በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ አወገዙ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ቁጥር ያላቸው በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጆሃንስበርግ ተነስተው የእንግሊዝ ቆንስላ ወደሚገኝበት ፕሪቶሪያ
በማምራት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘችው ዝናሽ ሃብታሙ ኢትዮጵያውያኑ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ነጻ እናወጣለን ማለታቸውን ገልጻለች
በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አሁንም ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ድጋፍ ከመግለጽ በተጨማሪ፣ በአገራቸው የስርአት ለውጥ ይመጣ ዘንድ እንደሚታገሉ ገልጸዋል።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚሰጠውን አስተያየት ተከትሎ ግንቦት7 ዛሬ ለመከላከያ እና ለፖሊስ ሰራዊት አባላት አገራዊ ጥሪ አስተላልፏል።
ግንቦት 7 ሰራዊቱና ፖሊስ የነፃነት ታጋዮችን እንዲቀላቀል፣ ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን እንዲቆም ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ የነጻነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል መሆኑንም ገልጿል።
No comments:
Post a Comment