም መታዘዙ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ሆኗል፡፡
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ለመልቀቅ ፈቃደና አለመሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment